Sunday, December 21, 2014

ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርአት መገለጫ ብቻ ሳይሆን የሰላማዊ ትግል ስልት አካል ጭምር ነው!

ተሾመ ዳባ
ምርጫ በአንባገነን መንግስት ውስጥ?
2007 electionምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርአት መገለጫ የሚሆነው ነጻ፣ ፍትሃዊና ተወዳዳሪ (free, fair and contested) ባህሪያትን የተላበሰ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ በኢ-ዴሞክራሲዊ መንግስት ውስጥ የሚደረጉ ምርጫዎች በምንም መመዘኛ የዴሞክራሲ ስርዓት መገለጫዎች አይሆኑም፡፡ በሀገራችን በአጼው፣ በደርግ እና በኢህአዴግ ዘመነ-መንግስታት ተደርገው የነበሩ ምርጫዎች የአጼውን፣ የደርጉንና የኢህአዴግን የአገዛዝ ስርዓቶች የስልጣን ዘመን ለማራዛም የተደረጉ (“mechanism of regime maintenance”) ምርጫዎች እንጂ አንዳቸውም የዴሞክራሲዊ ምርጫ ባህሪያትን የተላበሱ አይደሉም፡፡ በእርግጥ በባለፉት ሁለት የመንግስት ስርአቶችም ሆነ በኢህአዴግ ዘመነ-መንግስት የተደረጉ ምርጫዎች በተለያዩ የፖለቲካ አገዛዝ ስርአቶች ውስጥ እንደመደረጋቸውና በወቅቱ ካለው የሀገራችን የፖለቲካ ዕድገት አንጻር የተለያዩ ባህሪያትን የተላበሱ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ ግን በኢትዮጵያ ብቻ የታየ ሳይሆን በማንኛው ኢ-ዴሞክራሲያዊ መንግስት ውስጥ የሚደረጉ ምርጫዎች አጠቃላይ ገጽታ ነው፡፡

ተስፋዬ ገ/አብ ገዳ ከሰመረ አለሙ

ተስፋዬ ገ/አብ ለኤርትራ ነጻነት ታግሎ አገሬ የሚለዉን አገር ነጻ ከወጣ በሗላ በየጊዜዉ ኢትዮጵያን ሰፈር የሚያደርገዉን ቅሌት አስመለክተዉ ብዙዎች ዘግበዉታል በተለይም የተከበሩ የኢትዮጵያ ልጂ ኢንጂነር ዘዉገ አስፋዉ ተስፋዬ ስለሰዬ የማላዉቀዉ የለም ብሎ ሲቀባጥር በምሁር ብእራቸዉ ቢያበራዩትም ግለሰቡ ለእዉቀት ያልታደለ በመሆኑ አሁንም ኢትዮጵዉያን ሰፈር መተናኮሱን አላቆመም። ኤርትራ ዛሬ ምድር ላይ ያለ ችግር ተጠራቅሞ እሷ ላይ እንዳላረፈ ሁሉ ተስፋዬ ግን ለዉጊያ የመረጠዉ ሀገር ይችኑ ኢትዮጵያችንን ነዉ።
Tesfaye Gebreabተስፋዬ ገ/አብ በወጣትነት ዘመኑ በዘመኑ ሀገሪቱ ዉስጥ እንዳሉት ወጣቶች ተምሮ ወይ ተቀጥሮ ሊሰራ ባለመቻሉ በችሎታ ማነሰ ምክንያት ማለቴ ነዉ በወቅቱ በገፍ ልዩ ችሎታ ሳይጠይቅ ሁሉንም ያስተናግድ በነበረዉ በዉትድርና ዘርፍ ዉስጥ ተቀጥሮ ደርግን ሲያገልግል የቆየ ነበር። ችግሩ ዉትድርናዉንም በሀሞተ ቆራጥነት ሊወጣዉ ባለመቻሉ አንዴ በካድሬነት አንዴ በግጥም አንባቢነት የወቅቱን ጌቶቹን ሲያገለግል ቆይቶ የደርግ ዉድቀት አይቀሬ በመሆኑ ዘር አቋጥሮ ወደ ጠላት ጎራ ተቀላቅሎ ለመቀላቀሉ ግን የራሱን የሆን አንካሳ ምከንያት እየሰጠ በየጊዜዉ በመገለባበጥ የሚኖር ኤርትራዊ ነዉ።

ግፍና አፈና ዐመጽን ይወልዳሉ! (ያሬድ ኃይለማርያም)

የዐመጸኛ አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው (መ. ምሳሌ ም. 22፣  ቁ. 14)
ከያሬድ ኃይለማርያም
ብራስልስ፣ ቤልጂየም
ታኅሣሥ 10፣ 2007
ethiopia_flagሰብአዊ መበቶችን በመጣስ፣ ግፍ በመፈጸምና አፈናን በማጠናከር እደሜ የሚሸምት የአገዛዝ ሥርዓት የእያንዳንዱን ሰው መንፈሳዊና አካላዉ ጥንካሬ የማዳከም፣ ቅስምን የመስበርና ፍርሃትን የማንገስ ከፍተኛ አቅም እንዳለው ሁሉ በብሶት የሚወለዱ፣ እምቢኝ ለግፈኞች፣ እምቢኝ ለአንባገነኖች፣ እምቢኝ ለነጻነቴ የሚሉ መንፈሰ ጠንካራ ጀግኖችንና ታጋዮችንም ይወልዳል:: የአለማችን ስመ ጥርና ዘመን የማይረሳቸው የነጻነት ታጋዮች እነ ማህተመ ጋንዲ፣ ማርቲን ሉተር ኪነግ፣ ማንዴላ፣ ኡንግ ሳን ሱ ኪ እና ሌሎችም ብዙዎች የፈለቁት በብሶት ከተሞላ፣ ጭቆና ካንገሸገሸውና በአፋኝ ሥርዓት ከታመቀ ማኅበረሰቡ ጉያ ነው:: አንድን ማኅበረሰብ በአፈሙዝ፣ በሕግና በገንዘብ ኃይል ጭፍሎቆና አፍኖ ማቆየት የሚቻለውም ለተወሰነ ጊዜ ብቻ መሆኑን የእነዚህ ታጋዮች ገድልና የአለም ታሪክም ይመሰክራል:: አንድ ሕዝብ በላዩ ላይ ገዢዎች እየተፈራረቁበት ረዘም ላለ ጊዜ በአገዛዝ ሥርዓት ሥር ሊቆይ ይችል:: ይሁንና እድሜ ልክ የገዛ አፋኛ ሥርዓት ግን የለም::

የአንድነት መንገድ! (አስራት አብርሃም)


  • 45
     
    Share
አስራት አብርሃም
አስራት አብርሃም
አንድነት ለዴሞከራሲና ለፍትህ ፓርቲ በ2007 ምርጫ ከሁሉም ፓርቲዎች በተለየ ሁኔታ በጣም ግልፅና የማያሻማ የምርጫ እስትራቴጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ያለ ፓርቲ ነው። በዚህ ስሌትም የተዘጋውን የፖለቲካ ምህደር ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር ማስከፈት እንደሚችል አምኖ በምርጫው በሙሉ ልብ ለመሳተፍ ወስኗል። በዚህ ምክንያትም የያዘውን የምርጫና የሰላማዊ ትግል መስመር አስቀድሞ በይፋ በማወጅ የመርህ ፓርቲ መሆኑ አስመስክሯል። ይሄ አቋሙ በምርጫው እንደሚሳተፉ እርግጠኛ ሳይሆኑ የምርጫ ምልክት ከወሰዱ ፓርቲዎችና በሂደቱ ዝም ብለው በደመነፍስ ከገቡ ፓርቲዎች በእርግጠኝነት የተሻለ አቅጣጫ ያስቀመጠ ፓርቲ እንዲሆን አድርጎታል።

ድንቄም ጠቅላይ ሚኒሴቴር!

ወንድሙ መኰንን፣ ከብሪታኒያ 19 December 2014
ብዙ ተብሏል። እኔም አንድ ነገር ልጨምርና ልገላገለው። “የጊዮርጊስን መገበሪያ የበላ ሲለፈልፍ ይኖራል” ነው የሚባለው? ተናግሮ ከሚያናግር ይሰውራችሁ! ውሀን ምን ነበር የሚያናግረው? ድንጋይ! የሰውም ድንጋይ እራስ አለ! ይቅርታ አንጀቴ አርሮ ነው!
prime minister
ሦስት መንግስታትን የማየት ዕድል አጋጥሞኛል። ተወልጄ፣ አድጌ፣ ተምሬ ለዩኒበርሲቲ የበቃኹት በንጉሠ ነገሥቱ ዘመነ መንግሥት ነበር። ዕውነቱን እንናገር ከተባለ፣ ንጉሡ ሲናገሩም ሆነ ሲራመዱ፣ የርዕሰ ብሔርነት ግርማ ሞገስ ነበራቸው። “በንጉሥ መገዛቱ ጊዜ ያለፈበት፣ ያረጀ ያፈጀ፣ ገበሬውን በገባርነት ጠፍንጎ የያዘ፣ አገሪቱ በዕድገት ወደፊት እንዳትራመድ ያገዳት፣ ኋላ ቀር የፊውዳል ሥርዓት ነውና ወደሶሻሊዝም እንለውጣት” የሚሉ ድምጾች ከተማረው ክፍል አካባቢ እያየሉ መጡና እኛንም እንደጎርፍ ይዘውን ነጎዱ። ተከተልናቸው።

ግርማ ሠይፉ፣ ሠራዊት ፍቅሬና ቴዎድሮስ አድሐኖም ያልመረጥናቸው የህዝብ ልዑካን (ሁኔ አበሲኒያ)

ከሠሞኑ ወደግብፅ የሚያቀና ህወሀታዊ የልዑካን ቡድን ሲቋቋም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊጠብቀው በማይችለው መልኩ የልኡካን ቡድኑ ውስጥ የአንድ ሠው ስም ተሠማ “ግርማ ሠይፉ” የሚል በርካቶች ተገረሙ ወይ አንቺ ሐገር ሲሉም አዘኑ፡፡ ከዚህ ቀደም ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በፓርላማ ተብለው በተቀመጡባቸው ያለፉት 4 ዓመታት ለሐገራችን ፖለቲካ ያንን ያህል ለውጥ ባያመጡም፤ የህሊና እስረኞቹ ይፈቱ ዘንድ አሁንም ያንን ያህል ጠንከር ያለ ስረ ባይሠሩም አቶ ግርማ ሠይፉን ሌሎች አካላት ሲተቿቸው ግርማ ሠይፉን ደግፈው ከሚቆሙ አካላት መካከል አንዱ እኔ ነበርኩኝ ብዬ አስባለው፤ አስባለው ያልኩት ስለግርማ ሠይፉ ከኔ በላይም የሚያስብ ሌላ ህወሀት የተሠኘ የሠዎች ስብስብ መኖሩን ስላልተረዳሁና በቅርቡ እየታዩ ያሉትን የግርማን መንሸራተቶች ባለመመልከቴ ነበር፡፡

የፍረጃ ፖለቲካ አይጠቅመንም! መልስ ለሁኔ አቢሲኒያ ( ግሬስ አባተ)

በመጀመሪያ ይህን ፅሁፍ የምፅፍልህ ሌላውን ወገን ወግኜ ሳይሆን ይህ አካሄድ በመሰረታዊነት ትግሉን የሚጎዳ ስለሚመስለኝ ነው፡፡ በምንም ጉዳይ ትግሉን አንድ ኢንች በሚጎዳ ነገር ዝምታን አልመርጥም፡፡ ሲጀመር ሰራዊት ፍቅሬንና የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉን በአንድ ሚዛን ላይ የሚቀመጡ ግለሰቦች አንዳይደሉ በደንብ የምታውቅ ይመስለኛል፡፡ የቆሙለት አላማ በራሱ ይህንን አስረግጦ ስለሚነግረን በዚህ ላይ ጊዜ ማባከኑ ትርጉም የለውም፡፡ የመረጥከው ርዕስ በራሱ ሶስቱን ለይተህ ማቅረብህ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡ ያልመረጥናቸው ስትል ቀሪዎቹን ወይ መርጠሃቸዋል ወይ ይሁንታ ሰጥተሃቸዋል ማለት ነው፡፡
(ግርማ ሰይፉ)
(ግርማ ሰይፉ)
ያልመረጥናቸው ከምትል ይልቅ በምን መስፈርት ተመረጡ ብትል ጥሩ ይሆን ነበር፡፡ መብትህም ስለሆነ ! እንደምታውቀው የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ የተቋውሞው ፖለቲካ ብቸኛ የፓርላማ ተወካይ ናቸው፡፡ እንደምታውቀው የተቃውሞ ጎራው የግድቡን ጉዳይ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ መዋሉ በተለይም የአረቡ አብዮት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመጣ ለማስቀየሻ የተመዘዘ እና በቂ ጥናት ሳይደረግበት ወደ ስራ በመገባቱ እንጂ የሚቃወሙት ግድቡ ለምን ተገነባ በሚል አይደለም፡፡ ስለዚህ አቶ ግርማ የፓርላማ አባል በመሆናቸው ብቻ የዚህ ልዑክ አካል መሆን ቢችሉ ብዙም የሚገርም አይደለም፡፡

ይህም አልፎ እናየው ይሆናል

ከደቂቃዎች በፊት ሠንጋተራ አካባቢ ነበርኩ፡፡ አንድ ቦታ ላይ ችምችም ብለው የተሠሩና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ሦስት ትላልቅ ሕንጻዎችን አየሁ፡፡ ለቀድሞው ቁጭራ ሠንጋራ ከፍተኛ ግርማ ሞገስ አላብሰውታል፡፡ ከአንድ ሰው ጋር ስለነበርኩ ወሬ ለማጧጧፍ ፈለግሁና በቀልድ መልክ “እርግጠኛ ነኝ እነዚህ ሕንጻዎች የትግሬ መሆን አለባቸው” አልኩ፡፡ ያ አብሮኝ የነበረ ሰው ለካንስ ዝርሩን ያውቅ ኖሮ ቀጣዩን ታሪክ አጫወተኝ፡፡ እኔም ይህ ዓይነቱ ነገር ቢያስጠላኝም ታሪክን እየመዘገቡ ላሉ ሰዎች አንዳች ግባት ይሆናል በሚል እሳቤ ባጭሩ ልነግራችሁ ወደድኩ፡፡ ለነገሩ ሳይመዘገብ የቀረ ወያኔዊ ቅሌት ሲኖር አይደል! ለማንኛውም ምድረ አበሻ በምቀኝነት ተንጨርጨሪ እንጂ ይህችን የሰማሁዋትን ነገር አሁኑኑ እዘረግፋታለሁ፡፡

ዛሬ በባህርዳር ፋሽስቱ የኢሕአዴግ መንግስት ያቆሰላቸውና የገደላቸው ክርስቲያኖች (ፎቶ በጥቂቱ)

(ዘሐበሻ) የእምነት ቦታችን ተላልፎ ለባለሃብት አይሸጥም በሚል ጥያቄ በማንሳት ኣደባባይ በወጡት ክርስቲያኖች ላይ ኣምባገነኑ የኢህኣዴግ መንግስት ጥይት ሲያረግፍባቸው ውሎ ፫ ሰዎችን አና ፯ ሰዎችን ማቁሰሉን ዘሐበሻ ቀደም ብላ ዘግባ ነበር። የሞቱት ቁጥር ወደ ፯ አንዳደገ የቆሰሉት ደግሞ ከ፳ በላይ አንደሚደርስ ኣሁን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። አርምጃ ከተወሰደባቸውና ህይወታቸው ካለፉት መካከልም ፎቶዎች ኣግኝተናል ይመልከቱት።

በባህርዳር ከተማ በንፁሀን ዜጎች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ያደረሱ በህግ ፊት ይቅረቡ! – ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በትናንትናው ዕለት ታህሳስ 10/ 2007 ዓም በባህርዳር ከተማ መንግስት ኃይሎች የጥምቀት ክብረ በዓል ታቦት የሚያርፍበትን ቦታ ሊፈርስ ነው በመባሉ ምክንያት ስሞታ ለማሰማት ወደ አስተዳደሩ ጽ/ቤት ያመሩ ንፁሃን ዜጎች ላይ የመንግስት ኃይሎች የወሰዱትን የግዲያና የድብደባ ህገወጥ ተግባር ያወግዛል።

ህዝብ ያለው ድምጽ ነው፤ ግን ይህን ድምጽ የሚሰበስበው ማን ነው?

ዊት ሰለሞን
በአዲስ አበባ በታላቁ ኑር መስጊድ ለመቶ ምናምን ግዜኛ ጨዋው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ድምጹን አሰምቷል፡፡የታሰሩት ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣መጅሊሱ ከመንግስት ተጽእኖ እንዲላቀቅ ወዘተ ጠይቀዋል፡፡ተቃውሞው ከተጀመረ ሶስተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡
bbnደርግ አሸንፎ በመምጣቱ ምንም ነገር እንደማያቅተው የሚያምነው ኢህአዴግ አሁንም በጫካው ህግ የሚመራ በመሆኑ ለህዝቡ ጩህት በራሱ መዝገበ ቃላት ተገቢ ነው ያለውን ምላሽ ሰጥቷል፡፡ከፍተኛ ዝና እና ተቀባይነት የነበራቸውን ሰላም ፈላጊ ተደራዳሪዎች በአንድ ምሽት ለቃቅሞ በማሰር
‹‹ሽብርተኛ››ብሏቸዋል፡፡ርህራሄ አልባ በሆኑ ታጣቂዎች ደም እንደ ጅረት ፈሷል ኢህአዴግ ላለፉት ሶስት ዓመታት የሰጠው ምላሽ ሀይል የተቀላቀለበት ነበር፡፡ህዙ ግን ድምጹን ከማሰማት አላመነታም፡፡
በእኔ እምነት ‹‹መንግስት የለም ወይ››በማለት ህዝብ ጥያቄ ሲያቀርብ ኢህአዴግ አለሁ ያለው በመግደል፣በማሰርና በማሰቃየት ብቻ ነው፡፡ኢህአዴግ ከዚህ የዘለለ ምላሽ ለመስጠት ጠረጴዛ ስቦ የሚቀመጥበት ወኔ ወይም አፈጣጠር የለውም፡፡

“ኦ ባህር ዳር! ” (ነቢዩ ሲራክ)


  • 1425
     
    Share
bahr dar 2ሀገር ይዘን ፣ ሀገር አጥተን
ሰው ሞልቶ ፣ ሰው ጠፍቶብን
ባህር ወደን ፣ ባህር አጥተን
ባህር ይዘን ፣ ውሃ ጠምቶን
እውንት ይዘን ፣ ውሸት ተብለን
ድህነትን አቅፈን ፣ አድገት እያልን
ሰብዕናውን ሳናስቀድም ትተን
በእድገታችን ልማት ተመጻድቀን
የመናገር መጻፍ ፣ መቃወሙን
ፈጣሪ የሰጠንን መበት ተነፍጎን
ፈጣሪ አያለ  ፣ ሰው አምልከን
ሹም እያለ  ፣ ፍትህ ርቆን
የባህር ዳሩ ማህበል አይሎብን
ሰው ተጎዳ ፣ ሀዘን ጎዳን …

በባህርዳር የሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተደረገውን የጅምላ ግድያና ድብደባ እናወግዛለን »

አገር በቀል የሆነው፤ የቅኝ አገዛዝና ዘረኛው የወያኔ ሰርአት በባህር ዳር የሚኖሩ ወገኖቻችንን ላይ በትናንትናው እለት ያደረገውን የጅምላ ግድያና ድብደባ አሁንም በታላቅ ቁጭትና ሀዘን ለማየት ተገደናል። በተለይ አካለ ስንኩላንና በእድሜ የገፉ አዛውንት በድብደባ ቆስለው ማየት ምን ያህል ልብ የሚያደማና የስርአቱን ኢሰብአዊነትና ጨካኝነት አሁንም ደግሞ ደጋግሞ የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ ይህንን ዘግናኝ ወንጀል የፈጸሙት የስርአቱ አራማጆች አንድ ቀን ለፍርድ በሚቀርቡበት አደባባይ በመረጃነት የሚያዝ ይሆናል። ምንም እንኳን የመሳሪያና የዱላ እሩምታውን ቢያወርድበት፤ ቆራጡ የባህር ዳር ህዝብ ይህንን ተቋቁሞ ምሬቱን መግለጽ ብቻ ሳይሆን ከትግል አጋሩ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር፤ ይህንን የበሰበሰ ስርአት ከተከሻው አሽቀንጥሮ የሚጥልበት ጊዜ ሩቅ አይደለም።

Tuesday, December 16, 2014

ሕዝባዊ ዕንቢተኝነት ለኢትዮጵያ ትንሳኤ!

ነብዩ ኃይሉ
ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ.ም ዘጠኝ ፓርቲዎች ያቋቋሙት ትብብር የጠራው የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ፣ በገዢው ቡድን ውንብድና ከተስተጓጎለ በኋላ ስለሰላማዊ ትግል አይረቤነት የተለያዩ አስተያየቶች በመሰጠት ላይ ናቸው፡፡ የተወኑት አስተያየቶች “ትግሉ አልጋ በአልጋ መሆን አለበት” ከሚል የዋህ ልቡና የመነጩ የተስፋ መቁረጥ ስሜቶች ቢሆኑም፤ ጥቂት የማይባሉት ግን የህብረተሰቡን ቀልብ ከሰላማዊ ትግል አውድ ለማፋለስ ታቅደው የሚሰነዘሩ ይመስላሉ፡፡
Tensaye
በመሰረተ-ሀሳብ ደረጃ የትኛውንም የአገዛዝ ስርዓት ለመጣል የሚደረግ ትግል በአንድ ወጥ ቀኖናዊ የትግል ስልት ላይ ብቻ መመስረት ይገባዋል የሚል ድምዳሜ መስጠት አይቻልም፡፡ ሆኖም ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የትኛው የትግል ስልት ያዋጣል የሚለውን በኃላፊነት ስሜት የመምረጡ ተግባር ለታጋዩ የሚሰጥ ነው፡፡ በየትኛውም መለኪያ በትግል ላይ የሚፈጠር እንቅፋት ሁሉ ስልቱን ጥያቄ ምልክት ውስጥ ሊከት ግን አይችልም፡፡

Sunday, December 14, 2014

ውይ! አምባሳደሩ ተናገሩ!

ወንድሙ መኰንን፣ ብሪታኒያ
የዛሬ 30 ዓመት ገደማ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሒሣብ መዝገበ አያያዝ ትምሐርት አስተምር ነበር። ዛሬም በሱው ነው እንጀራዬን በስደት ዓለም ከስቃይ ጋር እንደወጥ እያጣቀስኩ የምበላው። ታዲያ ያኔ፣ የመምሕራን ካፌቴሪያ ለምሳ በየጠረጴዛው ዙሪያ በቡድን በቡድን እየተሰበሰብን አንዳንድ ክፍል ውስጥ ያጋጠሙን ገጠመኞች እያነሳን እንስቅ ነበር። አንድ ዕውቅ የኢኮኖሚክስ መምሕር ነበሩ። እግዚአብሔር ይመስገንና፣ ዛሬም በሕይወት አሉ። ስማቸውን ግን አልጠቅስም። ታዲያ አንድ ቀን ከጎናችን ካለው ጠረጴዛ ላይ ሁነው ምሳ እየበሉ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በዕለቱ ያጋጠማቸውን አስቂኝ ክስተት ሲገልጹ፣ ጆሮዬን ጣል አድርጌ እንደዋዛ እሰማቸው ነበር። ነገሩ እንዲህ ነው። አንዳንድ ጠጠር ያሉ የኢኮኖሚክስ ጽንሰ-ሀሳቦችን አንስተው ሲያስተምሩ፣ አንድ ወጣት ተማሪ ነገሩ ከብዶት ነው መሰል፣ ሳያስበው እንቅልፍ ይዞት ለሽ ይላል። ያንን ያዩት ዕውቁ የኢኮኖሚክስ ባለሙያ፣ ድምጻቸውን በድንገት በጣም ክፍ በማድረግ፣ ጮክ ብለው ማስተማር ይጀምራሉ።

ጀግኖችን እያሰብን የበኩላችንን እንወጣ!! በመስዋዕትነት ነፃነት ይረጋገጣል፤ ሰላም ይሰፍናል። (በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ)

teachers associationመምሀር የኔሰው ገብሬ በዳውሮ ከተማ ነዋሪና ትጉህ መምህር ነበር። እንደማንኛውም አገር ወዳድና የወገን ተቆርቋሪ እርሱም የወያኔ/ኢህአዴግ ሥርዓተ መንግሥት በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ገደብ የለሽ ሰቆቃ መቀበል ባለመቻሉ ፣ በአንፃሩ በተቃውሞ አቋሙን በአደባባይ የሚገልጽና ይህ እኩይ ድርጊት እንዲቆም ታግሎ ለማታገል በጽናት ስለቆመ የሥርዓቱ ሰለባ ሆነ። እስራቱና እንግልቱ አልበቃ ብሎ ከሥራ መደቡም ተገለለ ። በዚያው ላይ ፍትህ ለማግኘት የሚያስብ ሕሊናና የሚሰማ ጆሮ እንደሌለ ተረድቶ ለአሰቃዩትም ለአጠቃላይ ሕዝቡም መራር መልእክት ያስታላልፋል ብሎ ያሰበውን መስዋዕትነት መርጦ ራሱን በጋዝ አንድዶ ሕዳር 1 ቀን 2004 ዓ.ም መስዋዕት ሆነ።

ሕወሐት ደ/ፂዮንን ጠ/ሚ/ር ለማድረግ አቅዷል * የአዜብና የደህንነቱ ሹም ያልታሳካ እቅድ

Debretsion
(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
የጠ/ሚ/ር ስልጣን ወደ ሕወሐት ለመመለስ የፓርቲው ቁልፍ አመራሮች በምስጢር ሲመክሩ መስንበታቸውን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በአቶ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ፣ ፀጋይ በርሔ፣ አርከበ እቁባይና ስብሃት ነጋ የሚመራው የሕወሐት ከፍተኛ አመራሮች ከዚህ ቀደም ሲካሂዱት በነበረውና ህወሀት የጠ/ሚ/ ርነት ስልጣን መልሶ መያዝ ይኖርበታል፣ የሚለውን ምክክር ከዳር ለማድረስ አቋም መያዘያቸውን ያስታወቁት ምንጮቹ በተለይ በቅርቡ የተካሄደው የአራቱ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ በብአዴንና ኦህዴድ በኩል ቅሬታና ተቃውሞ እየበረታ በመምጣቱ የሕወሐት አመራሮች ስልጣኑን በእጃቸው ለማስገባት ቆርጠው መነሳታቸውን አስረድተዋል። በብአዴን በኩል የአቶ በረከት ስሞን ከስልጣን መገፋት በደጋፊዎችቻቸውና አመራሩ በኩል ቅሬታ መፍጠሩን የጠቆሙት ምንጮቹ በረከት ስሞን የጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም አማካሪ ተብለው ቢሾሙም ነገር ግን በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት ቢሮ እንዳልተሰጣቸውና የተሰጣቸው ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው የቀድሞ የደህንነት ቢሮ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀው በዚህ ቢሮ ኩማ ደመቅሳ እንደሚገኙና በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት አዲስ ቢሮ ተገንብቶ ይሰጣችኋል የተባለው ተግባራዊ እንዳልሆነ አያይዘው አስረድተዋል። በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት ቢሮ የተሰጣቸውና ከአቶ ሃ/ማርያም እያንዳንዷ እንቅስቃሴ ያልተለዩት አርከበ እቁባይ፣ አባይ ፀሐዬና ፀጋይ በርሄ ሲጠቀሱ በም/ጠ/ሚ/ር ቦታ ደብረፂዮን መኖራቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል።

የወያኔ መንግስት እስካሁን ድረስ በአፋር ህዝብ ላይ ያየውን ትዕግስት እንደ ፊራቻ ወይም አለማወቅ ወሰዶታል

afar
አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦
በአፋር ህዝብና በዒሳ ብሄረሰብ መሀከል ለብዙ ዘመናት የቆየው የብዙ ሰዎች ህይዎት ያለፈበት የድምበር ግጭት በብዙ መንግስታት ዘላቂ መፍትሄ ሳያገኝ ለዚህ አሰከፊ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይሁንና የአፋር ህዝብና ሶማሊኛ ተናጋሪው የዒሳ ብሄረሰብ አሁንም በኢህአዴግ መንግስት ዘላቂ መፍትሄ አላገኘም። ባለፉት ሁለት አስር አመታት የደቡብ አፋር ነዋሪዎችና ዒሳዎች መሃከል በተከሰተው ደም አፋሳሽ በሆነው ግጭት ከሁለቱም ብሄሮች ብዙ ሰዎች ሞተዋል። ከሶማሌ ክልል ከሺኒሌ ዞን በኮንትሮባንድ ስራ ወደ አፋር ክልል እየተጠጉ እዛ አካባቢ ሲኖሩ የነበሩ የአፋር ነዋሪዎችን በማሸበር የአፋር መሬትን በሃይል መያዛቸውን የሚነገርላቸው ዒሳዎች ከዚህም ባለፈ የብዙ አፋሮችን ግመሎች፣ ከብቶችና ንብረቶች ዘርፈዋል።

DUBAI HOLDING CONFIRM KENENISA BEKELE FOR STANDARD CHARTERED DUBAI MARATHON

* Legend To Compete as Ambassador for the Dubai Holding Wellness Programme
Dubai (UAE) 14 December, 2014:
the 2015 Standard Chartered Dubai Marathon announcing the participation of Ethiopia’s Kenenisa Bekele at the event on January 23, 2015.
the 2015 Standard Chartered Dubai Marathon announcing the participation of Ethiopia’s Kenenisa Bekele at the event on January 23, 2015.
Dubai Holding, the investment holding company, has announced that three-time Olympic Champion Kenenisa Bekele of Ethiopia will take part in the Standard Chartered Dubai Marathon on January 23, 2015 in his capacity as Ambassador of the Dubai Holding Wellness Programme.
The Dubai debut appearance of one of the greatest long distance athletes of all time will once again turn the spotlight on the world’s richest marathon as the 32 year-old competes in just the third marathon of what is an illustrious career.

አንድነት በጥቂት ቀናት ውስጥ የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ በስክት ተጠናቋል

አንድነት በጥቂት ቀናት ውስጥ የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ በስክት ተጠናቋል፤ የፓርቲው ተ/ም/ፕሬዝዳንት አቶ ተክሌ በቀለ የጉባኤውን የመዝጊያ ንግግር በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ አቶ ተክሌ በንግግራቸው አንድነት በብሔርም ሆነ በህብረብሔር ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመስራት መዘጋጀቱን እንዲሁም ከአንድነት ጋር ተመሳሳይ ፕሮግራም ላላቸው ፓርቲዎች ሁሉ የውህደት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ አቶ ተክሌ አክለውም አንድነት የ2007 ምርጫን በአሸናፊነት ለመወጣት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡
10801506_830102687048482_9079775044209922653_n
10847773_830102467048504_99358985024134609_n
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከትላንት ጀምሮ እያካሄደ ባለው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው፤ በዛሬው መርሀ ግብር በሀገሪቱ ነባራዊ ሁናቴዎች(የአርሶ አደሩ ፤የከተማው ነዋሪ፤የባለሐብቱ ሁናቴ) በዳግማዊ ተሰማ የተማሪውና የምሁሩ ሁናቴ በጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ የአንድነት የምርጫ ስትራቴጂ ግብ በፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ በላይ ፈቃዱ ቀርቦአል፡፡

በቅስቀሳው ወቅት የታሰሩት አመራሮችና አባላት አሁንም አልተፈቱም

ነገረ ኢትዮጵያ
10687129_627440187381643_6931792570194490039_nለ24ቱ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ እያሉ የታሰሩት ማቲያስ መኩሪያ የሰማያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ ህዝብ ግንኙነትና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ፣ ባህረን እሸቱ የምርጫ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ኃላፊ እንዲሁም ሲሳይ ዘርፉ እስካሁን ድረስ አልተፈቱም፡፡ ባህረን እሸቱና ማቲያስ መኩሪያ ከ30 በላይ እስረኞች ሶስት በአራት በሆነ ክፍል ታጭቀው በሚታሰሩበት ወረዳ 9፤ እንዲሁም ሲሳይ ዘርፉ ላዛሪስት በሚባል እስር ቤት ታስረው የሚገኙ ሲሆን ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ተገልጾአል፡፡
ሶስቱም ታሳሪዎች ‹‹ለህገ ወጥ ሰላማዊ ሰልፍ በመቀስቀስ›› በሚል ክስ ቀረበባቸው ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የታሰሩት አመራሮች፣ አባላትና ተሳታፊዎች እነዚህ እስረኞች ላይ ከቀረበው በበለጠ ‹‹ህገ መንግስቱን በመናድ›› በሚል ክስ ተከሰው 14 ቀን ቀነ ቀጠሮ ከተሰጠባቸው በኋላ ቀድመው መፈታታቸው ይታወቃል፡፡

የመድረክ ሰለማዊ ሰልፍ ተጠናቀቀ::

የመድረክ የወጣቶች ክንፍ ከፖሊስ እና ከፀጥታ አካላት እጅና ጓዋንት ሆኖ የክትትል፤ የኢንተለጀንስ እና የቁጥጥር ስራውን በአግባቡ እንዲሚወጣ ለመግለፅ እንፈልጋልን፡፡ የሚል የህዝብ ግንኙነት ስራ ትዝብት ውስጥ የጣለው የመድረክ ፓርቲ ከገንፍሌ ተነስቶ፣ በኣዋሬ ኣልፎ በየካ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ኳስ ሜዳ መጨረሻው ያደረገው ሰለማዊ ሰልፍ ተጠናቀቀ።
10411210_1519465441657186_7328125686046851094_nበዘጠኙ ፓርቲ ላይ የደረሰውን እስር ድብደባ እና እንግልት እንዳላወገዘ የሚነገርለት መድረክ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሁለት ሺህ የሚጠጋ የኣዲስ ኣበባ ኑዋሪ የተሳተፈበት ሰልፍ በወጣቶች የመድረክ ኣመራር፣ የሴቶች ተወካይ፣ ኣቶ ቡልቻ ሚደቅሳና የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ዼጥሮስ ባሰሙት ንግግሮች ተጠቃሏል።
ሰለማዊ ሰልፉ የኢህኣዴግ መንግስት ሊያርማቸው የሚገቡ፣ መመቻቸት ያሉባቸው ፖለቲካዊ ምህዳር፣ መወገድ ያለበት የፀረ ሽብር ህግ ፣ ምርጫው ፍትሃዊ እንዲሆን ሊያደረጉ የሚገቡ ስራዎች እንዲሰሩ፣ በየቦታው እያጋጠመ ያለው ዓፈና፣ እስርና እንዲሁም ግድያዎች እንዲቆሙ ጥሪ ቀርበዋል።

Saturday, December 13, 2014

አንዳርጋቸው ፅጌ እንዴት ተያዘ? – ከተስፋዬ ገብረአብ (Gadaa)

Andargachew Tsigeአንዳርጋቸው ፅጌን ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት የ2014 የፋሲካ በአል በዋለ ማግስት ነበር። ወደ ለንደን መንገድ ስለነበረው ከተከዜ በረሃ ወደ አስመራ መጥቶ ሳለ ደወለልኝና ተገናኘን። ሳገኘው ታሞ ነበር። ከምግብ ወይም ከውሃ ጋር የተያያዘ ቀላል ህመም እንደሆነ ነገረኝና ወደ ፋርማሲ ሄደን መድሃኒት ገዛን። እየደወልኩ ስለ ጤንነቱ ስጠይቀው ቆየሁ። በሶስተኛው ቀን ተሲያት ላይ ይመስለኛል ወደ ቤቱ ብቅ አልኩ። የግቢውን በር ገፍቼ ስገባ አንዳርጋቸው በሁለት እጆቹ ልሙጥ የባህር ድንጋዮችን ተሸክሞ ቁጭ ብድግ እያለ ስፖርት ሲሰራ አገኘሁት። ማጅር ግንዱ በላብ ርሶአል። ግቢው ውስጥ ካለችው የብርቱካን ዛፍ ላይ ያንጠለጠለውን ፎጣ አንስቶ ላቦቱን ማደራረቅ ያዘ።