Monday, September 21, 2015

የኦጋዴን ነፃነት ግንባር 2 ከፍተኛ አመራሮች በአልሸባብ አንገታቸው ተቀልቶ ተገደሉ * ግንባሩ የኢትዮጵያ መንግስት እጅ አለበት ሲል ከሰሰ

Zehabesha News
(ዘ-ሐበሻ) የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ሁለት ከፍተኛ አመራሮቼ ከሶማሊያ ባይዶዋ ወደ ኦጋዴን ሲጓዙ በአልሸባብ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው ተገደሉብኝ ሲል ከሰሰ። ለዚህም ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ነው ብሏል::
የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ከቅርብ ወራት ወዲህ በጠቅላላው ከአስር የማያንሱ አባሎቼ ሶማሊያ ውስጥ በአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ አንገታቸው ታርዶ ተገድለውብኛል ብሏል ።
እንደ ግንባሩ ክስ ከሆእ የኢትዮዽያ መንግስት የደህንነት ሰራተኞች በስውር ከአልሸባብ ንዑስ ቡድን ጋር በመገናኘት ግድያው እንዲፈፀም አሲረዋል።
በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ አገዛዝ እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ ባይሰጥም ከዚህ ቀደም መንግስት የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ያለው አሸባሪ ድርጅት ነው ሲል መክሰሱ ይታወሳል:: አማጺው ቡድንም ሆነ መንግስት እርስ በራሳቸው ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው እየተባባሉ መካሰሳቸው ለብዙዎች ግርምታን ፈጥሯ

Sunday, September 13, 2015

የዴምህት ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስግዶም ለምን ከዱ?

(ECADF) – የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ዴምህት) ከአርበኞች ግንቦት7፣ ከአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ እና ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ጋር ጥምረት መመስረቱን ባወጀበት ማግስት የጥምረቱ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙትና ዴምህትን ለዓመታት ሲመሩ የኖሩት አቶ ሞላ አስግዶም መክዳታቸው ታውቋል።Former TPDM chairman Mola Asgedom
ኢሳት በአጭር ሰበር ዜና ዘገባው እንደገለጸው ከሆነ አቶ ሞላ አስግዶም ድርጅታቸው ጥምረት እንዲመሰርት ፍላጎት አልነበራቸውም። ይሁንና አብዛኛው የዴህምህት አመራሮች ጥምረቱን በመፈለጋቸው ምክንያት ጥምረቱ እውን ሊሆን ችሏል።
ፋሲል የኔዓለም (የኢሳት ጋዜጥኛ) ወደ ኤርትራ ተጉዞ በነበረበት ወቅት ከአቶ ሞላ አስግዶም ጋር የመወያየት እድል አግኝቶ ነበር። የአቶ ሞላ አስግዶም መክዳት ከተሰማ በኋላ ፋሲል እንዲህ በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል፣
“የደሚህቱ ሞላ አስገዶም መክዳቱን ስሰማ በእጅጉ ተገርሜአለሁ። ከቀናት በፊት ሞላ ፣ ሰው አክባሪ፣ ተግባቢና አገሩን የሚወድ ሰው መሆኑን ጽፌ ነበር። ኤርትራ በነበርኩበት ጊዜ ደጋግሜ አግኝቸዋለሁ ፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ጊዜ ወስደን ተነጋግረናል። እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ስለሞላ የነበረኝ አመለካከት ቀደም ብዬ የገለጽኩት ነው።

ቴዲ አፍሮ – ለእውነት፣ ለፍትህና ለፍቅር መቆም የሚያስከፍለውን ዋጋ እየከፈለ ያለ ብርቱ ሰው


የቴዲ አፍሮ ምኞቶች ዘረኝነትና ጥላቻ በመንግሥት ደረጃ በሚሰበክበት አገር፣ ድንቁርና እጅግ በተጫናቸው የወያኔ ቱባ ባለሥልጣናት ሕዝብ በሚዘለፍበት፣ ታሪክ ተጣሞ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪን የሕብረተሰብ ክፍል በሌላው ላይ ለማነሳሳት ሌት ተቀን የሚደክሙና ጉርጓድ የሚምሱ ቡድኖችና ግለሰቦች ባሉበት አገር፣ ፍርሃትና ጥርጣሬ በነገሱበትና አፈና በበረታበት እንደ ኢትዮጵያ ባለ አገር እንደ ቴውድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ‹ ያሉ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በማሕበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ሚና በዘፈን ሕዝብን ከማዝናናት እጅግ ያለፈ ነው፡፡
የቴዲ ዘፈኖች ታሪክን ለሚክዱና ለሚያጣምሙ ማስተማሪያዎች ናቸው፡፡

Sunday, September 6, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ሰነዘሩ

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የውስጥ አርበኞች በህወሓት አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ከባድ ውጊያ አድርገው ከፍተኛ ጉዳት አደረሱ፡፡The Patriotic Ginbot 7 attacks factors
የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች ህወሓት “ክልል አንድ” እያለ በሚጠራው በጎንደር-ወልቃይት ደጃች ሜዳ ወረዳ አቤራ ቀበሌ ስልኪ ዳግባ በተባለው ቦታ ነሃሴ 23 2007 ዓ.ም በህወሓት መከላከያ ኃይል ላይ ድንገተኛ የተኩስ ውርጅብኝ በመክፈት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ወታደሮችን ገድለውና አቁስለው ድል ተቀዳጅተዋል፡፡
በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞችና በህወሓት የመከላከያ ሰራዊት መካከል የተካሄደው ድንገተኛ የሆነ ከባድ ፍልሚያ እኩለ ቀን ላይ ከ6፡30 ጀምሮ እስከ 7፡30 ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ሲሆን ምሳ በመመገብ ላይ እያለ ባልገመተው ሁኔታና ባለሰበው አሳቻ ሰዓት ድንገተኛ ተኩስ ተከፍቶበት የእሳት ዝናብ በላዩ ላይ የወረደበት የህወሓት ሰራዊት አብዛኛው ተበታትኖ ከአካባቢው የሸሸ ሲሆን የአፀፋ ተኩስ ከፍቶ ለአንድ ሰዓት ለመከላከል የሞከረው ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል፡፡

Thursday, September 3, 2015

ከዊሃ እስከ ኦምሃጀር – አንድ ሰሞን ከአርበኞች ጋር (ኤፍሬም ማዴቦ)

ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። አዎ! ማተቡን ላጠበቀና በአምላኩ ለሚታመን በእርግጥ ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። ሰዉ ነኝና እንደ ፈጣሪ ቃሌ ሁሉ እዉነት ነዉ ብዬ አለተፈጥሮዬ አላብጥም። ግን ሰዉ ብሆንም ፈጣሪዬን የምፈራ ሰዉ ነኝና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስል ልቦናዬ እያወቀዉ እንደነ ጋሼ እንደልቡ ዉሸት ደርድሬ ለአንባቢ የማቀርብበት ምንም ምክንያት የለም። ከዚህ ቀጥሎ የማስነብባችሁ እያንዳንዱ ቃል እንደ ዳያስፖራ ተረተኞች የምተርተዉ ‘ሰዉ ሰዉ’ የማይሸተት ተረት ሳይሆን ኢትዮጵያ ድንበር ላይ በየግንባሩ የተሰለፉትንና በስልጠና ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አርበኞች ስጎበኝ በአይኔ ያየሁትንና በጆሮዬ የሰማሁትን ቃል ነዉ።Ephrem Madebo with Patriotic Ginbot 7 fighters
ቨርጂኒያ ወደሚገኘዉ “Dulles” አዉሮፕላን ማረፊያ የሄድኩት ከልጄ ጋር ነበር። ከቤቴ Dulles የግማሽ ሰዐት መንገድ ነዉ። ያቺን ግማሽ ሰዐትና አዉሮፕላን ማረፊያ ደርሼ ሻንጣዬን እስካስጭን ድረስ አይኔ እያንዳንዷን ደቂቃ ከልጄ ከቢኒያም አልተለየም። መለየቱን ስላልወደደዉ ልቤ ደንግጧል። ከወያኔ ጋር ለመፋለም በረሃ የሚጓዘዉ ኤፍሬም ከአንድ ልጁ መለየት አቃተዉ። ምነዉ ብዬ እራሴን ጠየኩት- እኔዉ መልሼ ምንም አልኩ። ልጄን አቀፍኩት፤ አሁንም ደግሜ ደጋግሜ አቀፍኩት። እምባ ፊቴን ሞላዉ። ቀና ብሎ ተመለከተኝና ሲከፋዉ ታየኝ። ሁለተኛ ዙር እምባ ፊቴን ሞላዉ። “Son I don’t want to do this, but I have to do it” አልኩ በሁለት እጄ አቅፌ እንደያዝኩት። ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ አባት ሆይ ፈቃድህ ከሆነች ይቺ ጽዋ ከኔ ትለፍ ብሎ የጸለየዉ ፀሎት ትዝ አለኝ። እኛ ሰዎች የዳንነዉ ይህ ፀሎት ባለመመለሱ መሆኑ ትዉስ ሲለኝ ልቤ በሀሳቡ ጸና። አባባ Come on . . . be strong. I promise I will be the son that you raised- you will be proud of me” አለኝ ቢኒያም በዚያ 17 አመት ሙሉ በማዉቀዉ ቆንጆ ድምጹ። የተናገራቸዉ ቃላት ዉስጤ ገብተዉ ኃይል ሲሆኑኝ ተሰማኝ። ጠነከርኩ። ተሰናብቼዉ ወደኋላ እያየሁት ወደ ዉስጥ ገባሁ። ወደ ፍተሻዉ ቦታ ስሄድ ልቤን ከፍተኛ የመለየት ኃዘን እንደ ግግር በረዶ ሲጫነዉ ተሰማኝ፤ መሸከም አቃተኝና እንደ ህፃን ልጅ እያነባሁ ፍተሻዉ መስመር ላይ ገብቼ ወረፋ ያዝኩ።

ሰበር: የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከጠቅላላ ጉባኤው ሲመለሱ ተደበደቡ

118
‹‹የደበደበኝና የዘረፈኝ ሰው ተለቆ እኔ ታስሬያለሁ›› አቶ ጌትነት በሱፍቃድ
በወላይታ ዞን ቦሎቶሶሬ ወረዳ አረካ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ጌትነት በሱፍቃድ ተደብድበው ንብረቶቻቸውን መዘረፋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በምርጫው ወቅት ቅስቀሳ ላይ እያሉም በገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ተመሳሳይ ወንጀል ተፈፅሞባቸው እንደነበር የገለፁት አቶ ጌትነት ‹‹በምርጫው ወቅት ቅስቀሳ ላይ እያለሁ በካድሬዎች ተደብድቤ ንብረቴን ተቀምቻለሁ፡፡ ሌሎች የትግል ጓደኞቼም ተመሳሳይ ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ሆኖም ከፖሊስ ጣቢያ ጀምሮ እስከ ከንቲባው ፅ/ቤት ድረስ በመሄድ አቤቱታ ብናቀርብም የሚሰማን አላገኘንም፡፡›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በደቡብ ኦሞ የሰፈሩ የሰራዊት አባላት መጥፋታቸውን ተከትሎ ነዋሪዎች እየታሰሩ ነው

Ethiopian soldiers stand guard near boxes of weapons found hidden under a building in Mogadishu May 9, 2007. A large cache of weapons, believed to have been hidden by the Islamists, were discovered in Mogadishu by the Ethiopian forces and their Somali allies on Tuesday. REUTERS/Shabelle Media (SOMALIA)
በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በሃመር ብሄረሰብና በዞኑ ፖሊስ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ተከትሎ በአካባቢው የሰፈረው የአንድ ሻለቃ ጦር አባላት በርካቶቹ ኮብልለው በመጥፋታቸው ፣ ለወታደሮቹ መጥፋት ምክንያት ናቸው የተባሉ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። በመከላከያ ሰራዊቱ አባላት መካካል የሚታየው አለመተማማንና ልዩነት በመስፋቱ እርስ በርስ እስከመጋጨት ደርሰዋል።
ከወር በፊት በሃመር ወረዳ በተፈጠረው ግጭት በርካታ የወረዳው ነዋሪዎችና ፖሊስ አባላት ተገድለዋል። ግጭቱን ለማብረድ አንድ ሻለቃ ጦር በተለያዩ አካባቢዎች እንዲሰፍር ተደርጓል። ይሁን እንጅ በወታደሮቹ መካካል መተማመን በመጥፋቱ ከመካከላቸው በርካታ ወታደሮች በመኮብለላቸውና የደረሱበት ባለመታወቁ፣ አመራሮቹ ወታደሮች እንዲጠፉ አድርገዋል ያሉዋቸውን የሞተር አሽከርካሪዎች ይዘው አስረዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት አሽከርካሪዎች መካከል ጌታ ጫን ያለው ወርቁ፣ አሚኑ ትኩና አሚኑ ሃሰን ይገኙበታል። አሽከርካሪዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበው፣ ከ15 ቀናት የእስር ጊዜ በሁዋላ በዋስ ሲፈቱ፣ ወታደሮቹን በማሸሹ ሂደት ተሳትፈዋል የተባሉ በርካታ ወታደሮች በአርካሻ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ።