Friday, August 28, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ ኣባል አቤል ኤፍሬም ጓደኞቹ እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር ሆኖ ቀረበ

 ነው፤ በመሆኑም የአቃቤ ህግ ምስክር ሊሰማብን አይገባም›› በሚል ተቃውሞ ቢያቀርቡም አቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ ባስገባው ክስ ላይ ምስክሩን መጥቀሱን በማስረዳት ምስክሩ እንዲሰሙለት ጠይቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የደረሰው የክስ ማመልከቻ ላይ ምስክር እንደተመዘገበ በማረጋገጥም ብቸኛ ሆነው የቀረቡትን አንድ የአቃቤ ህግ ምስክር ሰምቷል፡፡ ምስክሩም ከ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሰሾች ጋር ሰማያዊ ፓርቲ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ሆነው እንደሚተዋወቁ፣ የካቲት 12/2007 ዓ.ም በ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ሰላማዊ ትግሉ እንዳላዋጣ በመጥቀስ ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ መጓዝ ማሰባቸውን ገልጸውለት በዚያው ቀን ማታ 3ኛ ተከሳሽን ጨምሮ ወደ ባህር ዳር እንደተጓዙ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
ባህር ዳር ሲደርሱ ጠዋት ላይ ግን ምስክሩ ሀሳቡን በመቀየር ወደ አዲስ አበባ መመለስ እንደሚፈልግ እንደገለጸላቸው፣ 1ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ‹ጎንደር ላይ የምናገኘው ሰው ስላለ ቢያንስ እሱን ካገኘኸው በኋላ መመለስ ትችላለህ› እናዳለው፣ ነገር ግን ምስክሩ በሀሳቡ ባለመስማማት ወደ አዲስ አበባ መመለሱንና ሌሎቹ ሦስቱ ግን ጉዟቸውን መቀጠላቸውን አስረድቷል፡፡

Monday, August 24, 2015

ፍርድ ቤት በነጻ እንዲለቀቁ የበየነላቸው አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ እንዳይፈቱ እገዳ ተላለፈ –

(ነገረ ኢትዮጵያ) ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብርተኝነት ክስ ነጻ ናችሁ ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች የሆኑት አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሶ ነጻ የተባለው አብርሃም ሰለሞን ከእስር እንዳይለቀቁ ታግደዋል፡፡ አቃቤ ህግ ይግባኝ እንደጠየቀባቸው የታወቀ ቢሆንም እንደ ህግ ባለሙያዎች ግን የአቃቤ ህግ ይግባኝ ገና ተቀባይነት ባላገኘበት ሁኔታ ከእስር እንዳይለቀቁ እግድ ማድረግ ከህግ ውጭ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡ ነጻ የተባሉት አመራሮች ባለፈው አርብ ከእስር ይወጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም አሁን ድረስ እስር ቤት እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

Monday, August 17, 2015

አንዳርጋቸውና ጓዶቹ

አምና ሰኔ 2006 ዓ ም አንዳርጋቸው ጽጌ በትራንዚት ላይ እያለ ከየመን በወያኔ መታፈኑ ሲነገር ሃዘንና ንዴት ያልተሰማው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም። ወያኔ ኤርትራ ውስጥ እንዳለ ሊገድለው ያደረገውን ሙከራ ኢሳት በተከታታይ ስላቀረበው ምን ያህል አዳጋ ውስጥ እንዳለ ለሁሉም ግልፅ ነበር። የአንዳርጋቸው መያዝ ከታለመው ግብ በተፃራሪ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ከዳር ዳር በቁጣ በማንቀሳቀሱ አፋኞቹ አምባገነኖች ከጠበቁት ውጭ ራሳቸውን ችግር ውስጥ ነው ያገኙት። መታፈኑ ለአስርት ዓመታት አፍዝዞ የያዘን ፍርሃትንና ክፍፍልን ሰባብሮ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በጋራ እንዲቆም ከማድረጉም በላይ አንዳርጋቸው የደላ ኑሮውን ትቶ በረሃ ለበረሃ የተንከራተተለት፣ በርሃብና በበሽታ የተንገላታለት፣ ከጓዶቹ ጋር ለኢትዮጵያውያን ነፃነት ይበጃል ብሎ የደከመለት ግንቦት ሰባት በብዙ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ እንዲገባና የማይነጥፍ ድጋፍ ባልተጠበቀ ፍጥነት እንዲያገኝ ሲያደርግ የወያኔንና የመሰሎችን ጎራ ናዳ ልኮባቸዋል። በተለይም በክፍፍልና በፍርሃት ተሸብቦ የነበረው ውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ከወትሮው በተለዬ ዘላቂ ለሆነ ትግል ራሱን ማዘጋጀቱን በተለያዩ እንቅስቃሴዎቹ እያሳየ ሲሆን አገር ውስጥ በሰላማዊ ትግል ይሳተፉ የነበሩ በርካታ ወጣቶች ቁጭ ብሎ ከመታሰር በርሃ እያቆራረጡ ወደትግሉ መቀላቀላቸውና ሌላውም ህዝብ መነሳሳትን ማሳየቱን ወያኔዎችም ሊደብቁት አልተቻላቸውም።Andargachew Tsege and his friends
አንዳርጋቸው የህይወት ተልዕኮውን በሚገባ ተወጥቷል። የግንቦት ሰባትን መሰረት ጥሏል። ከሌሎች ጋር ተባብሮ የመስራትን በር ከፍቷል። ከሁሉም በላይ የአንድ መሪ ሥራና ተልዕኮ አርዐያ መሆን ነውና በድፍረት በትግሉ ወላፈን ውስጥ ራሱን ማግዶ በማሳየቱ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን አነቃንቋል። ጠላቶቹም ሳይቀሩ ሊያከብሩት ያስገደደ ድርጊት ሆኗል። ዛሬ ወያኔ መጨበጫ አጥቶ እንደሚጨነቅ ሰሞኑን ቴዎድሮስ አድሃኖምን ማዳመጡ ብቻ በቂ ነው። አንዳርጋቸው በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ወያኔን የሚያውቅ ሁሉ ይረዳዋል። አንዳርጋቸው ችቦውን ለኩሶ ለተከታዩ ትውልድ አስተላልፏል።

ሰበር ዜና (Breaking News) “አንገነጠልም – ትግላችን የኦሮሞ ሕዝብ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ነው” – ብ/ ጀነራል ኃይሉ ጎንፋ ከአስመራ (የሚደመጥ)

ከሁለት ሳምንት በፊት አራት የኦነግ ድርጅቶች ወደ አንድ መምጣታቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል:: ይህን ተከትሎ ከአውስትራሊያ የሚሰራጨው ሲቢኤስ ራድዮ ብ/ጄ ኃይሉ ጎንፋ፤ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር – ኦነግ (በአባ ነጋ ጃራ የሚመራው) ምክትል ሊቀ መንበር፤ ስለ ኦነግ ዳግም መሰባሰብ አነጋግሯቸዋል:: ጄነራሉ ተበታትነን ምንም አናመጣም ብለዋል:: “ኦነግ የሚለውን ስያሜ በባለቤትነት እኔ ነኝ ብሎ የሚወስደው ማን ነው?” ለሚለው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል:: ያድምጡት::
General

Saturday, August 15, 2015

በምዕራብ ጎጃም የብአዴን አባላት አርበኞች ግንቦት 7 ውስጣችን ሰርጎ ገብቷል በሚል እርስበርስ እየተወነጃጀሉ መሆኑ ተሰማ * ክፍፍሉንም አባብሶታል

በምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራሮች መካከል መከፋፈል ተፈጠረ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው የምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራርና አባላት ከሀምሌ 29 እስከ ነሀሴ 1 2007 ዓ.ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ነው መከፋፈሉ ሊከስት የቻለው፡፡ የምዕራብ ጎጃም የብአዴን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሀብታሙ፣ የዞኑ ምክትል ከንቲባ አስፋው ገበየሁና የወረዳው የብአዴን ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አላምር ተሻለ የተባሉ የህወሓት አገልጋይ የመሩት በዱላ ቀረሽ ስድድብ፣ እርስበርስ መወነጃጀልና የተደበቀ ገመናን በመነስነስ ታጅቦ ለሦስት ቀናት የዘለቀው ስብሰባ ከመነሻው በዋናነት ለውይይት ያቀረባቸው አርበኞች ግንቦት 7 ባወጀው ጦርነት ላይ ተመስርቶ በሽበርተኝነት ላይ የሚያጠነጥን አንድ ሃሳብና የብአዴንን 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበርን የሚመለከት ሌላ ተጨማሪ እርዕስ ያነገበ ሁለት አብይ አጀንዳዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ስብሰባው የታቀደለትን አቅጣጫ ስቶ ፈር በመልቀቅ አባላትና የበታች የብአዴን አመራሮች ከአንድ ላይ በማበር በበላይ አመራሮቻቸው ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያነሱ የበላይ አመራሮች ደግሞ በፌደራል መንግስቱ በሚገኙ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ላይ ጣታቸውን ቀስረዋል፡

እየተቃወሙ ለመኖር…!

የአርበኞች ግንቦት 7 ቃልን ወደ ተግባር የማሸጋገር እንቅስቅሴ ያሸበረው ወያኔን ብቻ አለመሆኑን ከተቃውሞው ጎራ ከሚሰማው የተቀዋሚ ተቀዋሚዎች ጩኸት እያየን ነው፡፡ ርጥቡ ሬሳ ደረቅ ያስነሳ አንዲሉ ይህ ሰሞነኛ ጩኸት የተረሳ እንዲታወስ የተተወ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኖ የአንዳንዶቹ ጯሂዎች የትናንት ማንነት ድብቅ ዓላማና ፍላጎት ጭምር ጸሀይ እንዲሞቀው እየተደረገ ነው፡፡ የማለባባስ አጉል ባህላችንን ተራምደው የይሉኝታ ገመዳችንን በጥሰው ስም እየጠቀሱ መረጃና ማስረጃ እያጠቀሱ አካፋን አካፋ ለማለት ለደፈሩ ወገኖቼ ያለኝን አክብሮት እገልጻለሁ፡፡ እያለባበስን አርባ አመት አልቅሰናልና በቃ ማለት ይኖርብናል፡፡The Patriotic Ginbot 7 attacks factors
አደባባይ ወጥተው የሚጮኹትም ሆኑ ከኋላ ሆነው የሚገፉት የየግል ፍላጎታቸውም ሆነ አንድ የሚያደርጋቸው ምክንያት ምንነትና አንዴትነት በተለያዩ ሰዎች ተጽፋል፡፡ እውነት ናቸውና መስማማቴን እየገለጽሁ ያልተገለጸ የመሰለኝን ልጨምር፡
ስማቸው ብዙ ነው (ፖለቲከኛ ፣ጋዜጠኛ፣ነጻ ማህበር፣ወዘተ) መገኛቸው ሀገር ውስጥም ውጪም ነው፤ዓላማቸው ቢችሉ ምን-ይልክ ቤተ መንግሥት መታየት ካልሆነም በተቀዋሚነት ካባ አንድም ክብር ሁለትም ብር እያገኙ መኖር ነው፡፡ ተባብሮ መስራት አይሆንላቸውም፡ እነርሱ የሚመሩት ወይንም በቀጥታም ሆነ በተዘዋወዋሪ የሚቆጣጠሩት ካልሆነ በስተቀር ማናቸውም ትግል (ሰላማዊውም የጠብ-መንጃውም) አንድ ርምጃ ሲራመድ ማየት አይፈልጉም፡፡
ሲያልሙት የኖሩትን ሥልጣን ለማግኘት የሚቻለው ደግሞ አንድም በምርጫ አንድም በጡንቻ ነው፡፡እነርሱ በሁለቱም መንገድ ለመሄድ አይችሉም፡፡(አንዳንዶቹ ሁሉን ሞክረው የከሸፈባቸው ናቸው፡፡) የምርጫው ነገር እንኳን ለእነርሱ ፓርቲ መስርተው በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው መቀመጫቸውን ሀገር ቤት አድርገው ለሚፍጨረጨሩትም አልተሳካም፡፡ ሀገር ቤት በሚገኙ ተቀዋሚዎች ተከልለው ያደረጉት ሙከራም አልተሳካም፡፡ ( የኢትዮጵያ ዴሞክራሲዊ ኃይሎች ህብረት ይጠቀሳል) የጡንቻውን መንገድ ቢያልሙትም አልሆነላቸውም፤ አይሆንላቸውም፡፡ ከሌሎች ጋር ተባብረው በተቀዋሚነት ተከብረው ለመኖር፤ ከተቻለም ተከልለውም ቢሆን ወደ ምኒልክ ቤተ መንግሥት ለመድረስ መከጀላቸው ባይቀርም መሪነቱን እነርሱ ካልያዙት ወይንም እንቅስቃሴው በቀዳሚነት የእነርሱን ዓላማና ፍላጎት የሚያሳካ ካልሆነ በጅ አይሉምና፡ በዚህም መንገድ ስንዝር መራመድ አልቻሉም፤አይችሉምም፡፡
ስለሆነም ያላቸው ምርጫ ላለፉት ሀያ አመታት ሲተገብሩትም ያየነው ተቀዋሚ እየተባሉ መኖር ነውና በሰላማዊ ትግል በተአምር፣ ወይንም በተቃራኒው መንገድ በጦር የወያኔ ሥልጣን ቢቀየር ይህን ስለማያገኙ ጠንከር ያለ እንቅስቃሴ ሲጀመር ፈጥነው ይዘምቱበታል፡መገንባቱን ሳይሆን ማፍረሱን፣ ማቀራረቡን ሳይሆን ማለያየቱን፤ መደገፉን ሳይሆን ማደናቀፉን የተካኑበት ናቸውና እስካሁን በአብዛኛው ተሳክቶላቸዋል፡፡ ዛሬ ግን ተነቅቶባቸዋልና ድብቅ ማንነታቸውን ያጋልጡ፣ ቀሪ ህይወታቸውን ያበላሹ ለልጆቻቸው መጥፎ ስም ያቆዩ እንደሁ አንጂ የሚሳካላቸው አይመስለኝም፡፡
ፊሺካው ተነፍቷል ጦርነቱ ተጀምሯል በተባለበት ማግስት በፍጥነት ተጠራርተው ከጀመሩት ጫጫታ ውስጥ አንዳችም መፍትሄ ጠቋሚ ሀሳብ አለመኖሩ ከመነሻው በተቃውሞው ሰፈር ይገኙ እንጂ ለውጥ ናፋቂ ሳይሆኑ ወሬ አሟሟቂ፤ የተግባር ሳይሆን የምላስና የብዕር ታጋዮች መሆናቸውን የመሰከረ ነው፡፡ ትናትም ሆነ ዛሬ ሰላማዊውንም ሆነ የጠብ-መንጃውን ትግል የሚቃወሙት ተቀዋሚ እየተባሉ ሆነው ሳይሆን እያስመሰሉ፣ እየታገሉ ሳይሆን እያውደለደሉ ክብርም ብርም የሚያገኙበት ሜዳ እንዳያጡ በመስጋት ነው፡፡ ግን ለምን? እነርሱ በተቃዋሚነት እንዲኖሩ የወያኔ እድሜ መርዘም አለበት? የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንባ ገነን አገዛዝ ውስጥ መኖር አለበት ?ከእነርሱ ፍላጎትና ከሀገር ነጻነት የቱ ይበልጣል?፤የቱ ይቀድማል፡? በእውነቱ አሳፋሪም በታሪክና በትውልድ የሚያስጠይቅም እኩይ ተግባር ነው፡፡
ይህ አድራጎት ዛሬ የተጀመረ አይደለም፤ እንደውም ከአንዳንዶቹ ጋር አብሮ ያረጀ ነው፤ ትንሽ የቅርብ ግዜ ማሳያዎችን አንመልከት፡
ማሳያ አንድ፤ በ1992 ዓም ኢዴፓ የሚባል ፓርቲ ተመስርቶ በአጭር ግዜ ሰፊ እንቅስቃሴ አደረገና እውቅና አገኘ፤ በዚህ መልኩ እየገነነ ከቀጠለ በግልም ሆነ በድርጅት እስከመኖራቸውም እንዳይረሱ የሰጉት እነዚህ የወያኔም የተቀዋሚውም ተቀዋሚዎች የለመዱትንና የተካኑበትን የማደናቀፍ ዘመቻቸውን ከፈቱበት፤ የፓርቲው አመራሮች ቢቸግራቸው በእነዚህ ሰዎች በተወጠነውና በምድረ አሜሪካ በተዘጋጀ ጉባኤ ተካፋይ ሆነው የኢዴኃህ አባል ሆኑ፡፡ ሊቀመንበሩ ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ የህብረቱ ዋና ጸኃፊ ለመሆን ቢበቁም ከመነሻው የተገባው በእምነት ሳይሆን የሰዎቹን አፍራሽ ዘመቻ በመፍራት ነበርና ብዙም ሳይቆይ ፓርቲው ከህብረቱ ወጣ፣ መኢአድ ለጉባኤ የላካቸው አባላቱ ሀገር ቤት ሳይመለሱ ነበር ጉባኤው በእነዚህ ሰዎች ሴራ መጠለፉን ገልጾ የጉባኤውን ሂደት በመቃወም ጥያቄ አቅርቦ፤ጥያቄው ካልተመለሰ እንደማይቀጥል ያስታወቀው፡፡ ኢዴኃህም የቡና ውሀ ሆነ፡፡ (በምርጫ 97 የሰሩትም የሚረሳ አይደለም፡፡)
ማሳያ ሁለት፤ ቅንጅት ሲመሰረት መሪነቱን እንያዝ እንዳይሉ ከመስፈርቱ አንዱ በሀገር ቤት ያሉ የሚል በመሆኑ፣ እነርሱ ደግሞ አብዛኛዎቹ ከሀገር ውጪ ስለሚኖሩና ሀገር ቤት ፓርቲ ስለሌላቸው አልተቻላቸውም፤ በእጅ አዙር አንዳይቆጣ ጠሩት ከቅንጅት የወቅቱ ጥንካሬ አንጻር ለዛ የሚያበቃ አቅም አልነበራቸውም፡፡ እናም በሚያውቁት በለመዱትና በተካኑበት ስልትና መንገድ ብዙ ዘመቱበት፤ ወዳጅ መስለው በመቅረብ መጥፎ እየመከሩ አቅጣጫ ለማሳት፣ በአመራሩ መካከል መጠራጠር ለመፍጠር ብሎም ቅንጅትን ከመረጠው ሕዝብ ለማጣላት ከውጪም በሀገር ውስጥም በመልእክተኞቻቸው በኩል ብዙ ሰርተዋል፡፡ የቅንጅት አመራሮች ለፓርላማ ሳይሆን ለወህኒ ሲዳረጉም ተደስተዋል፡፡
ማሳያ ሶስት፤ የቅንጅት አመራሮች ከእስር ከወጡ በኋላ የፈጠሩት አለመግባባት እስከ መለያየት እንዲያደርሳቸው ከሁለቱም ወገን ደጋፊ መስለው በመሰለፍ የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል አይነት የተጫወቱት አፍራሽ ሚና ቀላል አይደለም፡፡ ይህን ለማረጋገጥ በወቅቱ በዌብ ሳይቶች በጋዜጦችና በማህበራዊ ድረ-ገጾች ወዘተ ላይ የተጻፉትን ማየት በየፓልቶኩ በያራዲዮው የተነገሩትን ማደመጥ በቂ ነው፡፡
ማሳያ አራት፤ የቅንጅት ከፊሉ ወገን ተሰባስቦ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ሊቀመንበሩ አድርጎ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ የተሰኘ ፓርቲ መስርቶ በአጭር ግዜ በሀገር ውስጥም ሆነ አውሮፓና አሜሪካ ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የተበለጥን ሰይጣናዊ ስሜታቸው አገርሽቶ የከፈቱት ዘመቻም የሚረሳ አይመስለኝም፡፡(በአብዛኛው የሚዘምቱት ሀገራዊ ድርጅት ላይ ነው)
አንድነት የቅንጅት ወራሽ መሆኑና ( ቅንጅት የሚለው ስምና ሁለት ጣት ምልክት ወያኔዎችን ያባንናቸዋል)ከጅምሩ ያገኘው ተቀባይነት ያሰጋው ወያኔ ወ/ት ብርቱካንን ዳግም ሲያስር ለእነዚህ ሰዎች ፌሽታ ነበር፡፡አጋጣሚውን በመጠቀምም ቀሪዎቹን አመራሮች ከቅርብም ከሩቅም ወዳጅ መስለው በመቅረብ በምክርም በገንዘብም በሌላ ሌላውም ከወዲያ ወዲህ እያላጉ የት ይደርሳል የተባለውን አንድነት ሽባ አደረጉት፡፡ የእነርሱም የወያኔም ሴራ ተደማምሮ አንድነት አምስት አመት ሙሉ ታሞ በምርጫ 2007 ዋዜማ ግብአተ መሬቱ ተፈጸመ፡፡ እናቃብራችሁ አንኳን አላሉም፡፡
ማሳያ አምስት፤ ሰማያዊ – ይህኛውም ፓርቲ በ2004 ዓም ተመስርቶ በአጭር ግዜ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ለስድስት አመት የተዘጋን የሰላማዊ ሰልፍ ክልከላ በር አስከፈተ ተብሎ ስሙ ሲናኝ የሌላው መግነን የእኛን መኮስመን ያስከትላል የሚል ከይሲ አስተሳሰብ ያላቸው እነዚህ ወገኖች ዘመቻ የጀመሩት ከመቅጽበት ነው፡፡
ይሉት ቢያጡ ሰበብ ቢቸግራቸው ከሌሎች ጋር ተባብሮ መስራት አለበት ብቻውን የትም አይደርስም አሉ፡፡ አልተሳካላቸውም እንጂ ይህን ሰበብ አድርገው በፓርቲው ውስጥ ክፍፍል እስከመፍጠር ደርሰውም እንደነበር ይታወቃል፡፡ሌላም ሌላም መጥቀስ ይቻላል፡፡አንድ ፓርቲ ጠንክሮ እንዳይወጣ ወይንም ፓርቲዎች ተባብረው በግንባርም ይሁን በውህደት ጠንክረው እንዳይታገሉ ካደረጉዋቸው ምክንያቶች አንዱ የእነዚህ ወገኖች ሴራ ነው፡፤
እነሆ አሁን ደግሞ የተለመደውንና መታወቂያቸው የሆነውን አፍራሽ ተግባር ጀመሩ፡፡ የኢሳይያስ ማንነትና የሻዕቢያ ምንነት የታያቸው ዛሬ ነው ? ጅብን ሲወጉ በአህያ ተከልሎ እንደሚባለው ይህ ሰበብ ነው፡፡ ዋና አላማው ኢሳይያስንና ሻዕቢያን ከለላ አድርጎ በነጻነት ትግሉና ታጋዮቹ ላይ መዝመት ነው፡፡
ተቃውሞአቸው ምንድን ነው፡፡
የሚያነሱት ነገር ለክርክር እንዳይቀርብ ለመለስ ምትም አንዳይመች ተቃውሞአቸው ስልታዊ መንገዳቸው የጎንዮሽ ነው፡፡የሚደግፉትም ሆነ የሚቃወሙት ነገር በግልጽ አይታወቅም፤ ዛሬ ያመሰገኑትን ነገ ይኮንኑታል፤ባከበሩ ማግስት ያዋርዳሉ፤ የእነርሱ የሆነ ሁሉ ቅዱስ በተቃራኒ የቆመ ወይም ለእነርሱ ያልተመቸ ሁሉ ርኩስ ነው፡፡ እነርሱ ሞክረውት አላስኬድ ባላቸው መንገድ ሌሎች መሄድ ከቻሉ በቅናት ያራሉ፡ እነርሱ ሊወዳጁት ያልቻሉትን ሰው ወይንም ድርጅት ሌሎች መወዳጀት ከቻሉ የውግዘት ናዳ ያወረዳሉ፤ እነርሱ ሞክረውት ያቃታቸውን ሌሎች ለማሳካት ከጀመሩ የማጥላላት ጥሩንባ ይነፋሉ፤ በታላቁ መጽኃፍ ትንቢተ ኢሳይያስ ም፣48 ቁ.22 ላይ “ክፉዎች ሰላም የላቸውም” ተብሎ እንደተጻፈው በክፋታቸው ለራሳቸው ሰላም አጥተው ሌላውንም ሰላም ያሳጣሉ፡፡
የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ተብሎ አንዳይተው፣ ዓላማችን ላሉት ስኬት አስበው ወቅት ጠብቀው የሚሰሩ መሆናቸውን አይተናል እያየንም ነው ፡፡ የተለመደ ተግባራቸው ነው ተብሎ ተንቆ አንዳይተው ብእራቸውም ሆነ ምላሳቸው የሚረጨው መርዝ ለትግሉ ውጤታማነት ሆነ ከድል በኋላ ለሚፈለገው መረጋጋት ብሎም ለኢትዮጵያውን አንድነት ጠንቅ ነው፡፡ መፍትሄው አላማችሁ ገብቶናል በቃችሁ ማለት መቻል ነው፡፡ይሄ ካልበገራቸውም ማንነታቸውን ጸሀይ ማሞቅ፡፡

በአዳማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ የኦሮሞ ዲያስፖራ አባላት የመንግስት ባለስልጣናትን በጥያቄ አጨናነቁ

Opdo
(ራዲዮ ዳንዲ ሃቃ ማክሰኞ ሐምሌ 5/ 2007) ስብሰባው ከአርባ ሰባት ሃገራት የተሰባሰቡ የኦሮሞ የዲያስፖራ አባላትን የአርባ ሰባቱ ሃገሮች ዲፕሎማቶች በተገኙበት ተካሂዷል ። መንግስት የኦሮሞ ዲያስፖራ ሳምንት ብሎ የሰየመውን ሳምንት በማስመልከት: ከመላው አለም ያሰባሰባቸውን የኦሮሚያ ዲያስፖራ አባላት: በሚሊኒየም አዳራሽ ጠቅላይ ሚስትሩ በተገኙበት ደማቅ የአቀባበል ስነ ስርዓት ካደረገላቸውና : ለሶስት ቀናት ያክል ሃገሪቷን ካስጎበኛቸው በኃላ : በአዳማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ በመሰብሰብ : የተለመደ ፕሮፓጋንዳውን ለመንዛት ቢሞክርም: ከኦሮሚያ የዲያስፖራ አባላት ፍፁም ያልጠበቀው :የጥያቄ ውርጅብኝ ዘንቦበታል ። ስብስባውን የመሩት አቶ አባዱላ ገመዳ አቶ ሙክታር ኸድር እና ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ሲሆኑ : ከኦሮሞ ዲያስፖራ አባላት የተነሱት ጥያቄዎች በአራት ነገሮች ላይ ያጠነጠኑ እንደነበሩና እነሱ :– 1)የሙስሊሙ ህብረተሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴን የፍርድ ሂደት በተመለከተ 2) የጋዜጠኞችን መታሰር ጉዳይ በተመለከተ 3) የኦሮሞ ተማሪዎችና ወጣቶች መታሰርን በተመለከተና 4) የመሬት ማስተር ፕላኑንና በተመለከተና በማስተር ፕላን ሰበብ ህዝብ ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ እንደነበር ምንጮቻችን አያይዘው ገልፀዋል። በተለይም የሙስሊሙ ህብረተሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጉዳይ ከዲያስፖራው አባላት ሲነሳ : የተሳታፊዎቹ ስሜት ፍፁም ልዩ እንደነበርና: እያንዳንዱ እነሱን በሚመለከት የሚነሳ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር : ከኃላው ከፍተኛ ጭብጨባ ይከተለው እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል ።