Thursday, April 2, 2015

የማለዳ ወግ …” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” አንጀሊና * ዘሐራ ጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት ስታደምቅ .

ለማፍቀር መፈቀር ፣ ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ግድ ይላል ! ይህ ተፈጥሯዊ ህግ ሆኖ በሁላችንም ላይ ባይሰረጽም የታደሉት ሲሆኑትና ሲታደርጉት ከማየት አልፎ የድካማቸው ፍሬ አፍርቶ ሲያዩት ምስክር እማኝ መሆን መታደል ነው ። መልካም መስራት ለራስ ነው እንዲሉ ውስጥን ከሚሰጠው እርካታ ባሻገር የታደሉት የዘሩት አሽቶ መልካም ስራቸው በስኬት ጎዳና ሲታይና በውጤት ስኬቱ ሲደምቁ ማየት ከምንም በላይ ያስደስታል ። በአንጻሩ መልካም ሰርተው እጃቸው ” አመድ አፋሽ ” የሆኑንም አለማችን ከማስተናገድ አልቦዘነችም ። የአማድ አፋሽነቱ ህመም ጥልቆ ቢያመም የሰሩት ለውስጥ እርካታ ነውና ሁሉምም የሚያየው አንድ ፈጣሪ ፍርድ ይሰጣልና ህመሙ ህመም አይባልም ። አድርጎ “አመድ አፋሽ ” መሆን ክሽፈት ነው ከተባለ ምድራዊ ጊዜያዊ ክሽፈትነት ፈቀቅ አይልም ፣ የመልካምነት ሰማያዊ ጸጋቸው ሰፊ ነውና እኒህም የታደሉ ናቸው !

አሳዛኝ ዜና በየመን ጦርነት 45 ኢትዮጵያዊያን ሞቱ ከ60 በላይ ቆሰሉ

ሰሞኑን ያለማቋረጥ የመን ላይ እየተወሰደ ባለው የአየር ጥቃት ምክንያት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በከፍተኛ ችግርና ጭንቀት ውስጥ ነበሩ፡፡ ዛሬ በተደረገ የአየር ድብደባ ምክንያት ካምፕ ውስጥ የነበሩ 45 ኢትዮጵያዊን ሲሞቱ ከ60 በላይ ቆስለዋል፡፡ በIOM ካምፕ ላይ በስህተት የተወሰደ እርምጃ ነው በተባለው በዚህ ጥቃት ላይ ካምፕ ውስጥ የነበሩት የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች ናቸው የሞቱት የሚል መግለጫ IOM ቢያወጣም በዛ ካምፕ ውስጥ የሚጠቀሙት ኢትዮጵያዊን መሆናቸው ግን የታወቀ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ሄጄ ካምፑን እንዳየሁት እኔም የማውቀው በጅቡቲ በኩል ወደ የመን የሚገቡ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ብቻ እንደሚያርፉበት ነው፡፡

BREAKING NEWS አንድ ኢትዮጵያዊ እስረኛ ከእስር ቤት በማምለጡ በአሜሪካ ፖሊስ እየተፈለገ ነው


ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ወሰን አሳዬ የተባለ እስረኛ በአሜሪካ ለመታከም ከነበረበት ሆስፒታል በማምለጡ በአሁኑ ሰዓት በሰሜን ቨርጂኒያ ሽብር ተፈጥሯል በርካታ ፓሊሶች እንዲሁም የስዋት(SWAT) ቡድን ሀይል በቦታ እያፈላለጉት ይገኛሉ።

አሳዛኙ የተገን ጠያቂዎች ይዞታ በፈረንሳይ

በአሁኑ ጊዜ ህገ ወጥ በሚባል መንገድ በአደገኛ ጉዞ አውሮፓ የሚደርሱ ስደተኞች በሙሉ አውሮፓን እንደጠበቋት ሆና አያገኟትም ።ከሞት ተርፈው ምድሪቱን ለመርገጥ ከበቁት መካከል ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው አስከፊ ህይወት የሚገፉ ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ።
ህይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚሞክሩ በርካታ አፍሪቃውያን ስደተኞች ካስቡበት ሳይደርሱ የበረሃና የውሐ ሲሳይ መሆናቸው ተደጋግሞ የሚነገር ጉዳይ ነው ። ከመካከላቸው እድል የቀናቸው ደግሞ በህይወት አውሮፓ መድረስ ቢችሉም እዚህም የሚጠብቃቸው አበሳ ቀላል የሚባል አይደለም ። የጥገኝነት ጥያቄ ማመልከቻቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ለዓመታት የሚንገላቱ ከዚያም አልፎ በደረሱበት ሃገር ማረፊያም ይሁን ምግብ ለማግኘት የሚቸገሩ የጎዳና ተዳዳሪ ሆነው ህይወታቸውን የሚገፋም ጥቂት አይባሉም ። በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ መውጫ ላይ በሚገኝ ባቡር ጣቢያ ስር ተጠልለው የሚኖሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች ለዚህ አብነት ናቸው ።

አንድነት ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ላይ ያቀረበው ክስ ውድቅ ሆነ

ፍትህ መረገጡን ባደባባይ አስመስክረናል፤ሃላፊነታችንንም ተወተናል!! ተክሌ በከለ
ለኔ እዉነተኛዉ የአንድነት ፓርቲ ትናንት በፍ/ቤት ዉሳኔ ተቀብሯል፡፡ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል እንደሆን ቀድም ሲል አዉቀናል፡፡ዳኛ ብርቱኳንም ፍርህይወትም ዳግም አልተከሰቱም፡፡እንደ ኢህአዴጉ የምርጫ ዉጤት 99.6 ከመቶዉ አመራሩና አባላቱ በምርጫ ቦርድ እንዲበተኑ የተበየነበት እንዲሁም በደጋፊዎች የተገዛ ንብረት ያለፍ/ቤት ትእዛዝ በመንግስት ታጣቂ ፖሊሶች የተዘረፈበት አንድነት የፍትህ ተቋሙን ለመፈተሸ ም/ቦርዱን መክሰሱ ይታወቃል፡፡
ም/ቦርድን መክሰሳችን አግባብ እንዳልሆነ አንቀጽ ተጠቅሶ ከማስፈራሪያ ጋር ክሱ ዉድቅ ተደርጓል፡፡ መፍትህ መረገጡን ባደባባይ አስመስክረናል፤ሃላፊነታችንንም ተወተናል፡፡ቀጣዩን በቀጣይ ሂደት የምናየዉ ይሆናል፤እንደሚፈልጉት ተበትነን አንቀርም፡፡አንድነቶች በያለንበት እንረጋጋ!!

ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ የቴድሮስ አድሃኖም ዋና አማካሪ የሃሰት ፕሮፌሰር እደሆኑ አበበ ገላው አጋለጠ

አዲስ ቮይስ– የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤትና የሚኒስትሩ ዋና አማካሪ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናትና ትንተና የበላይ ሃላፊ የሆኑት “ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ የሃሰት ፕሮፌሰር እደሆኑ አዲስ ቮይስ ባካሄደው እረዘም ያለ ምርመራ ማረጋገጥ ችሏል።። ግለሰቡ ለ15 አመታት በፕሮፌሰርነት አገልግየዋለሁ የሚሉት አንድ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ እንደማያውቃቸው የገለጸ ሲሆን የዶክትሬት ዲግሪ ያገኙበት ተቋምም በአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት “የዲፕሎማ ወፍጮ” (diploma mill) ተብሎ የተፈረጀ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

“ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ ከኦክቶበር 2010 ጀምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋና አማካሪ ሆነው በመንግስት የተሾሙ ሲሆን አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩ ወቅት ዋና አማካሪያቸው ሆነው ያገለገሉት እኚሁ ግለሰብ በአሁኑ ግዜ የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ዋና አማካሪ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናትና ትንተና ክፍል የበላይ ሃላፈ ሆነው በመስራት ላይ ይገኛሉ።