አንዳንዶቻችን ኢህአዴግ ያጠፋውን ጥፋት ለትግሬና ለትግራይ ጠቅልላችሁ ለምን እንደምታስረክቡ አይገባኝም፡፡አንዳንዶቻችሁማ ብሶባችኃል ትንሽ ዕድልና ብዙ ሃይል ብታገኙ መታወቂያ እያያችሁ ይሄን ህዝብ ብትረፈርፉት ደስታችሁ መሆኑን ትሰብካላችሁ፡፡ወንድሞቼ ኢህአዴግ ከመላው ብሄረሰቦች የተውጣጡ እንከፎች የመሰረቱት ማህበር እንጂ ትግሬና ትግሬያዊያን የፈጠሩት ክስተት አይደለም፡፡
የአማራ መሬት ምርጥ ሰዎችን እንደማፍራቱ አዲሱ ለገሰ፣ታምራት ላይኔ፣አለምነው መኮነንን የመሰሉ በሰው ደም ሻወር የሚያምራቸው ሰዎችን አፍርቷል፡፡የኦሮሞ ህዝብ ታሪክን በብርሃን ያደመቁ ጀግኖችን እንደመውለዱ አባዱላ ገመዳ፣ሙክታር ከድር፣ግርማ ብሩን የመሰሉ አስረፍራፊዎችን ለኢህአዴግ አዋጥቷል፡፡ጉራጌ ካሱ ኢላላን፣ሲዳማ ሽፈራው ሽጉጤን፣ወላይታ ሃይለማሪያምን አሳድጓል፡፡ሶማሌ ፣ጋምቤላ ፣ሀረር ውስጥ ለተፈጠሩ እልቂቶች ምላጭ ሳቢዎቹ ፣አሰቃዮቹ ራሳቸው በአከባቢው ተወልደው ያደጉ ሳዲስቶች አልነበሩም?
Thursday, January 29, 2015
በኢትዮጵያ መንግስት በጥብቅ የሚፈለጉ 3 አርቲስቶች
እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳብን በነፃነት ያለመግለጽ መብት አለመከበሩ ያጠቃው ጋዜጠኞችን ብቻ አይደለም። አርቲስቶችም ጋዜጠኞች ከሚከፍሉት መስዋእትነት ያልተናነሰ ትግል እያደረጉ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለመታደል ሆኖ የሃሳብን የመግለጽ ነጻነት በመገደቡ ዛሬ እንደ ታላቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙና ተመስገን ደሳለን ያሉ ጋዜጠኞች ያልሆነ ክስ ተልጠፎባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ። የእነዚ ታላላቅ ጋዜጠኞች ‘ወንጀል’ መንግስት እንደሚለው ሳይሆን የሕዝብን በደልና ብሶት ማሰማታቸው ብቻ ነው።
መታረም የሚገባዉ ማነዉ? ርዕዮት አለሙ ከቃሊቲ እስር ቤት
በግል የህትመት ዉጤቶች አማካኝነት በሀገሬ ዉስጥ የምመለከታቸዉን ችግሮች ለህዝብ ማቅረብና እንደዜጋም መፍትሔ ይሆናሉ ብዬ የማስባቸዉን ሀሳቦች መጠቆም ከጀመርኩ አምስት አመታት አለፉ፡፡ የመጀመሪያ ፅሑፌን ያዘጋጀሁት ” “ስህተቶችን” ለማረም የተፈፀሙ ስህተቶችና የስህተት ማረሚያ እርምጃዎች” በሚል ርዕስ እንደነበረ አስታዉሳለሁ፡፡ በዚህም ፅሑፍ የፕሬስ፣የፖለቲካፓርቲዎች ምዝገባና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የተመለከቱ አዋጆች የወጡበት ምክንያትና እንደሀገር የሚያሳድሩትን ተፅእኖ ለመዳሰስ ብሎም ኢህአዴግ ከስህተቶቹ እንዲታረም ለመምከር ሞክሬያለሁ፡፡

Tuesday, January 27, 2015
በኖርዌይ ኦስሎ እንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በደማቅ ሁኔታ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
ቀን፡ 01/26/2015
በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በዛሬው እለት ሰኞ( January 26,2015) በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በኖርዌይ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በህብረት ሁነው ከ14፡00 _15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ አካሄዱ።
የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ የነበሩትንና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአረመኔው፣ ሰው በላ፣ ጨቋኙና በአንምባ ገነኑ የወያኔ ፋሺስታዊ ቡድን የአለም አቀፍ የሰባዊ መብትን ህግ በጣሰ መንገድ በሰኔ 2014 ታፍነው እስኳሁንም ድረስ ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም እንዲሁም የእንግሊዝ መንግስት አርበኛው የነጻነት ታጋዩ አንዳርጋቸው እየተፈጸመበት ያለውን ተፈጥሮአዊና ዲሞክራሲያዊ የመብት ጥሰት ተመልክቶ ከእስር ሊወጣበት የሚችልበትን አፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ ለማሳሰብ ነው።

Sunday, January 25, 2015
በኢትዮጵያ ውስጥ አገዛዙ የሚያካሂደው አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏል – ሸንጎ
ለአስቸኳይ ስርጭት

- አቶ አሥራት አብርሃም – የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ
- አቶ ሰለሞን ሥዩም – የአንድነት የ”ሚሊዮኖች ድምጽ” የኢዲቶሪያል ቦርድ አባል
- አቶ ስንታየሁ ቸኮል – የአዲስ አበባ የወጣቶች ክፍል ሃላፊ
- አቶ ነዋይ ገበየሁ – የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ም/ሃላፊ እንደሚገኙበት ለመረዳት ተችሏል።
Thursday, January 22, 2015
የሕሊና እስረኛዋ ርዕዮት ዓለሙ ልደት: ከርዕዮት በጎውን እንቅና !
ይድነቃቸው ከበደ
ዙርያን በመመልከት ካለንበት መጀመር ለምንም ነገር የተሻለ ነው፤ ከቤተሰብህ፣ከጓደኛ፣ከማህበረሰብ ራስን ለመረዳት እና ትርጉም ያለው ሥራ ለመስራት፣ በጎውን ለማድረግ ብንቀና ለስኬታችን ቀላል መንገድ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል “በጎውንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቀችሁ ማን ነው ? በማላት በጴጥ.መ.ምዕ 3ቁ 13 ላይ ተገልፆ ይገኛል ፡፡
1310 ቀን በእስር እያሣለፈች የምትገኘው፣የተወዳጇ የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ የልደት በዓል ፣እጅግ በጣም ደስ በሚል ሁኔታ በድምቀት ተከብሯአል፡፡ በልደት ቀኗ ተዋቂ ግለሰቦች፣የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት፣ጋዜጠኞች፣የማህበራዊ-ድረ ገፅ ዋንኛ አንቀሳቃሾች፣ ጓደኞቿ እና ቤተሰብ በመገኘት የበዓሉ ተካፋይ ለመሆን ችለዋል፡፡ በቦታው በመገኘት ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፣ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፣ኢ/ር ይልቃል ጌትነት እንዲሁም አቶ በላይ በፍቃዱ በተሰጣቸው አጭር ደቂቃ በመጠቀም ለርዮት መልካ ልደት ከመመኘት በላፈ ፣አስደማሚ ንንግር አድረገዋል፡፡

“ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም” – በኢትዮጵያ የመገናኛ-ብዙሃን ነጻነት ላይ የሚፈፀም የመብት ጥሰት (የሂውማን ራይትስ ዋች መግለጫ)
እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 2015 ዓ.ም. ማጠቃለያ
የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) እ.ኤ.አ. በ2010 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ 99.6 በመቶ የፓርላማ መቀመጫን ካሸነፈ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን እና መረጃ የማግኘት መብትን በመገደብ በግል መገናኛ-ብዙሃን ላይ እያሳደረ ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ አባብሶታል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ቢያንስ 60 ጋዜጠኞች ሃገር ለቀው የተሰደዱ ሲሆን ሌሎች 19 ጋዜጠኞች ደግሞ በእስር ላይ እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡ መንግስት በደርዘኖች የሚቆጠሩ ህትመቶችን ዘግቷል፤ እንዲሁም አብዛኛዎቹን የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ስርጭቶች በቁጥጥሩ ስር በማድረግ ኢትዮጵየዊያን የሀገር ውስጥ የፖለቲካ ጉዳዮችን በተመለከተ ነጻ መረጃ እና ትንታኔ የሚያገኙበትን እድል አጣቧል። በግንቦት 2007 በሚካሄደው ምርጫ መገናኛ-ብዙሃኑ ህዝቡን በወሳኝ ጉዳዮች ላይ በማስተማርም ሆነ መረጃ በመስጠት ረገድ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ ይችሉ ነበር፤ እንዲሁም የመከራከሪያ መድረክ በመሆን ሊያገለግሉ ይችሉ ነበር፤ ይሁን እንጂ መንግስት በሃገሪቱ ላለው ብቸኛ የበላይነት የግሉን መገናኛ-ብዙሃን እንደ ስጋት አድርጎ በመውሰድ የግሉን መገናኛ-ብዙሃን፣ ነጻ ጋዜተኝነትን እና ተቺ ትንታኔን ለማጥፋት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም የከፋ ውጤት አስከትሏል።
Tuesday, January 20, 2015
ካድሬዎች በየሜዳው የምርጫ ካርድ በግዳጅ እየሰጡ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ ከ2 ምርጫ በፊት በ0 የተሸነፈው የገዢው ስርዓት ባለፈው ምርጫ 96.6% አሸንፍኩ ማለቱን ተከትሎ ምርጫው መሳቂያ እንደሆነበት ብዙዎች ሲተቹበት የቆየ ጉዳይ ነው:: በባለፈው ዓመት ምርጫ ብዙ ሰው “ብንመርጥም ስለሚጭበረበር ግዜዬን አላጠፋም” በሚል ካርድ ያልወሰደ ሲሆን ዘንድሮ በግድ እንዲወስዱ እየተደረገ ነው::
የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ያነጋገሯቸው ምንጮች እንደሚሉት ስርዓቱ ያዘጋጃቸው ካድሬዎች በየቤቱ እየሄዱ የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ እያስገደዱ ሲሆን ከታክሲና አውቶቡስ መውረጃ ቦታዎች ላይ ወንበር እና ጠረጴዛ አስቀምጠው አላፊ አግዳሚውን በግድ የምርጫ ካርድ እንዲውስድ እያስገደዱት ነው::
Monday, January 19, 2015
(ይናገራል ፎቶ) ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ኤርትራ በርሃ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ታጋዮች ጋር
የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ኤርትራ ከሚገኙ የኢትዮጵያውያን ታጋዮች ጋር ቆይታ አድርጓል:: ጋዜጠኛው እዚያው የሚገኙትንና ብረት አንስተው አሁን ያለውን የሕወሓት አስተዳደር ለመጣል ከሚታገሉት ታጋዮች ጋር የተነሳውን ፎቶዎች ይናገራል ፎቶ ስንል አቅርበንላችኋል::
Saturday, January 17, 2015
የተመስገን ደሳለኝ ወንድም በ8 ፖሊሶች ተደበደበ * ጠ/ፍ/ቤት የተመስገንን ይግባኝ ውድቅ ኣድርጎ የ3 ዓመት ፍርዱን ኣጸና
(ዘሐበሻ) ጋዜጠኛ ተመስገን ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደርጎ የ3 ዓመት እስሩ እንዲፀናበት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰነ ። ከዚህ ፍርድ ቀደም ብሎ ወንድሞ ታሪኩ ደሳለኝ በ8 ፖሊሶች ክፉኛ ተደበደበ።
ታሪኩ ደሳለኝ በፌስቡክ ገጹ ጉዳዩን እንዲህ ገልጾታል:-
ለስምንት አንድን ሰው በደም እስኪታጠብ ድረስ በርግጫ፣ በጥፊና በሰደፍ መደብደብ፣ በእጁ ላይ የሚገኝውን ብርና መፃሀፍ መንጠቅ፣ ስልኩን መስበር…. ይህ ድርጊት በሌሊት አንድ ሰው ላይ በሌቦች የተፈፀመ ሳይሆን ትላንት ከረፋዱ በ 5 ሰዓት ላይ በዝዋይ እስር ቤት ግቢ ውስጥ በኔ ላይ የተፈፀመ ነው፤
ነገሩ እነዲህ ነው የሆነው፣ እንደልማዴ ዝዋይ የደረስኩት በማለዳ ነው፡፡ የያዝኩትን ስንቅ አስፈትሼ እንደጨረስኩ የሬዲዬ መገናኛ የያዘ መቶ አለቃ እንደሆነ የሚገልፅ ማዕረግ ያለው ወታደር እየገላመጠኝ “ለምን መጣህ?” አለኝ፤ “እዚህ የታሰረ ወንድም አለኝ እሱን ለመጠየቅ ነው” ስል መለስኩ፡፡ ቀጥ ብለህ ወጣ ተከተለ “አንተ ወንድምህን መጠየቅ አትችለም” ሲለኝ “ምክኒያቱ ይነገረኝ” ብዬ ብናገር ከጉዳይም አልቆጠረኝም “እሺ እ…ኔ ባልገባ እንኳን ያመጣሁት ምግብን አድርሱልኝ” ብል ስሚ አጣሁ፡፡ አንገቴን ደፍቼ ልወጣ ስል መቶ አለቃው በሬዲዬ እያወራ አንድቆም በእጁ ምልክት ሲሰጠኝ ልገባ ነው ብዬ ደሰ አለኝ፡፡

Thursday, January 15, 2015
ሰማያዊ ቲሸርት የለበሱ ወጣቶች ከስላሴ በዓል ላይ ተባረሩ
• ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ‹የፈራ ይመለስ› የሚል ቲሸርት አስለብሶ ሲበጠብጠኝ ሰንብቷል፡፡›› የየካ ክፍለ ከተማ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ
• ‹‹ገዥው ፓርቲ ጥላውን የማያምንበት ደረጃ ላይ ደርሷል!›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ

Monday, January 12, 2015
የአርቲስት አስቴር በዳኔና ሳሞራ ፍጥጫ በደደቢት በረሃ
…አርቲስት አስቴር በዳኔ ከተቀመጠችበት ወደፊት ወጥታ ማይኩን ስትጨብጥ ፍርኃት ቢጤ እንደወረራት ከመጀመሪያው ያስታውቃል፡፡ ‹‹በጣም ነው የሚያስፈራው፤›› በማለት የጀመረችውን አስተያየቷን የያዘችውን ማስታወሻ እያነበበች አስተያየት መስጠት ቀጠለች፡፡
‹‹ይህንን ዕድል ተመቻችቶልን በቴሌቪዥን ስናየው የኖርነው ታሪክ ለማየት ስለቻለን እጅግ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ በፊት የነበረኝ ያልተጨበጠ አመለካከት በመረጃ የተደገፈ ሆኗል፤›› በማለት ሐሳቧን ቀጠለች፡፡ ‹‹እውነትን መናገር እወዳለሁ፡፡ የሐሳብ ነፃነትም አለ፡፡ በእርግጥ የፖለቲካ ሰው አይደለሁም፤›› በማለት ታዳሚዎችን ፈገግ ያሰኘች ሲሆን፣ በሒደትም የፍርኃቷ መጠን እየቀነስ የመጣ ይመስላል፡፡
ወያኔ ኢትዮጵያን አፍርሶ ወደ ጉሬው ለመግባት
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ቅዳሜ ጥር ፪ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፰
የመጨረሻ መሠናዶውን እያደረገ ነው
· የትግሬ-ወያኔዎች ከተለያዩ ጎሣዎች እና ነገዶች ሰዎችን መልምለው እና አደራጅተው፣ እንዲሁም የወታደራዊ፣ የደህንነት፣ የአደረጃጀት፣ የአመራር እና የቁጥጥር ሥራ የሚሠሩ የትግሬ-ወያኔዎች መድበው በከፍተኛ ሚሥጢር ኢትዮጵያን የማፈራረስ ሤራ እየተዶለቱ መሆኑን በተጨባጭ መረጃዎች አረጋግጠናል።
· የትግሬ-ወያኔዎች ከተለያዩ ጎሣዎች እና ነገዶች ሰዎችን መልምለው እና አደራጅተው፣ እንዲሁም የወታደራዊ፣ የደህንነት፣ የአደረጃጀት፣ የአመራር እና የቁጥጥር ሥራ የሚሠሩ የትግሬ-ወያኔዎች መድበው በከፍተኛ ሚሥጢር ኢትዮጵያን የማፈራረስ ሤራ እየተዶለቱ መሆኑን በተጨባጭ መረጃዎች አረጋግጠናል።

የትግሬ-ወያኔ የመጨረሻ ግብ ኢትዮጵያን በመበታተን፣ የትግራይ ረፑብሊክ መመሥረት መሆኑን በ1968 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ፕሮግራሙ መሠረት ላለፉት ፵(አርባ) ዓመታት ያደረገው ጉዞ ያሣያል። በጉዞው የኢትዮጵያን የረጅም ዘመን ታሪክ ክዶ በመቶ ዓመት መገደቡን፣ የትግሬ-ወያኔ መሪዎች እና አባሎች በተደጋጋሚ በጻፉዋቸው መጻሕፍት እና በየአጋጣሚው ባደረጉዋቸው ንግግሮች ለሕዝብ ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። «ኤርትራ በኢትዮጵያ በቅኝ ግዛትነት የተያዘች ናት፤ ስለሆነም ሻዕቢያ የሚያካሂደው የመገንጠል እና የነፃነት ጥያቄ ተገቢ እና ትክክል ነው።» ብለው፣ ከሻዕቢያ በላይ ሻቢያ ሆነው፣ የትግራይን ልጆች የጦር ማገዶ በማድረግ ኤርትራን ማስገንጠላቸው ማንም ሊያስተባብለው የማይችለው ሃቅ ነው።
የማለዳ ወግ … የኢትዮጵያ አፈር የጠራው ጠቢብ የክብር ጉዞ ፍጻሜ !
መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይውላል …!

ገዢ ቢሰባ ለመሬት አህያ ቢሰባ ላራዊት
ቢኒያም ግዛው ከኖርዌይ ኦስሎ
ይሄ ምርጫ መቼስ ስንቱን ያስታውሰናል?በደርግ ዘመን እናቶች ወንድ ልጃቸውን ከየጉያቸው እየተነጥቁ እና እየታፈሱ በጦርነት ሲማገዱ ወንድ ልጅ ላለመውለድ. . . ትዝም አላለሽ ወይ የክፉ አመቱ ላንቺና ለልጅሽ ያለቀ ስንበቱ ማህጸኔን ዝጋ ይቅር ምን አባቱ በእንባ እየዳከርሽ ብለሽ ያልሽበቱ። እያሉ ፈጣሪን ወንድ ልጅ እንዳይሰጣቸው የለመኑትን ቤቱ ይቁጠራቸው። የአፈሳና የሀገራችንን አንድምታ ለመረዳት ከሰሞኑ በየከተማዎችና ጎዳናዎች ያለው የድብደባ የአፈሳና የሞት ፍርሀት ድባብ ተቀባብሎ ለቃታ የተዘጋጁ ጥይት በእያንዳንዱ ሰላማዊ ዜጋ ጆሮ ስር ተደግኖ እንደሚራመድ በቀላሉ መረዳት ይቻላል።
. . . ጭቃ ከማቡካት ጀምሮ አብሬው ያደኩት ጓደኛዬ ስሙ ጌታቸው ይባላል። እንዴት እንደምንዋደድ እንደምንተሳሰብ እና እንደምንመካከር አትጠይቁኝ። በቃ ጌቾ ምርጥ ጓደኛዬ ነው።
. . . ጭቃ ከማቡካት ጀምሮ አብሬው ያደኩት ጓደኛዬ ስሙ ጌታቸው ይባላል። እንዴት እንደምንዋደድ እንደምንተሳሰብ እና እንደምንመካከር አትጠይቁኝ። በቃ ጌቾ ምርጥ ጓደኛዬ ነው።
ሰሚ ያጣ ጮኸት ከካርቱም – አጥናፉ መሸሻ
በመላው አለም ለምትገኙ ኢትዮጽያዊያኖች ሁሉ ፤ በተለያዩ ግዜያት ሰብአዊ መብታችን ይከበር ዘንድ ፤ ከምድር ሱዳን የሲቃ ጮኸታን ሰምታችሁ በተቻላችሁ መጠን ትታደጉን ዘንድ ደጋግመን በፁሁፍ አሰምተናል ፤ እንሆ በአሁኑ ሰአት ወያኔ ከምንግዜውም በላይ በከፋ መልኩ ፤ ካርቱም ውስጥ ስደተኛውን አንደተለመደው እያሳፈሰ ፤ ወዳልታወቀ እስር ቤት እያሳወሰደ ይገኛል ፤ በተለይ ጀዋዛት እየተባለ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ ፤ በሸህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ታጉሮው ይገኛሉ ፤ ከእነዚህም ውስጥ ለልደት ደሮ ለመግዛት ገበያ የሔዱ እህቶቻችን ከነደሮቸው ፤ ልደትን መድሀኒአለም ቤተክርስትያን አክብረው የሚመለሱ ነጭ የለበሱ ወገኖች እስር ቤቱን ሞልተውታል ፤ በተጨማሪ ዴም እየተባለ ከሚጣረው ሰፈር ውስጥ አንድ ወጣት ሀለፎም አዲሱ ተካልኝ የተባለ የአንገት መስቀሉን በጥሰው መኪና ላይ ጭነው እስር ቤት አጎረውት ይገኛል ፤ መታወቂያ ለማውጣት እድሜው የማይፈቅድ ወጣት ሳይቀር ያለ አንዳች እርህራሔ አስር ቤት ይገኛል ፤ ይህን ወጣት እንደምሳሌ ተጠቀምንበት እንጅ በርካታ ወጣቶች መኖራቸውን አናሳስባለን;;
“አንዱ ቡድን ሌላዉን ጥሎ ለማለፍ የሚያደርገዉ ግብግብ ዉጤታማ ሊሆን አይችልም” ትንሳኤ ኢህአፓ
እኛ የትንሳኤ ስብስብ በተለያዩ ጊዜያት በጽሁፍ፤ በሬዲዮ ብሎም በቴለቪዥን መስኮትያለንን አላማ ለኢህአፓ አባላቶችና በተለያዬ ምክንያት ከድርጅቱ ለወጡ እንዲሁም በድርጅቱ ዉስጥ ለመታገል ለሚፈልጉ ታጋይ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በተደጋጋሚ አሳዉቀናል፤ ዛሬም እንደገና ወደፊት ድርጅቱን ለማጠናከር ተገቢ ናቸዉ ብለን ለምንመኛቸዉና አጥብቀን ስለምንታገልለት ዴሞክራሲያዊ አካሄድ መተንተኑ ተገቢ ነዉ እንላለን፤፤
አሁንም ቢሆን የኢህአፓ ከሁለት መከፈል እጅጉን አሳዝኖናል፤ አበሳጭቶናልም፤ ይህነዉ የሚባል ወይም መሰረታዊ የሆነ የአላማ፤ የርእዩተ አለምና የራእይ ልዩነት ሳይኖር፤ ብዙ ጓዶች ዉድ ህይወታቸዉን የገበሩበት፤ የቆሰሉለትና የደሙለትን ድርጅት፤ ሃላፊነት በጎደለዉና ከምክንያት ይልቅ በስሜት ተገፋፍቶ፤ በግብር ይዉጣ መልክ ድርጅቱን መከፋፈልና ትግሉን አደጋ ላይ መጣሉ፤ በትንሳኤ ስር የተሰባሰብነዉን ጓዶች አንገብግቦናል አሳስቦናልም፤ ለዚህም ነዉ እራሳችንን አሰባስበንና አጠናክረን በዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት የሚመራና፤ ከሁላም በላይ ለሰፊዉ ህዝብ የበላይነት የሚታገል የጋራ አአንድ ኢህአፓ ለማሰባሰብ ያለምነዉ፤፤
Friday, January 9, 2015
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፖለቲካዊ ደባ አንድነት ከመስመር አይወጣም! – አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ!
በየትኛውም የአለም ክፍል በተለያየ አጣራርና ስያሜ ቢሰጣቸውም ምርጫን ለማስፈፀም በሕግ የሚቋቋሙ ተቋማት ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ተቋማት በአንድ ሀገር ዘላቂ ለሆነ ሠላምና መረጋጋት ብሎም ለዴሞክራሲዊ ስርዓት ግንባታ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ በአንባገነን ስርዓት ውስጥ ላሉ ሀገሮች ደግሞ ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ ያላቸው ሚና ከምንም በላይ ከፍተኛ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራው ምርጫ ቦርድ ይህን የመሰለ ግዙፍ ተግባር እንዲያከናውን፣ የሕዝብ እና የሀገር አደራ እንዲወጣ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም ነው፡፡ የዚህ ተቋም አሰራር በተቋቋመለት ዓላማ፣ ሕግ እና አለም አቀፍ መስፈርት መሠረት ነፃ፣ ገለልተኛ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያለው መሆን ይጠበቅበታል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀደሙት አሠራሮችና ውሳኔ አሰጣጦች በበርካታ ኢትዮጵያውያን እና አለም አቀፍ ታዛቢዎች በአሉታዊ ጎኑ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በመላው ሀገሪቱ ለምትገኙ ለአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ! ወሳኝ የትግል ምእራፍና ወሳኝ ሰዓት ላይ እንገኛለን !!!
ኢህአዲግና ምርጫ ቦርድ በስውር ከተደራጁ ህገ-ወጥ የማፊያ ቡድኖች ጋር በመሆን አይበገሬና በቆራጥ ሰላማዊ የነፃነት አርበኞች የተገነባውን አንድነት ፓርቲን ላለፉት ጊዜያት ፓርቲያችንን ለመበታተንና የህዝብ አለኝታነቱን በማሳጣት ከምርጫ ለማስወጣትና ሰላማዊ የትግል ሂደቱን ለማኮላሸት ያልፈነቀሉት ድንጋይ እንዳልነበረ፤..መላው ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያንና የአንድነት አባላት ሲከታተሉት የነበረ ሀቅ ነው፡፡ ……በኢህአዲግ የበላይነት የሚመራው ምርጫ ቦርድ፤….. በህወሀት ካድሬዎች ተቀባብሎ የሚሰጠውን አንድነትን ኢላማ ያደረገ ጥይት ለመተኮስ ወደኋላ አልተመለሰም፡፡ ….ከጥቂት የስርአቱ ተላላኪ በአንድነት ውስጥ የተሰገሰጉ ሰርጎ ገቦችና በገንዘብ የተገዙ የሀገርም ሆነ የወገን ፍቅር የሌላቸው ባንዳዎች ጋር በመደራጀት አንድነትን የመፈረካከስ ውጥናቸውን ለማሳካት በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ በጅተው ሲንቀሳቀሱ ሰንብተዋል፡፡
ለምን ወለድናቸው?። – ዳዊት ዳባ።
ፖሊስ የደብረ ማርቆስ ተማሪዎችን እየደበደበ ነው፡፡ የትናንትናው ተቃውሞ በኢሳትና በሌሎች ሚዲያዎች መተላለፉን ተከትሎ ‹‹ማን ነው ከኢሳትና ከሌሎች ሚዲያዎች ጋር እየተደዋወለ መረጃ የሚሰጠው?›› እንዲሁም ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ካለ ተናገሩ›› በሚል ተማሪዎቹን አሳልፈው እንዲሰጡ ከፍተኛ ደብደባ እየፈጸመ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡ ፖሊስ አሁንም ተማሪዎችን እየፈለገ እያሰረ መሆኑም ተገልጾአል ይላል የዛሬ ዋና ዜና።
ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ ዝዋይ የታሰሩ 16 የፖለቲካ እስረኞች ጠያቂና ምግብ እንዳይገባላቸው ተከለከሉ
ነገረ ኢትዮጵያ
• የሰማያዊ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ባልደረባ እንዳይጠይቁ ተከልክለዋል
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ በዝዋይ የፌደራል ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙ 16 የፖለቲካ እስረኞች ባልታወቀ ምክንያት ጠያቂና ምግብ እንዳይገባላቸው ተከለከሉ፡፡

ጠያቂዎቹ ‹‹የመጠየቅ መብት አለን›› በሚል ወደ ውስጥ ለመግባት ግፊት በማድረጋቸው ፖሊሶች ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ አበበ ቀስቶ፣ ናትናኤል መኮንን፣ በቀለ ገርባ፣ ጄኔራል አሳምነው ጽጌና ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጨምሮ ጠያቂና ምግብ እንዳይገባላቸው የተከለከሉትን የ16 የፖለቲካ እስረኞችን ስም ዝርዝር አሳይተዋቸዋል፡፡
ፍትሕ አያረጅም! የኢትዮጵያና የአርሚኒያ ትግል -ኪዳኔ ዓለማየሁ
መግቢያ፤

የግልና የ«ብሄር» ነፃነት በኣቶ ገብሩ ኣስራት እይታ
ኣምሃ ኣስፋው
«ሉኣላዊነትትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ» የተሰኘው የኣቶ ገብሩ መፅሃፍ ከፍተኛ ተቀባይነትና ኣድናቆት እንዳተረፈ በየድረ ገፁ ተወስቷል። መፅሃፉ በኣማርኛው ጥራትም ሆነ በይዘቱ ጥልቀት ሊደነቅ የሚገባው ይመስለኛል። እርግጥ ብዙ የፊደል ግድፈቶች ኣሉበት። ይህ ግን፣ የኣርታኢዎች ስህተት ብቻ ሳይሆን፣ መቀምሮች (Computers) ማንም ሳያዛቸው በራሳቸው ፊደሎችን የመቀያየር ጠባይ ስላላቸውም ጭምር ነው። ይህ መፅሃፍ የደረሰን ከወያኔ/ህወሃት ኣባል እይታ ቢሆንም የዘመኑን ታሪክ ለማወቅ እጅግ ጠቃሚ ይመስለኛል። ሁኔታው ሲፈቅድ፣ ኢትዮጵያዊያን ልጆች ከሚማሩባቸው መፃህፍት ኣንዱ ቢሆን ከተለያዩ ኣቅጣጫዎች በሚመጡ ሃሳቦች የታነፁ ዜጎችን ለማፍራት ይጠቅማል የሚል እምነት ኣለኝ።
የኣቶ ገብሩን መፅሃፍ በኣማርኛው ጥራትና በይዘቱ ጥልቀት ባደንቀውም፣ የኣንድምታውን ትክክለኛነትም ሆነ የጭብጡን እውንነት እቀበላለሁ ማለቴ ኣይደለም። የዛሬው ፅሁፌም ምክንያት ከማይስማሙኝ ኣስተሳሰባቸው ኣንዱን ለመተቸት ነው፤ በንግግር ነፃነት ስለሚያምኑ ትችቴ ቅር እንደማያሰኛቸው በማመን።

ኣቶ ገብሩ ባለማለት፣ የማለትን ጥበብ የተካኑ ፖለቲከኛ ይመስላሉ። የኣፄ ቴዎድሮስን የጀግንነት ኣሟሟት ሲተርኩ፣ ጠላቶቻቸውን፣ እንግሊዞችን፣ እየመሩ ያመጡት ኣፄ ዮሃንስ መሆናቸውን ይዘሉታል። የኣፄ ምኒልክንና የጣሊያኖችን ውል ደጋግመው ሲያትቱ፣ ጣሊያኖች ኤርትራን በኣፄ ዮሃንስ ዘመን ያልያዟት ለማስመሰል ይሞክራሉ። በሻብያና በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል በተደረገው የመጨረሻ ጦርነት፣ ከምእራብ እስከምስራቅ፣ ከሰሜን እስከደቡብ ያለውን ህዝብ ጀግንነት ሲያሞግሱ፣ ሸዋን እንዳልነበረ ሁሉ ይዘሉታል። በምርጫ 97 የቅንጅትን ኣባል ማህበሮች እንቅስቃሴ ሲገልፁ፣ የመኢኣድ ኣስተዋፅኦ እንዳልነበር፣ እነ ኣቶ ሃይሉ ሻውል ደግሞ እንዳልተፈጠሩ ለማድረግ ሞክረዋል። በደፈናው «ነባር ፖለቲከኞች» ይሏቸዋል። ኣድሃሪ፣ ፊውዳል፣ ነፍጠኛ፣ ትምክህተኛ፣ ምናልባትም እንደ ቀስተ ደመና የምሁራን ሳይሆን የደንቆሮዎች ስብስብ ከሚል ኣስተሳሰብ ብዙም የራቁ ኣይመስለኝም።

እነዚህ የቀድሞ ባለስልጣኖች ስልጣናቸውን ሲነጠቁና ጥቅማቸውን ሲነፈጉ የሚያሰሙት የ«ተሳስተን ነበር» ጩኸት ይገርመኛል። እንዲያውም የጥላሁንን ዘፈን ያስታውሰኛል።
ለመላው የክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፥ – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፪ሺህ፯ኛ የልደት በዓል አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ አፈር የጠራው ጠቢብ፣ የድሆች አባት ዶ/ር በርናርድ ተለየን ! -ነቢዩ ሲራክ
የማለዳ ወግ …የድሆች አባት ዶ/ር በርናርድ ተለየን !
* የኢትዮጵያ አፈር የጠራው ጠቢብ
*” ክብር ሞቱ ለሰማዕት ”
* የኢትዮጵያ አፈር የጠራው ጠቢብ
*” ክብር ሞቱ ለሰማዕት ”
ዛሬ የምናዘክረው ሰው የኢትዮጵያ አፈር ፍቅር ጠርቶት ለጉስቁል ተገፊው ደሃ የሀገሬ ሰው ህይዎት ትንሳኤ ተግቶ ለውጥ ስላመጣ ጠቢብ ነው። ዝካሬ ታሪኩ ቢያስተምረን ፣ አርአያ ሰብዕናው ግብአት፣ ተሞክሮ ቢሆነን ፣ ህይዎት ንብረቱን በእኛው ቀዬ ስላፈሱሰ ትጉት ሀኪም ነው ! ነፍሳቸውን ይማር ብለን ለሰሩት ስራ ክብር በመስጠት እናዘክራቸዋለን! ዶክተር በርናርድ አንደርሰን ይባላሉ ! በርናርድ ዛሬ አይሰሙም ፣ አያዩንም …
የዶር በርናርድን እረፍት ያረዳችኝ መነኩሴዋ እናቴ ሀዘኑ ጎድቷት ” ልጀዋ ዋርካችን ተገረሰሰ እኮ ፣ የድሆች አባትና ጠዋሪ መድሃኒታችን አጣንኮ … ” ነበር ያለችኝ … ያልጠበቅኩት ነበርና ድንጋጤው መላ አካሌን ወረረው ። የእንባ ሳግ እየተናነቃት ሃዘኗን ያጋራችን እናቴን ከማጽናናት ባለፈ ምንም ማለት አልተቻለኝም! እናም ስለ ጠቢቡን የድሆች አባት ዶር በርናርድ አንደርሰን ላዘክር በተጎዳ ስሜት ብዕሬን ሳነሳ ጠቢቡ በሰጡት የኑዛዜ ቃል መሰረት ቀብራቸው በሚወዷት ሀገረ ኢትዮጵያ ምድር ይሆን ዘንድ በተናዘዙት መሰረት ሊፈጸም ተቃርቧል ። ውድ ባለቤታቸው የአርበኛው ደራሲ ገሪማ ታፈረ ልጅ ከሲስተር እማዋይሽ ገሪማም ከምድረ አሜሪካ የዶር በርናርድን ቃል ለመፈጸም ዛሬ እኩለ ቀን አ.አ ይገባሉ ! ጥቂት ስለድሆች አባት በርናርድ አንደርሰን ላጫውታችሁ …
የበደል ድርድር – የቅጥፈት ውድድር። (ከሥርጉተ ሥላሴ)
/ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

መታረም የሚገባዉ ማነዉ? ርዕዮት አለሙ ከቃሊቲ እስር ቤት
በግል የህትመት ዉጤቶች አማካኝነት በሀገሬ ዉስጥ የምመለከታቸዉን ችግሮች ለህዝብ ማቅረብና እንደዜጋም መፍትሔ ይሆናሉ ብዬ የማስባቸዉን ሀሳቦች መጠቆም ከጀመርኩ አምስት አመታት አለፉ፡፡ የመጀመሪያ ፅሑፌን ያዘጋጀሁት ” “ስህተቶችን” ለማረም የተፈፀሙ ስህተቶችና የስህተት ማረሚያ እርምጃዎች” በሚል ርዕስ እንደነበረ አስታዉሳለሁ፡፡ በዚህም ፅሑፍ የፕሬስ፣የፖለቲካፓርቲዎች ምዝገባና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የተመለከቱ አዋጆች የወጡበት ምክንያትና እንደሀገር የሚያሳድሩትን ተፅእኖ ለመዳሰስ ብሎም ኢህአዴግ ከስህተቶቹ እንዲታረም ለመምከር ሞክሬያለሁ፡፡
የኢህአዴግ ሰዎች በአንድ የገዢዉ ፓርቲ ልሳን በሆነ ድረገፅ አማካኝነት የማስጠንቀቂያ ይዘት ያለዉ ምላሽ መስጠት የጀመሩት ከላይ ከጠቀስኩት የመጀመሪያ ፅሁፌ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በአዲስፕሬስ ጋዜጣ ላይ በአዘጋጅነት ተቀጥሬ መስራት ስጀምር ግን ሁኔታዉ እየባሰ መጣ፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም አዳማ ላይ ከተለያዩ ሚዲያዎች ለተዉጣጣን ጋዜጠኞች የሰጠዉን ስልጠና ከተካፈልኩ በኋል ከስልጠናዉ ጋር በተያያዘ ለህትመት ያበቃሁት ፅሁፍ ኢህአዴጎችን በእጅጉ አስቆጣቸዉ፡፡ በመሆኑም ወደቢሮአችን ተደዉሎ ከኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የተደወለ መሆኑ ከተገለፀ በኋላ ለጽሑፌ ምላሽ የላኩ በመሆኑ በፍጥነነት እንድናወጣዉ ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጠን፡፡ ምላሻቸዉን ለማዉጣት የእነሱ መደወልም ሆነ ትዕዛዝ አስፈላጊ አልነበረም፡፡ የዝግጅት ክፍላችን አንድ ጽሑፍ የቀረበበት አካል ምላሹን በዚያዉ በተፃፈበት የህትመት ዉጤት ላይ ማስነበብ እንደሚችል በህግ የተደነገገ መሆኑን ከማወቁም በላይ የትኛዉንም አይነት ሀሳብ ለማስተናገድ ክፍት ነበርና ምላሻቸዉን በጋዜጣችን ላይ ታተመ፡፡ በዚህ ብቻ ግን አልተገቱም፤ በወቅቱ የገዢዉ ፓርቲን ሀሳብ በማቀንቀን ይታወቁ የነበሩት እንደ ዳጉ ኢትዮጵያና ሰነድ ያሉ ጋዜጦች ሀሳቦቼን በሃሳብ መምታት ባለመቻላቸዉ ይሁን ባለመፈለጋቸዉ ተራ ዘለፋዎችን ያወርዱብኝ ጀመር፡፡

Wednesday, January 7, 2015
አሁን አንድነት ግልፅ ጦርነት የታወጀበት ይመስላል – አቶ ኪዳኔ አመነ – የመድረክ ወጣት አመራር
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በተመለከተ ብዙ እየሰማን ነው፡፡ ፓርቲው ራሱን የማፅዳት ሃላፊነት ከተወጣ በኋላ ገዢው ፓርቲ ጥርሱን የነከሰበት ይመስላል፡፡ ብዙ ፈተና እየገጠመው ነው፡፡ በምርጫ ቦርድ ጥያቄ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ በድጋሚ እስከማድረግም ደርሰዋል፡፡
በኔ እምነት አንድነት ፓርቲ በበኩሉ ብዙ ርቀት የሄደ ይመስለኛል፡፡ ትእግስታቸው አደንቃለሁ፡፡ ፓርቲው በውስጡ ከጥቂቶች በቀር በዙዎቹ ቁምነገር የሚያስቡ የምናከብራቸውና የምንወዳቸው ጥሩ ሰዎች አሉት፡፡ ትርጉም ያለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ጥቂት ፓርቲዎች አንድነት አንዱ ነው፡፡
በኔ እምነት አንድነት ፓርቲ በበኩሉ ብዙ ርቀት የሄደ ይመስለኛል፡፡ ትእግስታቸው አደንቃለሁ፡፡ ፓርቲው በውስጡ ከጥቂቶች በቀር በዙዎቹ ቁምነገር የሚያስቡ የምናከብራቸውና የምንወዳቸው ጥሩ ሰዎች አሉት፡፡ ትርጉም ያለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ጥቂት ፓርቲዎች አንድነት አንዱ ነው፡፡
ታሪክ ለመስራት እንዘጋጅ – አቶ ተክሌ በቀለ የአንድነት ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር
አንድነት ፓርቲ የኢህኣዴግን ምንነት ላላመኑ ወገኖች ለማጋለጥ በትጋትና በስሌት ሲሰራ ቆይቷል፡፡እየሰራም ነዉ፤እዚህ ደርሷል፡፡ “የሆደ ሰፊዉን ምርጫ ቦርድ” ሆድ በገሃድ አጋልጧል፡፡በነአሞራዉና ወዲ ቐሺ(በተጋሩ ሁሉ) ትግልና ሞት የሚቀልዱትን በህዝብ ፊት ወጥተዉ ዛሬም እንዲዋሹና ለኢትዮጵያችን የፖለቲካ ታሪክ እነማን ምን እንደሆኑ አንድነት ፓርቲ የበኩሉን ሚና ተጫዉቷል፡፡ ለኔ ከባድመ ዉሳኔና ልህዝቡ በወቅቱ ከተነገረዉ ጋር ይመሳሰላል፤ይጠጋጋል፡፡
ኢህኣዴግ ምርጫዉን እንደማይፈልገዉ፤ከፈለገዉም ለተለመደዉ ቀልዱ ከነማን ጋርና በምን ሁኔታ እንደሚፈልገዉ ፓርቲያችን ሶስተኛዉን (የአዉሮፓና አሜሪካ ታዛቢዎች የሌሉበት ምርጫ መሆኑን፤የህዝብ ታዛቢዎች የተበላሸ የምርጫ ሂደትና ፓርቲዎችን የማፈራረስ/የማዳከም ስራዎች) ነጥብ አስመዝግቧል፡፡
ኢህኣዴግ ምርጫዉን እንደማይፈልገዉ፤ከፈለገዉም ለተለመደዉ ቀልዱ ከነማን ጋርና በምን ሁኔታ እንደሚፈልገዉ ፓርቲያችን ሶስተኛዉን (የአዉሮፓና አሜሪካ ታዛቢዎች የሌሉበት ምርጫ መሆኑን፤የህዝብ ታዛቢዎች የተበላሸ የምርጫ ሂደትና ፓርቲዎችን የማፈራረስ/የማዳከም ስራዎች) ነጥብ አስመዝግቧል፡፡
Monday, January 5, 2015
ዛሬ የወያኔው ፖሊስ ስለለቀቀው የአንዳርጋቸው ጽጌ አዲስ ቪድዮ ዙሪያ የተሰጡ አስተያየቶች
የሕወሓት አስተዳደር ፖሊስ ዛሬ ስለአንዳርጋቸው አዲስ ቪድዮ ለቋል:: በየሶሻል ሚዲያዎችም መነጋገሪያ ሆኗል:: በዚህ ዙሪያ ከሶሻል ሚዲያዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ስለቪድዮው ሰብስበናል ያንብቧቸው:-

የጆሜክስ ካሳዬ አስተያየት:-

የጆሜክስ ካሳዬ አስተያየት:-
ሌባና ፖሊስ የሚባለው የገዢው አገልጋይ የሆነው የፌዴራል ፖሊስ ፕሮግራም የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ቪዲዮ በማሳየት አሜሪካን የሚያስንቅ የምርመራ ሥልት አለን እንደ ሌባ ሻይ ሳንገርፋቸው ይናዘዛሉ በማለት የድፍረቱን (የድድብናውን) ልክ ሊያሳየን ሞክሯል፣ ይህ መራር ቀልድ በአስቀያሚ የማዕከላዊ ምርመራ ሂደት ውስጥ ያለፉትንና ቶርቸርን ያስተናገዱት ጓደኞቼን ሳስብ ድፍረቱ አሳምሞኛል ፤ጓደኞቼም በማዕከላዊ ቆይታቸው የታዘቡት ጥፍራቸው የተነቀለባቸውን ተማሪዎች ሳስብ እነዚህን መርማሪዎች እና ጋዜጠኞች በፍትህ አደባባይ አገኛቸው ዘንድ ዘወትር እናፍቃለሁ፤
ፕሮግራሙ አሜሪካን ሊያብጠለጥል የፈለገበት እና የጠቀሰወው ሰሞነኛው የቶርች ሪፖርት ኢትዮጵያም ተሳታፊ መሆኗን እንዳጋለጠ ዘንግተውት ይሆን ብዬ አልጠይቅም አንዴ ምንም አያመጡም አያውቁም ተብለን ተንቀናልና (ሕዝብን ከመናቅ ካለሆነ ከምን ይመነጫል?)፡፡
ዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ለአስራ አምስተኛ ጊዜ ተቀጠሩ
በዛሬው እለት በካንጋሮ ፍርድ ቤት የቀረቡት የዛኦን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ከዚህ ሁሉ ኢ-ፍትሃዊ እስር በኋላም ቢሆን ከፊታቸው ላይ ሳቅና ፈገግታን ሊነጠቁ ያልቻሉ መሆኑ በግልጽ ለአምባገነኖች እና አሽከሮቻቸው አሳይተዋል:: በሙሉ ራስ መተማመን ስሜት እና በታላው ብሩህ መንፈሳቸውን ተላብሰው ካንጋሮ ፍርድ ቤት ይደረሱት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የአሸናፊነት ስሜት በፊታቸው ይነበባል::ፖሊስ ጉዳዩን የሚከታተሉ እና በፍርድ ቤቱ የተገኙትን ስልካቸውን እንዲያጠፉ ያደረገ ሲሆን በችሎት ክተሰየሙት ዳኛ አንዱ መቀየራቸውም ታውቋል:;እንዲሁም ፖሊስ ያሰራቸውን ጦማርያን እና ጉዳዩን ሊክታተሉ የመጡትን በአይን እንኳን እንዳይነጋገሩ ሲያዋክብ ታይቷል::
Friday, January 2, 2015
ግንቦት 7 – ቀኑ ሲቃረብ መውጫው ይጠባል!

አቶ በረከት እሱን መች ጠየቅንህ?
ከፍተኛ ይቅርታ ይህ ጦማር ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለው ተቆርጦ በመቅረቱ ታርሞ ቀርቧል።
ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ(ህወሃት)የተመሠረተበትን አርባኛ ዓመት ለማክበር ሽር ጉድ እየተባለ ባለበትና በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ የሀገሪቱ የገንዘብ ወጭ ተደርጎ አስረሽ ምችው የሚደለቅበት ሰአት ላይ ያለን ሲሆን የዘድሮው በዓል አከባበር ደግሞ የተለየ ሆኗል አስቀድመው ነው የጀመሩት ያም ሆነ ይህ በዓሉ ለምን ይከበራል? የሚያከብረውስ ማን ነው? ብለን ስንጠይቅ ድርጅቱ በጫካ አሥራ ሰባት ዓመት በትረ ሥልጣኑን ከጨበጠ በኋላ በከተሞች ለሃያ ሦሥት ዓመታት ያህል የምሥረታ በዓሉን በከፍተ የገንዘብ ወጭ እያከበረ ዘልቋል።
የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይግባኝ ለታህሳስ 30 ተቀጠረ * ዝዋይ እስር ቤት ሆኖ በፕላዝማ ችሎቱን ተከታትሏል

(ዘ-ሐበሻ) ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ያስገባው የይግባኝ ጥያቄን ለመስመት ስድስት ኪሎ የሚገኘው ፍርድ ቤት ተሰይሞ የነበረ ሲሆን ጉዳዩን ተመስገን እስር ቤት ሆኖ በፕላዝማ ተከታትሏል::
ከ’ፍሪ ተመስገን ደሳለኝ” የፌስቡክ ገጽ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ዛሬ ታህሳስ 23/2007 ጠቅላይ ፍረድቤት በዋለው ችሎት የጋዜጠኝ ተመስገን ደሳለኝን ይግባኝ ከሰማ በኋላ ጉዳዩ ለይግባኝ ያስቀርባል አያስቀርብም የሚለውን ለመወሰን ለታህሳስ 30/2007 ዓ.ም ቀጥሮ ሰቷል፡፡
ግንቦት 7 – ቀኑ ሲቃረብ መውጫው ይጠባል!

መልዕክት ከቂሊንጦ እስር ቤት! አብርሃ ደስታ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
‹‹እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም›› አብርሃ ደስታ
እዚህ እስር ቤት ውስጥ በሽብር ስም የገባ ሰው በፈጠራ ወንጀል እንደገባ ነው የሚታመነው፡፡ ስለዚህ የሽበር ክስ ተመስርቶባቸው የታሰሩትን ሰዎች ማንም ወንጀለኛ አድርጎ አይመለከታቸውም፡፡ በእርግጥም አሸባሪ የለም፤ የፈጠራ ክስ ነው ያሳሰራቸው፡፡ አሸባሪ አለ ከተባለም እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም፡፡
ነጻ መውጣት ያለበት ቡድን አለ፣ እሱም ኢህአዴግ ራሱ ነው፡፡ እኔ አልታሰርኩም፡፡ የታሰሩት ኢህአዴጎች ናቸው፡፡ እስር የአዕምሮ ነው፡፡ እኔ አዕምሮየ አልታሰረም፡፡ ነጻ ሰው ነኝ፤ ውስጤ በጣም ነጻነት አለው፡፡ የታሰሩት ኢህአዴጎች ናቸው፡፡
አቶ በረከት እሱን መች ጠየቅንህ?
ከፍተኛ ይቅርታ ይህ ጦማር ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለው ተቆርጦ በመቅረቱ ታርሞ ቀርቧል።
ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ(ህወሃት)የተመሠረተበትን አርባኛ ዓመት ለማክበር ሽር ጉድ እየተባለ ባለበትና በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ የሀገሪቱ የገንዘብ ወጭ ተደርጎ አስረሽ ምችው የሚደለቅበት ሰአት ላይ ያለን ሲሆን የዘድሮው በዓል አከባበር ደግሞ የተለየ ሆኗል አስቀድመው ነው የጀመሩት ያም ሆነ ይህ በዓሉ ለምን ይከበራል? የሚያከብረውስ ማን ነው? ብለን ስንጠይቅ ድርጅቱ በጫካ አሥራ ሰባት ዓመት በትረ ሥልጣኑን ከጨበጠ በኋላ በከተሞች ለሃያ ሦሥት ዓመታት ያህል የምሥረታ በዓሉን በከፍተ የገንዘብ ወጭ እያከበረ ዘልቋል።
Subscribe to:
Posts (Atom)