Sunday, October 18, 2015

ሰበርና አስደሳች ዜና … በእስር ከቀሩት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በፍቃዱ ሃይሉ ሲቀር ሌሎቹ በነፃ ተለቀዋል

የዛሬውን ችሎት አስመልክቶ ከዞን9 ጦማር የተሰጠ ማስታወሻ

ዛሬ ጥቅምት 5 2007 በዋለው ችሎት አንድ አመት ከ5 ወር እስር ቤት የቆዪት አራት የዞን9 ጦማርያን ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።
በውሳኔው መሰረት አንደኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ መከላከል ሳያስፈልጋት ከክሱ ነፃ
ሶስተኛ ተከሳሽ ናትናኤል ፈለቀ መከላከል ሳያስፈልገው ከክሱ ነፃ
አምስተኛ ተከሳሽ አጥናፍ ብርሃኔ መከላከል ሳያስፈልገው ከክሱ ነፃ
ስድስተኛ ተከሳሽ አቤል ዋበላ መከላከል ሳያስፈልገው ከክስ ነፃ የተባሉ ሲሆን
ሁለተኛ ተከሳሽ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ከሽብር ክስ ነፃ የተባለ ሲሆን መአከላዊ ምርመራ በሃይል እና በማሰቃየት የሰጠው ቃል ላይ አመፅ እንዳነሳሳ አምኗል በሚል በወንጀል ህጉ 257 መሰረት እንዲከላከል ግን ዋስትና መጠየቅ እንደሚችል ተገልፇል።
የጦማርያኑ ጠበቃ በፍቃዱ ይግባይ እንዲሰጠው የጠየቁ ሲሆን አቃቤ ህግ ተቃውሞ አሰምቶ ይግባኙ ላይ ለጥቅምት 10 ለማየት ቀጠሮ ሰጥቷል።
ባለፉት 1 አመት ከ5 ወራት በማንኛውም በቻላችሁት አቅም ሁሉ ከጎናችን ለቆማችሁ ከፍተኛ ምስጋና እያቀረብን በፍቃዱ ይፈታ የሚለው ጥያቄያችን እንደሚቀጥል ለማሳወቅ እንወዳለን።
የዞን 9 ጦማርያን ከማረሚያ ቤት ሲወጡም የምናሳውቅ ይሆናል

Monday, September 21, 2015

የኦጋዴን ነፃነት ግንባር 2 ከፍተኛ አመራሮች በአልሸባብ አንገታቸው ተቀልቶ ተገደሉ * ግንባሩ የኢትዮጵያ መንግስት እጅ አለበት ሲል ከሰሰ

Zehabesha News
(ዘ-ሐበሻ) የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ሁለት ከፍተኛ አመራሮቼ ከሶማሊያ ባይዶዋ ወደ ኦጋዴን ሲጓዙ በአልሸባብ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው ተገደሉብኝ ሲል ከሰሰ። ለዚህም ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ነው ብሏል::
የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ከቅርብ ወራት ወዲህ በጠቅላላው ከአስር የማያንሱ አባሎቼ ሶማሊያ ውስጥ በአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ አንገታቸው ታርዶ ተገድለውብኛል ብሏል ።
እንደ ግንባሩ ክስ ከሆእ የኢትዮዽያ መንግስት የደህንነት ሰራተኞች በስውር ከአልሸባብ ንዑስ ቡድን ጋር በመገናኘት ግድያው እንዲፈፀም አሲረዋል።
በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ አገዛዝ እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ ባይሰጥም ከዚህ ቀደም መንግስት የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ያለው አሸባሪ ድርጅት ነው ሲል መክሰሱ ይታወሳል:: አማጺው ቡድንም ሆነ መንግስት እርስ በራሳቸው ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው እየተባባሉ መካሰሳቸው ለብዙዎች ግርምታን ፈጥሯ

Sunday, September 13, 2015

የዴምህት ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስግዶም ለምን ከዱ?

(ECADF) – የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ዴምህት) ከአርበኞች ግንቦት7፣ ከአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ እና ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ጋር ጥምረት መመስረቱን ባወጀበት ማግስት የጥምረቱ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙትና ዴምህትን ለዓመታት ሲመሩ የኖሩት አቶ ሞላ አስግዶም መክዳታቸው ታውቋል።Former TPDM chairman Mola Asgedom
ኢሳት በአጭር ሰበር ዜና ዘገባው እንደገለጸው ከሆነ አቶ ሞላ አስግዶም ድርጅታቸው ጥምረት እንዲመሰርት ፍላጎት አልነበራቸውም። ይሁንና አብዛኛው የዴህምህት አመራሮች ጥምረቱን በመፈለጋቸው ምክንያት ጥምረቱ እውን ሊሆን ችሏል።
ፋሲል የኔዓለም (የኢሳት ጋዜጥኛ) ወደ ኤርትራ ተጉዞ በነበረበት ወቅት ከአቶ ሞላ አስግዶም ጋር የመወያየት እድል አግኝቶ ነበር። የአቶ ሞላ አስግዶም መክዳት ከተሰማ በኋላ ፋሲል እንዲህ በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል፣
“የደሚህቱ ሞላ አስገዶም መክዳቱን ስሰማ በእጅጉ ተገርሜአለሁ። ከቀናት በፊት ሞላ ፣ ሰው አክባሪ፣ ተግባቢና አገሩን የሚወድ ሰው መሆኑን ጽፌ ነበር። ኤርትራ በነበርኩበት ጊዜ ደጋግሜ አግኝቸዋለሁ ፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ጊዜ ወስደን ተነጋግረናል። እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ስለሞላ የነበረኝ አመለካከት ቀደም ብዬ የገለጽኩት ነው።

ቴዲ አፍሮ – ለእውነት፣ ለፍትህና ለፍቅር መቆም የሚያስከፍለውን ዋጋ እየከፈለ ያለ ብርቱ ሰው


የቴዲ አፍሮ ምኞቶች ዘረኝነትና ጥላቻ በመንግሥት ደረጃ በሚሰበክበት አገር፣ ድንቁርና እጅግ በተጫናቸው የወያኔ ቱባ ባለሥልጣናት ሕዝብ በሚዘለፍበት፣ ታሪክ ተጣሞ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪን የሕብረተሰብ ክፍል በሌላው ላይ ለማነሳሳት ሌት ተቀን የሚደክሙና ጉርጓድ የሚምሱ ቡድኖችና ግለሰቦች ባሉበት አገር፣ ፍርሃትና ጥርጣሬ በነገሱበትና አፈና በበረታበት እንደ ኢትዮጵያ ባለ አገር እንደ ቴውድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ‹ ያሉ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በማሕበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ሚና በዘፈን ሕዝብን ከማዝናናት እጅግ ያለፈ ነው፡፡
የቴዲ ዘፈኖች ታሪክን ለሚክዱና ለሚያጣምሙ ማስተማሪያዎች ናቸው፡፡

Sunday, September 6, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ሰነዘሩ

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የውስጥ አርበኞች በህወሓት አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ከባድ ውጊያ አድርገው ከፍተኛ ጉዳት አደረሱ፡፡The Patriotic Ginbot 7 attacks factors
የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች ህወሓት “ክልል አንድ” እያለ በሚጠራው በጎንደር-ወልቃይት ደጃች ሜዳ ወረዳ አቤራ ቀበሌ ስልኪ ዳግባ በተባለው ቦታ ነሃሴ 23 2007 ዓ.ም በህወሓት መከላከያ ኃይል ላይ ድንገተኛ የተኩስ ውርጅብኝ በመክፈት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ወታደሮችን ገድለውና አቁስለው ድል ተቀዳጅተዋል፡፡
በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞችና በህወሓት የመከላከያ ሰራዊት መካከል የተካሄደው ድንገተኛ የሆነ ከባድ ፍልሚያ እኩለ ቀን ላይ ከ6፡30 ጀምሮ እስከ 7፡30 ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ሲሆን ምሳ በመመገብ ላይ እያለ ባልገመተው ሁኔታና ባለሰበው አሳቻ ሰዓት ድንገተኛ ተኩስ ተከፍቶበት የእሳት ዝናብ በላዩ ላይ የወረደበት የህወሓት ሰራዊት አብዛኛው ተበታትኖ ከአካባቢው የሸሸ ሲሆን የአፀፋ ተኩስ ከፍቶ ለአንድ ሰዓት ለመከላከል የሞከረው ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል፡፡

Thursday, September 3, 2015

ከዊሃ እስከ ኦምሃጀር – አንድ ሰሞን ከአርበኞች ጋር (ኤፍሬም ማዴቦ)

ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። አዎ! ማተቡን ላጠበቀና በአምላኩ ለሚታመን በእርግጥ ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። ሰዉ ነኝና እንደ ፈጣሪ ቃሌ ሁሉ እዉነት ነዉ ብዬ አለተፈጥሮዬ አላብጥም። ግን ሰዉ ብሆንም ፈጣሪዬን የምፈራ ሰዉ ነኝና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስል ልቦናዬ እያወቀዉ እንደነ ጋሼ እንደልቡ ዉሸት ደርድሬ ለአንባቢ የማቀርብበት ምንም ምክንያት የለም። ከዚህ ቀጥሎ የማስነብባችሁ እያንዳንዱ ቃል እንደ ዳያስፖራ ተረተኞች የምተርተዉ ‘ሰዉ ሰዉ’ የማይሸተት ተረት ሳይሆን ኢትዮጵያ ድንበር ላይ በየግንባሩ የተሰለፉትንና በስልጠና ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አርበኞች ስጎበኝ በአይኔ ያየሁትንና በጆሮዬ የሰማሁትን ቃል ነዉ።Ephrem Madebo with Patriotic Ginbot 7 fighters
ቨርጂኒያ ወደሚገኘዉ “Dulles” አዉሮፕላን ማረፊያ የሄድኩት ከልጄ ጋር ነበር። ከቤቴ Dulles የግማሽ ሰዐት መንገድ ነዉ። ያቺን ግማሽ ሰዐትና አዉሮፕላን ማረፊያ ደርሼ ሻንጣዬን እስካስጭን ድረስ አይኔ እያንዳንዷን ደቂቃ ከልጄ ከቢኒያም አልተለየም። መለየቱን ስላልወደደዉ ልቤ ደንግጧል። ከወያኔ ጋር ለመፋለም በረሃ የሚጓዘዉ ኤፍሬም ከአንድ ልጁ መለየት አቃተዉ። ምነዉ ብዬ እራሴን ጠየኩት- እኔዉ መልሼ ምንም አልኩ። ልጄን አቀፍኩት፤ አሁንም ደግሜ ደጋግሜ አቀፍኩት። እምባ ፊቴን ሞላዉ። ቀና ብሎ ተመለከተኝና ሲከፋዉ ታየኝ። ሁለተኛ ዙር እምባ ፊቴን ሞላዉ። “Son I don’t want to do this, but I have to do it” አልኩ በሁለት እጄ አቅፌ እንደያዝኩት። ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ አባት ሆይ ፈቃድህ ከሆነች ይቺ ጽዋ ከኔ ትለፍ ብሎ የጸለየዉ ፀሎት ትዝ አለኝ። እኛ ሰዎች የዳንነዉ ይህ ፀሎት ባለመመለሱ መሆኑ ትዉስ ሲለኝ ልቤ በሀሳቡ ጸና። አባባ Come on . . . be strong. I promise I will be the son that you raised- you will be proud of me” አለኝ ቢኒያም በዚያ 17 አመት ሙሉ በማዉቀዉ ቆንጆ ድምጹ። የተናገራቸዉ ቃላት ዉስጤ ገብተዉ ኃይል ሲሆኑኝ ተሰማኝ። ጠነከርኩ። ተሰናብቼዉ ወደኋላ እያየሁት ወደ ዉስጥ ገባሁ። ወደ ፍተሻዉ ቦታ ስሄድ ልቤን ከፍተኛ የመለየት ኃዘን እንደ ግግር በረዶ ሲጫነዉ ተሰማኝ፤ መሸከም አቃተኝና እንደ ህፃን ልጅ እያነባሁ ፍተሻዉ መስመር ላይ ገብቼ ወረፋ ያዝኩ።

ሰበር: የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከጠቅላላ ጉባኤው ሲመለሱ ተደበደቡ

118
‹‹የደበደበኝና የዘረፈኝ ሰው ተለቆ እኔ ታስሬያለሁ›› አቶ ጌትነት በሱፍቃድ
በወላይታ ዞን ቦሎቶሶሬ ወረዳ አረካ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ጌትነት በሱፍቃድ ተደብድበው ንብረቶቻቸውን መዘረፋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በምርጫው ወቅት ቅስቀሳ ላይ እያሉም በገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ተመሳሳይ ወንጀል ተፈፅሞባቸው እንደነበር የገለፁት አቶ ጌትነት ‹‹በምርጫው ወቅት ቅስቀሳ ላይ እያለሁ በካድሬዎች ተደብድቤ ንብረቴን ተቀምቻለሁ፡፡ ሌሎች የትግል ጓደኞቼም ተመሳሳይ ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ሆኖም ከፖሊስ ጣቢያ ጀምሮ እስከ ከንቲባው ፅ/ቤት ድረስ በመሄድ አቤቱታ ብናቀርብም የሚሰማን አላገኘንም፡፡›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በደቡብ ኦሞ የሰፈሩ የሰራዊት አባላት መጥፋታቸውን ተከትሎ ነዋሪዎች እየታሰሩ ነው

Ethiopian soldiers stand guard near boxes of weapons found hidden under a building in Mogadishu May 9, 2007. A large cache of weapons, believed to have been hidden by the Islamists, were discovered in Mogadishu by the Ethiopian forces and their Somali allies on Tuesday. REUTERS/Shabelle Media (SOMALIA)
በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በሃመር ብሄረሰብና በዞኑ ፖሊስ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ተከትሎ በአካባቢው የሰፈረው የአንድ ሻለቃ ጦር አባላት በርካቶቹ ኮብልለው በመጥፋታቸው ፣ ለወታደሮቹ መጥፋት ምክንያት ናቸው የተባሉ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። በመከላከያ ሰራዊቱ አባላት መካካል የሚታየው አለመተማማንና ልዩነት በመስፋቱ እርስ በርስ እስከመጋጨት ደርሰዋል።
ከወር በፊት በሃመር ወረዳ በተፈጠረው ግጭት በርካታ የወረዳው ነዋሪዎችና ፖሊስ አባላት ተገድለዋል። ግጭቱን ለማብረድ አንድ ሻለቃ ጦር በተለያዩ አካባቢዎች እንዲሰፍር ተደርጓል። ይሁን እንጅ በወታደሮቹ መካካል መተማመን በመጥፋቱ ከመካከላቸው በርካታ ወታደሮች በመኮብለላቸውና የደረሱበት ባለመታወቁ፣ አመራሮቹ ወታደሮች እንዲጠፉ አድርገዋል ያሉዋቸውን የሞተር አሽከርካሪዎች ይዘው አስረዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት አሽከርካሪዎች መካከል ጌታ ጫን ያለው ወርቁ፣ አሚኑ ትኩና አሚኑ ሃሰን ይገኙበታል። አሽከርካሪዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበው፣ ከ15 ቀናት የእስር ጊዜ በሁዋላ በዋስ ሲፈቱ፣ ወታደሮቹን በማሸሹ ሂደት ተሳትፈዋል የተባሉ በርካታ ወታደሮች በአርካሻ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ።

Friday, August 28, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ ኣባል አቤል ኤፍሬም ጓደኞቹ እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር ሆኖ ቀረበ

 ነው፤ በመሆኑም የአቃቤ ህግ ምስክር ሊሰማብን አይገባም›› በሚል ተቃውሞ ቢያቀርቡም አቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ ባስገባው ክስ ላይ ምስክሩን መጥቀሱን በማስረዳት ምስክሩ እንዲሰሙለት ጠይቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የደረሰው የክስ ማመልከቻ ላይ ምስክር እንደተመዘገበ በማረጋገጥም ብቸኛ ሆነው የቀረቡትን አንድ የአቃቤ ህግ ምስክር ሰምቷል፡፡ ምስክሩም ከ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሰሾች ጋር ሰማያዊ ፓርቲ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ሆነው እንደሚተዋወቁ፣ የካቲት 12/2007 ዓ.ም በ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ሰላማዊ ትግሉ እንዳላዋጣ በመጥቀስ ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ መጓዝ ማሰባቸውን ገልጸውለት በዚያው ቀን ማታ 3ኛ ተከሳሽን ጨምሮ ወደ ባህር ዳር እንደተጓዙ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
ባህር ዳር ሲደርሱ ጠዋት ላይ ግን ምስክሩ ሀሳቡን በመቀየር ወደ አዲስ አበባ መመለስ እንደሚፈልግ እንደገለጸላቸው፣ 1ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ‹ጎንደር ላይ የምናገኘው ሰው ስላለ ቢያንስ እሱን ካገኘኸው በኋላ መመለስ ትችላለህ› እናዳለው፣ ነገር ግን ምስክሩ በሀሳቡ ባለመስማማት ወደ አዲስ አበባ መመለሱንና ሌሎቹ ሦስቱ ግን ጉዟቸውን መቀጠላቸውን አስረድቷል፡፡

Monday, August 24, 2015

ፍርድ ቤት በነጻ እንዲለቀቁ የበየነላቸው አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ እንዳይፈቱ እገዳ ተላለፈ –

(ነገረ ኢትዮጵያ) ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብርተኝነት ክስ ነጻ ናችሁ ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች የሆኑት አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሶ ነጻ የተባለው አብርሃም ሰለሞን ከእስር እንዳይለቀቁ ታግደዋል፡፡ አቃቤ ህግ ይግባኝ እንደጠየቀባቸው የታወቀ ቢሆንም እንደ ህግ ባለሙያዎች ግን የአቃቤ ህግ ይግባኝ ገና ተቀባይነት ባላገኘበት ሁኔታ ከእስር እንዳይለቀቁ እግድ ማድረግ ከህግ ውጭ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡ ነጻ የተባሉት አመራሮች ባለፈው አርብ ከእስር ይወጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም አሁን ድረስ እስር ቤት እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

Monday, August 17, 2015

አንዳርጋቸውና ጓዶቹ

አምና ሰኔ 2006 ዓ ም አንዳርጋቸው ጽጌ በትራንዚት ላይ እያለ ከየመን በወያኔ መታፈኑ ሲነገር ሃዘንና ንዴት ያልተሰማው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም። ወያኔ ኤርትራ ውስጥ እንዳለ ሊገድለው ያደረገውን ሙከራ ኢሳት በተከታታይ ስላቀረበው ምን ያህል አዳጋ ውስጥ እንዳለ ለሁሉም ግልፅ ነበር። የአንዳርጋቸው መያዝ ከታለመው ግብ በተፃራሪ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ከዳር ዳር በቁጣ በማንቀሳቀሱ አፋኞቹ አምባገነኖች ከጠበቁት ውጭ ራሳቸውን ችግር ውስጥ ነው ያገኙት። መታፈኑ ለአስርት ዓመታት አፍዝዞ የያዘን ፍርሃትንና ክፍፍልን ሰባብሮ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በጋራ እንዲቆም ከማድረጉም በላይ አንዳርጋቸው የደላ ኑሮውን ትቶ በረሃ ለበረሃ የተንከራተተለት፣ በርሃብና በበሽታ የተንገላታለት፣ ከጓዶቹ ጋር ለኢትዮጵያውያን ነፃነት ይበጃል ብሎ የደከመለት ግንቦት ሰባት በብዙ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ እንዲገባና የማይነጥፍ ድጋፍ ባልተጠበቀ ፍጥነት እንዲያገኝ ሲያደርግ የወያኔንና የመሰሎችን ጎራ ናዳ ልኮባቸዋል። በተለይም በክፍፍልና በፍርሃት ተሸብቦ የነበረው ውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ከወትሮው በተለዬ ዘላቂ ለሆነ ትግል ራሱን ማዘጋጀቱን በተለያዩ እንቅስቃሴዎቹ እያሳየ ሲሆን አገር ውስጥ በሰላማዊ ትግል ይሳተፉ የነበሩ በርካታ ወጣቶች ቁጭ ብሎ ከመታሰር በርሃ እያቆራረጡ ወደትግሉ መቀላቀላቸውና ሌላውም ህዝብ መነሳሳትን ማሳየቱን ወያኔዎችም ሊደብቁት አልተቻላቸውም።Andargachew Tsege and his friends
አንዳርጋቸው የህይወት ተልዕኮውን በሚገባ ተወጥቷል። የግንቦት ሰባትን መሰረት ጥሏል። ከሌሎች ጋር ተባብሮ የመስራትን በር ከፍቷል። ከሁሉም በላይ የአንድ መሪ ሥራና ተልዕኮ አርዐያ መሆን ነውና በድፍረት በትግሉ ወላፈን ውስጥ ራሱን ማግዶ በማሳየቱ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን አነቃንቋል። ጠላቶቹም ሳይቀሩ ሊያከብሩት ያስገደደ ድርጊት ሆኗል። ዛሬ ወያኔ መጨበጫ አጥቶ እንደሚጨነቅ ሰሞኑን ቴዎድሮስ አድሃኖምን ማዳመጡ ብቻ በቂ ነው። አንዳርጋቸው በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ወያኔን የሚያውቅ ሁሉ ይረዳዋል። አንዳርጋቸው ችቦውን ለኩሶ ለተከታዩ ትውልድ አስተላልፏል።

ሰበር ዜና (Breaking News) “አንገነጠልም – ትግላችን የኦሮሞ ሕዝብ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ነው” – ብ/ ጀነራል ኃይሉ ጎንፋ ከአስመራ (የሚደመጥ)

ከሁለት ሳምንት በፊት አራት የኦነግ ድርጅቶች ወደ አንድ መምጣታቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል:: ይህን ተከትሎ ከአውስትራሊያ የሚሰራጨው ሲቢኤስ ራድዮ ብ/ጄ ኃይሉ ጎንፋ፤ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር – ኦነግ (በአባ ነጋ ጃራ የሚመራው) ምክትል ሊቀ መንበር፤ ስለ ኦነግ ዳግም መሰባሰብ አነጋግሯቸዋል:: ጄነራሉ ተበታትነን ምንም አናመጣም ብለዋል:: “ኦነግ የሚለውን ስያሜ በባለቤትነት እኔ ነኝ ብሎ የሚወስደው ማን ነው?” ለሚለው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል:: ያድምጡት::
General

Saturday, August 15, 2015

በምዕራብ ጎጃም የብአዴን አባላት አርበኞች ግንቦት 7 ውስጣችን ሰርጎ ገብቷል በሚል እርስበርስ እየተወነጃጀሉ መሆኑ ተሰማ * ክፍፍሉንም አባብሶታል

በምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራሮች መካከል መከፋፈል ተፈጠረ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው የምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራርና አባላት ከሀምሌ 29 እስከ ነሀሴ 1 2007 ዓ.ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ነው መከፋፈሉ ሊከስት የቻለው፡፡ የምዕራብ ጎጃም የብአዴን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሀብታሙ፣ የዞኑ ምክትል ከንቲባ አስፋው ገበየሁና የወረዳው የብአዴን ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አላምር ተሻለ የተባሉ የህወሓት አገልጋይ የመሩት በዱላ ቀረሽ ስድድብ፣ እርስበርስ መወነጃጀልና የተደበቀ ገመናን በመነስነስ ታጅቦ ለሦስት ቀናት የዘለቀው ስብሰባ ከመነሻው በዋናነት ለውይይት ያቀረባቸው አርበኞች ግንቦት 7 ባወጀው ጦርነት ላይ ተመስርቶ በሽበርተኝነት ላይ የሚያጠነጥን አንድ ሃሳብና የብአዴንን 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበርን የሚመለከት ሌላ ተጨማሪ እርዕስ ያነገበ ሁለት አብይ አጀንዳዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ስብሰባው የታቀደለትን አቅጣጫ ስቶ ፈር በመልቀቅ አባላትና የበታች የብአዴን አመራሮች ከአንድ ላይ በማበር በበላይ አመራሮቻቸው ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያነሱ የበላይ አመራሮች ደግሞ በፌደራል መንግስቱ በሚገኙ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ላይ ጣታቸውን ቀስረዋል፡

እየተቃወሙ ለመኖር…!

የአርበኞች ግንቦት 7 ቃልን ወደ ተግባር የማሸጋገር እንቅስቅሴ ያሸበረው ወያኔን ብቻ አለመሆኑን ከተቃውሞው ጎራ ከሚሰማው የተቀዋሚ ተቀዋሚዎች ጩኸት እያየን ነው፡፡ ርጥቡ ሬሳ ደረቅ ያስነሳ አንዲሉ ይህ ሰሞነኛ ጩኸት የተረሳ እንዲታወስ የተተወ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኖ የአንዳንዶቹ ጯሂዎች የትናንት ማንነት ድብቅ ዓላማና ፍላጎት ጭምር ጸሀይ እንዲሞቀው እየተደረገ ነው፡፡ የማለባባስ አጉል ባህላችንን ተራምደው የይሉኝታ ገመዳችንን በጥሰው ስም እየጠቀሱ መረጃና ማስረጃ እያጠቀሱ አካፋን አካፋ ለማለት ለደፈሩ ወገኖቼ ያለኝን አክብሮት እገልጻለሁ፡፡ እያለባበስን አርባ አመት አልቅሰናልና በቃ ማለት ይኖርብናል፡፡The Patriotic Ginbot 7 attacks factors
አደባባይ ወጥተው የሚጮኹትም ሆኑ ከኋላ ሆነው የሚገፉት የየግል ፍላጎታቸውም ሆነ አንድ የሚያደርጋቸው ምክንያት ምንነትና አንዴትነት በተለያዩ ሰዎች ተጽፋል፡፡ እውነት ናቸውና መስማማቴን እየገለጽሁ ያልተገለጸ የመሰለኝን ልጨምር፡
ስማቸው ብዙ ነው (ፖለቲከኛ ፣ጋዜጠኛ፣ነጻ ማህበር፣ወዘተ) መገኛቸው ሀገር ውስጥም ውጪም ነው፤ዓላማቸው ቢችሉ ምን-ይልክ ቤተ መንግሥት መታየት ካልሆነም በተቀዋሚነት ካባ አንድም ክብር ሁለትም ብር እያገኙ መኖር ነው፡፡ ተባብሮ መስራት አይሆንላቸውም፡ እነርሱ የሚመሩት ወይንም በቀጥታም ሆነ በተዘዋወዋሪ የሚቆጣጠሩት ካልሆነ በስተቀር ማናቸውም ትግል (ሰላማዊውም የጠብ-መንጃውም) አንድ ርምጃ ሲራመድ ማየት አይፈልጉም፡፡
ሲያልሙት የኖሩትን ሥልጣን ለማግኘት የሚቻለው ደግሞ አንድም በምርጫ አንድም በጡንቻ ነው፡፡እነርሱ በሁለቱም መንገድ ለመሄድ አይችሉም፡፡(አንዳንዶቹ ሁሉን ሞክረው የከሸፈባቸው ናቸው፡፡) የምርጫው ነገር እንኳን ለእነርሱ ፓርቲ መስርተው በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው መቀመጫቸውን ሀገር ቤት አድርገው ለሚፍጨረጨሩትም አልተሳካም፡፡ ሀገር ቤት በሚገኙ ተቀዋሚዎች ተከልለው ያደረጉት ሙከራም አልተሳካም፡፡ ( የኢትዮጵያ ዴሞክራሲዊ ኃይሎች ህብረት ይጠቀሳል) የጡንቻውን መንገድ ቢያልሙትም አልሆነላቸውም፤ አይሆንላቸውም፡፡ ከሌሎች ጋር ተባብረው በተቀዋሚነት ተከብረው ለመኖር፤ ከተቻለም ተከልለውም ቢሆን ወደ ምኒልክ ቤተ መንግሥት ለመድረስ መከጀላቸው ባይቀርም መሪነቱን እነርሱ ካልያዙት ወይንም እንቅስቃሴው በቀዳሚነት የእነርሱን ዓላማና ፍላጎት የሚያሳካ ካልሆነ በጅ አይሉምና፡ በዚህም መንገድ ስንዝር መራመድ አልቻሉም፤አይችሉምም፡፡
ስለሆነም ያላቸው ምርጫ ላለፉት ሀያ አመታት ሲተገብሩትም ያየነው ተቀዋሚ እየተባሉ መኖር ነውና በሰላማዊ ትግል በተአምር፣ ወይንም በተቃራኒው መንገድ በጦር የወያኔ ሥልጣን ቢቀየር ይህን ስለማያገኙ ጠንከር ያለ እንቅስቃሴ ሲጀመር ፈጥነው ይዘምቱበታል፡መገንባቱን ሳይሆን ማፍረሱን፣ ማቀራረቡን ሳይሆን ማለያየቱን፤ መደገፉን ሳይሆን ማደናቀፉን የተካኑበት ናቸውና እስካሁን በአብዛኛው ተሳክቶላቸዋል፡፡ ዛሬ ግን ተነቅቶባቸዋልና ድብቅ ማንነታቸውን ያጋልጡ፣ ቀሪ ህይወታቸውን ያበላሹ ለልጆቻቸው መጥፎ ስም ያቆዩ እንደሁ አንጂ የሚሳካላቸው አይመስለኝም፡፡
ፊሺካው ተነፍቷል ጦርነቱ ተጀምሯል በተባለበት ማግስት በፍጥነት ተጠራርተው ከጀመሩት ጫጫታ ውስጥ አንዳችም መፍትሄ ጠቋሚ ሀሳብ አለመኖሩ ከመነሻው በተቃውሞው ሰፈር ይገኙ እንጂ ለውጥ ናፋቂ ሳይሆኑ ወሬ አሟሟቂ፤ የተግባር ሳይሆን የምላስና የብዕር ታጋዮች መሆናቸውን የመሰከረ ነው፡፡ ትናትም ሆነ ዛሬ ሰላማዊውንም ሆነ የጠብ-መንጃውን ትግል የሚቃወሙት ተቀዋሚ እየተባሉ ሆነው ሳይሆን እያስመሰሉ፣ እየታገሉ ሳይሆን እያውደለደሉ ክብርም ብርም የሚያገኙበት ሜዳ እንዳያጡ በመስጋት ነው፡፡ ግን ለምን? እነርሱ በተቃዋሚነት እንዲኖሩ የወያኔ እድሜ መርዘም አለበት? የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንባ ገነን አገዛዝ ውስጥ መኖር አለበት ?ከእነርሱ ፍላጎትና ከሀገር ነጻነት የቱ ይበልጣል?፤የቱ ይቀድማል፡? በእውነቱ አሳፋሪም በታሪክና በትውልድ የሚያስጠይቅም እኩይ ተግባር ነው፡፡
ይህ አድራጎት ዛሬ የተጀመረ አይደለም፤ እንደውም ከአንዳንዶቹ ጋር አብሮ ያረጀ ነው፤ ትንሽ የቅርብ ግዜ ማሳያዎችን አንመልከት፡
ማሳያ አንድ፤ በ1992 ዓም ኢዴፓ የሚባል ፓርቲ ተመስርቶ በአጭር ግዜ ሰፊ እንቅስቃሴ አደረገና እውቅና አገኘ፤ በዚህ መልኩ እየገነነ ከቀጠለ በግልም ሆነ በድርጅት እስከመኖራቸውም እንዳይረሱ የሰጉት እነዚህ የወያኔም የተቀዋሚውም ተቀዋሚዎች የለመዱትንና የተካኑበትን የማደናቀፍ ዘመቻቸውን ከፈቱበት፤ የፓርቲው አመራሮች ቢቸግራቸው በእነዚህ ሰዎች በተወጠነውና በምድረ አሜሪካ በተዘጋጀ ጉባኤ ተካፋይ ሆነው የኢዴኃህ አባል ሆኑ፡፡ ሊቀመንበሩ ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ የህብረቱ ዋና ጸኃፊ ለመሆን ቢበቁም ከመነሻው የተገባው በእምነት ሳይሆን የሰዎቹን አፍራሽ ዘመቻ በመፍራት ነበርና ብዙም ሳይቆይ ፓርቲው ከህብረቱ ወጣ፣ መኢአድ ለጉባኤ የላካቸው አባላቱ ሀገር ቤት ሳይመለሱ ነበር ጉባኤው በእነዚህ ሰዎች ሴራ መጠለፉን ገልጾ የጉባኤውን ሂደት በመቃወም ጥያቄ አቅርቦ፤ጥያቄው ካልተመለሰ እንደማይቀጥል ያስታወቀው፡፡ ኢዴኃህም የቡና ውሀ ሆነ፡፡ (በምርጫ 97 የሰሩትም የሚረሳ አይደለም፡፡)
ማሳያ ሁለት፤ ቅንጅት ሲመሰረት መሪነቱን እንያዝ እንዳይሉ ከመስፈርቱ አንዱ በሀገር ቤት ያሉ የሚል በመሆኑ፣ እነርሱ ደግሞ አብዛኛዎቹ ከሀገር ውጪ ስለሚኖሩና ሀገር ቤት ፓርቲ ስለሌላቸው አልተቻላቸውም፤ በእጅ አዙር አንዳይቆጣ ጠሩት ከቅንጅት የወቅቱ ጥንካሬ አንጻር ለዛ የሚያበቃ አቅም አልነበራቸውም፡፡ እናም በሚያውቁት በለመዱትና በተካኑበት ስልትና መንገድ ብዙ ዘመቱበት፤ ወዳጅ መስለው በመቅረብ መጥፎ እየመከሩ አቅጣጫ ለማሳት፣ በአመራሩ መካከል መጠራጠር ለመፍጠር ብሎም ቅንጅትን ከመረጠው ሕዝብ ለማጣላት ከውጪም በሀገር ውስጥም በመልእክተኞቻቸው በኩል ብዙ ሰርተዋል፡፡ የቅንጅት አመራሮች ለፓርላማ ሳይሆን ለወህኒ ሲዳረጉም ተደስተዋል፡፡
ማሳያ ሶስት፤ የቅንጅት አመራሮች ከእስር ከወጡ በኋላ የፈጠሩት አለመግባባት እስከ መለያየት እንዲያደርሳቸው ከሁለቱም ወገን ደጋፊ መስለው በመሰለፍ የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል አይነት የተጫወቱት አፍራሽ ሚና ቀላል አይደለም፡፡ ይህን ለማረጋገጥ በወቅቱ በዌብ ሳይቶች በጋዜጦችና በማህበራዊ ድረ-ገጾች ወዘተ ላይ የተጻፉትን ማየት በየፓልቶኩ በያራዲዮው የተነገሩትን ማደመጥ በቂ ነው፡፡
ማሳያ አራት፤ የቅንጅት ከፊሉ ወገን ተሰባስቦ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ሊቀመንበሩ አድርጎ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ የተሰኘ ፓርቲ መስርቶ በአጭር ግዜ በሀገር ውስጥም ሆነ አውሮፓና አሜሪካ ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የተበለጥን ሰይጣናዊ ስሜታቸው አገርሽቶ የከፈቱት ዘመቻም የሚረሳ አይመስለኝም፡፡(በአብዛኛው የሚዘምቱት ሀገራዊ ድርጅት ላይ ነው)
አንድነት የቅንጅት ወራሽ መሆኑና ( ቅንጅት የሚለው ስምና ሁለት ጣት ምልክት ወያኔዎችን ያባንናቸዋል)ከጅምሩ ያገኘው ተቀባይነት ያሰጋው ወያኔ ወ/ት ብርቱካንን ዳግም ሲያስር ለእነዚህ ሰዎች ፌሽታ ነበር፡፡አጋጣሚውን በመጠቀምም ቀሪዎቹን አመራሮች ከቅርብም ከሩቅም ወዳጅ መስለው በመቅረብ በምክርም በገንዘብም በሌላ ሌላውም ከወዲያ ወዲህ እያላጉ የት ይደርሳል የተባለውን አንድነት ሽባ አደረጉት፡፡ የእነርሱም የወያኔም ሴራ ተደማምሮ አንድነት አምስት አመት ሙሉ ታሞ በምርጫ 2007 ዋዜማ ግብአተ መሬቱ ተፈጸመ፡፡ እናቃብራችሁ አንኳን አላሉም፡፡
ማሳያ አምስት፤ ሰማያዊ – ይህኛውም ፓርቲ በ2004 ዓም ተመስርቶ በአጭር ግዜ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ለስድስት አመት የተዘጋን የሰላማዊ ሰልፍ ክልከላ በር አስከፈተ ተብሎ ስሙ ሲናኝ የሌላው መግነን የእኛን መኮስመን ያስከትላል የሚል ከይሲ አስተሳሰብ ያላቸው እነዚህ ወገኖች ዘመቻ የጀመሩት ከመቅጽበት ነው፡፡
ይሉት ቢያጡ ሰበብ ቢቸግራቸው ከሌሎች ጋር ተባብሮ መስራት አለበት ብቻውን የትም አይደርስም አሉ፡፡ አልተሳካላቸውም እንጂ ይህን ሰበብ አድርገው በፓርቲው ውስጥ ክፍፍል እስከመፍጠር ደርሰውም እንደነበር ይታወቃል፡፡ሌላም ሌላም መጥቀስ ይቻላል፡፡አንድ ፓርቲ ጠንክሮ እንዳይወጣ ወይንም ፓርቲዎች ተባብረው በግንባርም ይሁን በውህደት ጠንክረው እንዳይታገሉ ካደረጉዋቸው ምክንያቶች አንዱ የእነዚህ ወገኖች ሴራ ነው፡፤
እነሆ አሁን ደግሞ የተለመደውንና መታወቂያቸው የሆነውን አፍራሽ ተግባር ጀመሩ፡፡ የኢሳይያስ ማንነትና የሻዕቢያ ምንነት የታያቸው ዛሬ ነው ? ጅብን ሲወጉ በአህያ ተከልሎ እንደሚባለው ይህ ሰበብ ነው፡፡ ዋና አላማው ኢሳይያስንና ሻዕቢያን ከለላ አድርጎ በነጻነት ትግሉና ታጋዮቹ ላይ መዝመት ነው፡፡
ተቃውሞአቸው ምንድን ነው፡፡
የሚያነሱት ነገር ለክርክር እንዳይቀርብ ለመለስ ምትም አንዳይመች ተቃውሞአቸው ስልታዊ መንገዳቸው የጎንዮሽ ነው፡፡የሚደግፉትም ሆነ የሚቃወሙት ነገር በግልጽ አይታወቅም፤ ዛሬ ያመሰገኑትን ነገ ይኮንኑታል፤ባከበሩ ማግስት ያዋርዳሉ፤ የእነርሱ የሆነ ሁሉ ቅዱስ በተቃራኒ የቆመ ወይም ለእነርሱ ያልተመቸ ሁሉ ርኩስ ነው፡፡ እነርሱ ሞክረውት አላስኬድ ባላቸው መንገድ ሌሎች መሄድ ከቻሉ በቅናት ያራሉ፡ እነርሱ ሊወዳጁት ያልቻሉትን ሰው ወይንም ድርጅት ሌሎች መወዳጀት ከቻሉ የውግዘት ናዳ ያወረዳሉ፤ እነርሱ ሞክረውት ያቃታቸውን ሌሎች ለማሳካት ከጀመሩ የማጥላላት ጥሩንባ ይነፋሉ፤ በታላቁ መጽኃፍ ትንቢተ ኢሳይያስ ም፣48 ቁ.22 ላይ “ክፉዎች ሰላም የላቸውም” ተብሎ እንደተጻፈው በክፋታቸው ለራሳቸው ሰላም አጥተው ሌላውንም ሰላም ያሳጣሉ፡፡
የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ተብሎ አንዳይተው፣ ዓላማችን ላሉት ስኬት አስበው ወቅት ጠብቀው የሚሰሩ መሆናቸውን አይተናል እያየንም ነው ፡፡ የተለመደ ተግባራቸው ነው ተብሎ ተንቆ አንዳይተው ብእራቸውም ሆነ ምላሳቸው የሚረጨው መርዝ ለትግሉ ውጤታማነት ሆነ ከድል በኋላ ለሚፈለገው መረጋጋት ብሎም ለኢትዮጵያውን አንድነት ጠንቅ ነው፡፡ መፍትሄው አላማችሁ ገብቶናል በቃችሁ ማለት መቻል ነው፡፡ይሄ ካልበገራቸውም ማንነታቸውን ጸሀይ ማሞቅ፡፡

በአዳማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ የኦሮሞ ዲያስፖራ አባላት የመንግስት ባለስልጣናትን በጥያቄ አጨናነቁ

Opdo
(ራዲዮ ዳንዲ ሃቃ ማክሰኞ ሐምሌ 5/ 2007) ስብሰባው ከአርባ ሰባት ሃገራት የተሰባሰቡ የኦሮሞ የዲያስፖራ አባላትን የአርባ ሰባቱ ሃገሮች ዲፕሎማቶች በተገኙበት ተካሂዷል ። መንግስት የኦሮሞ ዲያስፖራ ሳምንት ብሎ የሰየመውን ሳምንት በማስመልከት: ከመላው አለም ያሰባሰባቸውን የኦሮሚያ ዲያስፖራ አባላት: በሚሊኒየም አዳራሽ ጠቅላይ ሚስትሩ በተገኙበት ደማቅ የአቀባበል ስነ ስርዓት ካደረገላቸውና : ለሶስት ቀናት ያክል ሃገሪቷን ካስጎበኛቸው በኃላ : በአዳማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ በመሰብሰብ : የተለመደ ፕሮፓጋንዳውን ለመንዛት ቢሞክርም: ከኦሮሚያ የዲያስፖራ አባላት ፍፁም ያልጠበቀው :የጥያቄ ውርጅብኝ ዘንቦበታል ። ስብስባውን የመሩት አቶ አባዱላ ገመዳ አቶ ሙክታር ኸድር እና ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ሲሆኑ : ከኦሮሞ ዲያስፖራ አባላት የተነሱት ጥያቄዎች በአራት ነገሮች ላይ ያጠነጠኑ እንደነበሩና እነሱ :– 1)የሙስሊሙ ህብረተሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴን የፍርድ ሂደት በተመለከተ 2) የጋዜጠኞችን መታሰር ጉዳይ በተመለከተ 3) የኦሮሞ ተማሪዎችና ወጣቶች መታሰርን በተመለከተና 4) የመሬት ማስተር ፕላኑንና በተመለከተና በማስተር ፕላን ሰበብ ህዝብ ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ እንደነበር ምንጮቻችን አያይዘው ገልፀዋል። በተለይም የሙስሊሙ ህብረተሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጉዳይ ከዲያስፖራው አባላት ሲነሳ : የተሳታፊዎቹ ስሜት ፍፁም ልዩ እንደነበርና: እያንዳንዱ እነሱን በሚመለከት የሚነሳ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር : ከኃላው ከፍተኛ ጭብጨባ ይከተለው እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል ።

Wednesday, July 22, 2015

የፕ/ር ብርሃኑ አስመራ ከገቡ ጀምሮ፣ በአገር ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ኢሳት ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ

የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ "ለነጻነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል መሬት ላይ ወርዶ መምራት ይገባል" በሚል እምነት በከፍተኛ ውጣ ውረድ ከአሜሪካ ኤርትራ መግባታቸው እንደተሰማ በአርበኞች ግንቦት7 ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ፣ አስመራ በሚገኘው የድርጅቱ ጽህፈት ቤት አቀባበል ያደረጉላቸው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ተናግረዋል።በዋና ጽህፈት ቤቱ የሚሰሩ የፖለቲካ እና የውጭ ግንኙነት ክፍል አባላት ለፕሮፌሰሩ በጋራ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የገለጸው ሻለቃ አክሊሉ፣ ከአባላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በሰራዊቱ ውስጥ የታየው መነቃቃት ለነጻነት የሚደረገው ትግል እንዲፋጠን፣ በተለይም ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የሚደረገውን ተቀራርቦ የመስራት ድርድር እንዲፋጠን እንደሚያደርገው ሳለቃ አክሊሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል። ፕ/ር ብርሃኑ አስመራ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የኤርትራ ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል። የፕ/ር ብርሃኑ አስመራ መድረስ ዜና ይፋ ከሆነ ጀምሮ፣ በአገር ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ኢሳት ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። አርበኞች ግንቦት7ትን ለመቀላቀል የሚጠይቀው ህዝብ እየጨመረ መምጣቱንም ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ፕ/ር ብርሃኑ ግንቦት7ትን በሊቀመንበርነት ሲመሩ ቆይተው ፣ አርበኞች ግንቦት7 ውህደት ከፈጸሙ በሁዋላ የውህዱ ድርጅት ሊቀመንበር ሆነዋል። በውህደቱ ላይ ለመገኘት የነበራቸው ውጥን ከጉዞ ሰነድ ጋር በተያያዘ ባለመሳካቱ፣ ለመሪነት የተመረጡት በሌሉበት ነው። ይሁን እንጅ በውህደቱ ወቅት ለጉባኤተኛው በስልክ ባስተላለፉት መልክት፣ አንዳንድ ችግሮች ተፈተው በቅርቡ በረሃ ወርደው እንደሚቀላቀሉዋቸው ቃል ገብተው ነበር። በምርጫ 97 በተደረገው ምርጫ አሸንፈው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ብርሃኑ፣ ምርጫውን ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ ከሁለት አመት ላለነሰ ጊዜ በእስር ቤት አሳልፈዋል። ከዚያም አሜሪካ በሚገኘው በክኔል ዩኒቨርስቲ በመምህርነት ሲያገለግሉ ቆይተው ከወራት በፊት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማእረግ አግኝተዋል።

ሊቀመንበራችን ትግል ሜዳ ውስጥ ነው!- መግለጫ

ሐምሌ 12 2007 ዓ.ም.
ህወሓት በኢትዮጵያዊያን እና በኢትዮጵያ ላይ ያሰፈነው ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ እንዲያበቃ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈኑበት የፓለቲካና የኢኮኖሚ ሥርዓት እንዲመሠረት እና የሀገራችን አንድነት በጠንካራ መሠረት ላይ ለማኖር አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ተገዶ የገባበት የመረረ የአመጽ ትግል መጀመሩን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በጀግነትና በጽናት እየታገሉ ነው።
ይህ ትግል በባርነትና በነፃነት መካከል የሚደረግ ወሳኝ ትግል ነው። የዚህ ትግል ውጤት የእኛ የዚህ ዘመን ትውልድ ሕይወት ብቻ ሳይሆን የአገራችንን የወደፊት ታሪክ፤ የልጅ ልጆቻችንን ሕይወት ይወስናል። በዚህም ምክንያት ይህንን ትግል በድል መወጣት ግዴታችን ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት ለነፃነት ግድ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከጎናችን ሊቆም ይገባል።

Saturday, June 27, 2015

ሳሙኤል አወቀ በኢህአዴግ ከመገደሉ በፊት እንዲህ ብሎ ነበር

ሳሙኤል አወቀ እስር፣ ድብደባ፣ ዛቻ እየተደረገበት ወደኋላ ሳይል ሲታገል የቆየ ወጣት ነው፡፡ በርካታ ምሁራን ቤታቸው ቁጭ ባሉበት ይህ ወጣት በድፍረት የምስኪኑን አርሶ አደር ስቃይ በየቀኑ ለሚዲያ ሲያጋልጥ ቆይቷል፡፡
ሳሙኤል አወቀ
ለዚህ ሁሉ ግን በቀል ተፈፅሞበታል፡፡ ለነገዋ ኢትዮጵያ፣ ለነፃነት ያለመው ወጣት በትናንትናው ዕለት ተገድሎ ተገኝቷል፡፡ ይህ ወጣት ከቀናት በፊት ይህን ፅፎ ነበር፡፡
እናስርሃለን፣ እንገድልሃለን!
(የገዥዎቻችን የሥራና የመግባቢያ ቋንቋ)
ሳሙኤል አወቀ
“ሀገሬ፣ ታሪክ፣ ሐይማኖት፣ ባሕልና ሸማግሌዎች አሏት፡፡ ነገር ግን ምነው ትንፍሽ የሚል ጠፋ? በየቀበሌው ጠያቂ የሌለው ጥቃቅን ንጉስ ነግሶብናል:: በደል እና ግፍ ራሳቸው እየፈፀሙ ለራሳቸው እንድንሰግድ የሚያደርግሥርዓት ተበጅቷል:: የቀበሌ ካድሬ የፍርድ ቤት ውሳኔ እንኳን አይገዛውም:: አላምንበትም አልተማከርሁበትም ይላል:: ወደየት ይደረሳል? ለማንስ ይነገራል? ከተመደበለት የቀበሌ ኮሚኒቲ ፖሊስ ጋር አብሮ ያስራል፡፡ ይገርፋል፡፡ ይደበድባል፡፡ ሲፈልግ የሀሠት ምሰክር አደራጅቶ እሰር ቤት ያሰወረውራል፡፡ የህዝብ ሮሮ ለነሱ ሙዚቃ ሆኗል፡፡ ሀይ ባይ፣ ገላጋይ፣ ገሳጭ አሥታራቂ ሽማግሌዎች እና የኃይማኖት መሪዎች በዓለማዊ ሕይወት ሕዝባቸውን ረስተዋል፡፡

7 ኢትዮጵያውያን በደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ ጥገኝነት ጠየቁ

5423b23fcd57d3e20706cba7493baeb2_XLህጋዊ መታወቂያ ወይም የጉዞ ሰነድ አልያዙም ተብሏል
– የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአ/አ ስንነሳ ህጋዊ ሰነድ ነበራቸው ብሏል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየርላንድ ርዕሰ መዲና ደብሊን በኩል ወደ አሜሪካ ሎሳንጀለስ የጀመረውን አዲስ በረራ ለማስመረቅ ባለፈው ቅዳሜ ከአዲስ አበባ በመነሳት ባደረገው ጉዞ፣ ተሳታፊ የነበሩ 7 ኢትዮጵያውያን መንገደኞች፣ አውሮፕላኑ ደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ሲያርፍ ወደ ኢሚግሬሽን ክፍሉ አምርተው ጥገኝነት መጠየቃቸውን አይሪሽ ኢንዲፔንደንት ትናንት ዘገበ፡፡ሁለት ህጻናትን ጨምሮ ጥገኝነት የጠየቁት 7 መንገደኞች በአየር ማረፊያ ጣቢያው ሲደርሱ ምንም አይነት መታወቂያ ወይም የጉዞ ሰነዶችን አልያዙም ነበር ያለው ዘገባው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቃል አቀባይ ግን፣ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች በሙሉ ከአዲስ አበባ ሲነሱ ህጋዊ ሰነዶችን ይዘው ነበር፣ ስለ ጥገኝነት ጠያቂዎቹ የግል ጉዳይ ግን አስተያየት መስጠት አንፈልግም ብለዋል፡፡

Thursday, April 2, 2015

የማለዳ ወግ …” ልዩነት መልካም ነገር ነው! ” አንጀሊና * ዘሐራ ጥቁር አልማዝ ሆና ነጯን እናት ስታደምቅ .

ለማፍቀር መፈቀር ፣ ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ግድ ይላል ! ይህ ተፈጥሯዊ ህግ ሆኖ በሁላችንም ላይ ባይሰረጽም የታደሉት ሲሆኑትና ሲታደርጉት ከማየት አልፎ የድካማቸው ፍሬ አፍርቶ ሲያዩት ምስክር እማኝ መሆን መታደል ነው ። መልካም መስራት ለራስ ነው እንዲሉ ውስጥን ከሚሰጠው እርካታ ባሻገር የታደሉት የዘሩት አሽቶ መልካም ስራቸው በስኬት ጎዳና ሲታይና በውጤት ስኬቱ ሲደምቁ ማየት ከምንም በላይ ያስደስታል ። በአንጻሩ መልካም ሰርተው እጃቸው ” አመድ አፋሽ ” የሆኑንም አለማችን ከማስተናገድ አልቦዘነችም ። የአማድ አፋሽነቱ ህመም ጥልቆ ቢያመም የሰሩት ለውስጥ እርካታ ነውና ሁሉምም የሚያየው አንድ ፈጣሪ ፍርድ ይሰጣልና ህመሙ ህመም አይባልም ። አድርጎ “አመድ አፋሽ ” መሆን ክሽፈት ነው ከተባለ ምድራዊ ጊዜያዊ ክሽፈትነት ፈቀቅ አይልም ፣ የመልካምነት ሰማያዊ ጸጋቸው ሰፊ ነውና እኒህም የታደሉ ናቸው !

አሳዛኝ ዜና በየመን ጦርነት 45 ኢትዮጵያዊያን ሞቱ ከ60 በላይ ቆሰሉ

ሰሞኑን ያለማቋረጥ የመን ላይ እየተወሰደ ባለው የአየር ጥቃት ምክንያት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በከፍተኛ ችግርና ጭንቀት ውስጥ ነበሩ፡፡ ዛሬ በተደረገ የአየር ድብደባ ምክንያት ካምፕ ውስጥ የነበሩ 45 ኢትዮጵያዊን ሲሞቱ ከ60 በላይ ቆስለዋል፡፡ በIOM ካምፕ ላይ በስህተት የተወሰደ እርምጃ ነው በተባለው በዚህ ጥቃት ላይ ካምፕ ውስጥ የነበሩት የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች ናቸው የሞቱት የሚል መግለጫ IOM ቢያወጣም በዛ ካምፕ ውስጥ የሚጠቀሙት ኢትዮጵያዊን መሆናቸው ግን የታወቀ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ሄጄ ካምፑን እንዳየሁት እኔም የማውቀው በጅቡቲ በኩል ወደ የመን የሚገቡ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ብቻ እንደሚያርፉበት ነው፡፡

BREAKING NEWS አንድ ኢትዮጵያዊ እስረኛ ከእስር ቤት በማምለጡ በአሜሪካ ፖሊስ እየተፈለገ ነው


ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ወሰን አሳዬ የተባለ እስረኛ በአሜሪካ ለመታከም ከነበረበት ሆስፒታል በማምለጡ በአሁኑ ሰዓት በሰሜን ቨርጂኒያ ሽብር ተፈጥሯል በርካታ ፓሊሶች እንዲሁም የስዋት(SWAT) ቡድን ሀይል በቦታ እያፈላለጉት ይገኛሉ።

አሳዛኙ የተገን ጠያቂዎች ይዞታ በፈረንሳይ

በአሁኑ ጊዜ ህገ ወጥ በሚባል መንገድ በአደገኛ ጉዞ አውሮፓ የሚደርሱ ስደተኞች በሙሉ አውሮፓን እንደጠበቋት ሆና አያገኟትም ።ከሞት ተርፈው ምድሪቱን ለመርገጥ ከበቁት መካከል ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው አስከፊ ህይወት የሚገፉ ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ።
ህይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚሞክሩ በርካታ አፍሪቃውያን ስደተኞች ካስቡበት ሳይደርሱ የበረሃና የውሐ ሲሳይ መሆናቸው ተደጋግሞ የሚነገር ጉዳይ ነው ። ከመካከላቸው እድል የቀናቸው ደግሞ በህይወት አውሮፓ መድረስ ቢችሉም እዚህም የሚጠብቃቸው አበሳ ቀላል የሚባል አይደለም ። የጥገኝነት ጥያቄ ማመልከቻቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ለዓመታት የሚንገላቱ ከዚያም አልፎ በደረሱበት ሃገር ማረፊያም ይሁን ምግብ ለማግኘት የሚቸገሩ የጎዳና ተዳዳሪ ሆነው ህይወታቸውን የሚገፋም ጥቂት አይባሉም ። በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ መውጫ ላይ በሚገኝ ባቡር ጣቢያ ስር ተጠልለው የሚኖሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች ለዚህ አብነት ናቸው ።

አንድነት ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ላይ ያቀረበው ክስ ውድቅ ሆነ

ፍትህ መረገጡን ባደባባይ አስመስክረናል፤ሃላፊነታችንንም ተወተናል!! ተክሌ በከለ
ለኔ እዉነተኛዉ የአንድነት ፓርቲ ትናንት በፍ/ቤት ዉሳኔ ተቀብሯል፡፡ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል እንደሆን ቀድም ሲል አዉቀናል፡፡ዳኛ ብርቱኳንም ፍርህይወትም ዳግም አልተከሰቱም፡፡እንደ ኢህአዴጉ የምርጫ ዉጤት 99.6 ከመቶዉ አመራሩና አባላቱ በምርጫ ቦርድ እንዲበተኑ የተበየነበት እንዲሁም በደጋፊዎች የተገዛ ንብረት ያለፍ/ቤት ትእዛዝ በመንግስት ታጣቂ ፖሊሶች የተዘረፈበት አንድነት የፍትህ ተቋሙን ለመፈተሸ ም/ቦርዱን መክሰሱ ይታወቃል፡፡
ም/ቦርድን መክሰሳችን አግባብ እንዳልሆነ አንቀጽ ተጠቅሶ ከማስፈራሪያ ጋር ክሱ ዉድቅ ተደርጓል፡፡ መፍትህ መረገጡን ባደባባይ አስመስክረናል፤ሃላፊነታችንንም ተወተናል፡፡ቀጣዩን በቀጣይ ሂደት የምናየዉ ይሆናል፤እንደሚፈልጉት ተበትነን አንቀርም፡፡አንድነቶች በያለንበት እንረጋጋ!!

ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ የቴድሮስ አድሃኖም ዋና አማካሪ የሃሰት ፕሮፌሰር እደሆኑ አበበ ገላው አጋለጠ

አዲስ ቮይስ– የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤትና የሚኒስትሩ ዋና አማካሪ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናትና ትንተና የበላይ ሃላፊ የሆኑት “ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ የሃሰት ፕሮፌሰር እደሆኑ አዲስ ቮይስ ባካሄደው እረዘም ያለ ምርመራ ማረጋገጥ ችሏል።። ግለሰቡ ለ15 አመታት በፕሮፌሰርነት አገልግየዋለሁ የሚሉት አንድ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ እንደማያውቃቸው የገለጸ ሲሆን የዶክትሬት ዲግሪ ያገኙበት ተቋምም በአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት “የዲፕሎማ ወፍጮ” (diploma mill) ተብሎ የተፈረጀ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

“ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ ከኦክቶበር 2010 ጀምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋና አማካሪ ሆነው በመንግስት የተሾሙ ሲሆን አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩ ወቅት ዋና አማካሪያቸው ሆነው ያገለገሉት እኚሁ ግለሰብ በአሁኑ ግዜ የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ዋና አማካሪ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናትና ትንተና ክፍል የበላይ ሃላፈ ሆነው በመስራት ላይ ይገኛሉ።

Wednesday, March 18, 2015

አርበኞች ግንቦት7 – በህወሓት ላይ የሚቀርቡ ተቃውሞዎች ሁሉ ወደ እምቢተኝነት ይደጉ!

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracyየኢትዮጵያ ሕዝብ በአለፉት 23 ዓመታት በህወሓት ዘረኛ አገዛዝ የደረሰበት ስቃይ እንዲቀንስ፤ ገዢዎቹ ከጫንቃው እንዲወዱ፤ ህወሓትን አውርዶ የሚፈልጋቸው መሪዎችን በነፃነት እንዲመርጥ ሲጠይቅና አቤቱታ ሲያሰማ ቆይቷል። በ1997 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሕዝብ ምኞት የሚሳካ መስሎ የታየ የነበረ ቢሆንም በአገዛዙ አረመኔዓዊ እርምጃ ተሰናክሏል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ “ድምፃችን ይሰማ” የሚሉ አቤታዎች ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መምጣት ጀምሯል – “ድምፃችን ይሰማ ሙስሊሞች”፣ “ድምፃችን ይሰማ ኦርቶዶክሶች”፣ “ድምፃችን ይሰማ መምህራን”፣ “ድምፃችን ይሰማ ተማሪዎች”፣ … ወዘተ። በተለይ ሙስሊም ወገኖቻችን በተደራጀ መንገድ “ድምፃችን ይሰማ” እያሉ ሲወተውቱ ሦስት ተከታታይ ዓመታት አልፈዋል። ወገኖቻችን “ድምፃችን ይሰማ” በማለታቸው ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገድለዋል።
አቤቱታ የሚሰማ ጆሮ የሌለው አገዛዝ ሲገጥም ምን ይደረጋል? ለአቤቱታ አቅራቢው ያለው ምርጫ ከሁለት አንድ ነው። ወይ አቤቱታን እርግፍ አድርጎ ጥሎ በደልን ተቀብሎ “እህህ !” እያሉ መኖር፤ አሊያም “በቃኝ፣ እንቢ አልገዛም” ማለት፤ ሦስተኛ ምርጫ የለም።

የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት በአሜሪካ የደረሰባቸው ተቃውሞ በጠ/ሚ ሃይለማርያም፣ ጌታቸውን አሰፋ፣ ኢሳትና ሌሎች ሃይሎች የተቀነባበረ ነው አሉ

imagesየሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት በአሜሪካ የደረሰባቸው ተቃውሞ በጠ/ሚ ሃይለማርያም፣ ጌታቸውን አሰፋ፣ ኢሳትና ሌሎች ሃይሎች የተቀነባበረ ነው አሉ
መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በአንድ ኢትዮጵያዊ ከፍተኛ ተቃውሞ ያገጠማቸው አቶ አብዲ ሙሃመድ ተቃውሞውን ያቀነባበሩት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ የደህንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ፣ ኢሳት ፣ ግንቦት7 እና የኤራትራ መንግስት በጋራ በመሆን ነው ሲሉ አካራ ኒውስ በተባለው የግል ዌብሳይታቸው ላይ በሶማልኛ ባወጡት ረጅም ጽሁፍ ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ ተቃውሞውን ሲያሰማ የነበረውን መኮንን የተባለውን ሰው ስም ከፊት በማስቀደም፣ መኮንን ጌታቸው አሰፋ ሃይለማርያም ብለው ጽሁፋቸውን ይጀምሩና ኢሳት ከጀርባ ሆኖ ሲያቀናብር እንደነበር ያትታሉ።

መድረክ ከምርጫ ጋር በተያያዘ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ዘርዝሮ አቀረበ

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ ክልሎችን የሚሸፍነው ሪፖርት፣ በዜጎች ላይ የተፈጸሙ ዝርዝር ጥቃቶችን አቅርቧል።  በትግራይ ክልል በአጽቢወንበርታ ምርጫ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመድረክ ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት አቶ ወ/ገብርኤል ኃይሉ የዕጩነት መታወቂያ እንደያዙ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ የአስር ወራት የእስራት ቅጣት ተፈርዶባቸዋል፡፡
 “በቆላ ተንቤን ወረዳ በወርቅ አምባ ምርጫ ክልል የክልል ም/ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት አቶ ብርሃን ንጉስ ተክለእግዚም በተመሳሳይ ሁኔታ የዕጩነት መታወቂያቸውን እንደያዙ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ የሶስት ዓመት የእስራት ቅጣት ተፈርዶባቸዋል፡፡”
” ወ/ሮ ቤራይ ገብሩ የሚባሉ በሁመራ ምርጫ ክልል የክልል ም/ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ደግሞ ከታሰሩ በኋላ ተፈትተዋል፡፡ የአቶ ወ/ገብርኤል ኃይሉ የእርሻ መሬትም ተነጥቆ የሕወሐት አባላት ለሆኑ ወጣቶች ተሰጥቷል፡፡ “
በሁመራ ምርጫ ክልል የአረና/መድረክ አባል የሆኑት ቄስ ህሉፍ ካህሳይና በቆላ ተንቤን የአረና/መድረክ አባል የሆኑት  አቶ ዜናዊ አስመላሽም በፖሊስ፣ በኢህአዴግ ካድሬዎችና በአከባቢ ሚሊሺያዎች ተደብድበው ለከፍተኛ ጉዳት ተዳርገዋል፡፡

Saturday, March 7, 2015

ተዋቂው ጋዜጠኛ አለምንህ ዋሴ የህዝቡን ትግል ተቀላቀለ !


2_1812

ጋዜጠኛው በኢትዮጵያዊነቱ አያሌ በደሎች እንደ ተፈጸሙበት ያወጋል ! በተለይ ይላል ጋዚጠኛ አለምነህ ዋሴ ፍትህ እኩልነት በሌለባት ሃገሬ ጋዜጠኛ ርዩት ዓለሙ ላይ የተፈፀመው ኢሰባዊ ድርጊት ከሁሉም በላይ ከህሊናው ሊጠፋ የማይችል ዘግናኝና አረምኔያዊ ድርጊት መሆኑን ይገልጻል ። ጋዜጠኛው ልጆቹን ከማሳደግ ባሻገር ሃገሩ ላይ ሲኖር ደስተኛ እንዳ ልነበረ በመጥቀስ ክእንግዲ አለ ጋዜጠኛ አለምንህ ዋሴ « ፍትህ እኩልነትና ነጻነት እስኪሰፍን » ሃገር አለኝ ብዬ ፊቴን ወደ ኢትዮጵያ አልዞርም ብሏል ። ጋዜጠኛው ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጀት ገለልተኛ ሆኖ ወገኑን ማገልገል እንዳልቻለና የገዢው ስረአት ወሬአቀባይ ሳይሆኑ ገለልተኛ ሆኖ በነጻነት ኢትዮጵያ ውስጥ ሰርቶ መኖር ለህልውና አደገኛ መሆኑን የራሱን ተሞክሮ በመጥቀስ ያብራራል።

Tuesday, March 3, 2015

”ፀረ-የኢትዮጵያ ታሪክነት’ነት ለምን? – ሁኔ አቢሲኒያ

Adwaአንድ ወቅት ሎሬት ጸጋዬ አንድ ስብሰባ ላይ የተጠየቁት ጥያቄ ትዝ ይለኛል። <<ስለ አፄ ቴዎድሮስ ሁል ጊዜ እያሞገሱ ለምን ይጽፋሉ?>> ተብለው ሲጠየቁ <<አይ ሌላውንማ የኢትዮጵያ ጠላቶች ይጽፉታል>> ነበር ያሉት።  ስሞኑን ሎሬት የተነበዩትን በገሃዱ ሕይወታችን እያነበብን ይሆን?
የህወሓት መስራቾች ለትግል በረሃ ከወጡበት ዘመን ምሮ፣ ቂም ቋጥረው ደም የተቃቡት ከደርግ አገዛዝ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሐገሪቱ ታሪክም ጋር እስኪመስል ድረስ በአፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ላይ ተጠምደው እንደነበር ይታወሳል፤ በተለይም ለአፄ ምኒሊክ ስምና ስራ ያላቸው ጥላቻ ወሰን አልባ ነው። የድርጅቱ ‘ማኔፌስቶ’ የተዋቀረበት ጭቃና ማገርም በሐገሪቱ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ቡድን የበላይነት (ጭቆና) መኖሩን አውስቶ የአንድነትና የዘመናዊት ኢትዮጵያ አባት ዳግማዊ ምኒሊክን አንኳሶና አጠልሽቶ አዲስ ታሪክ መፍጠሩ የትላንት ትዝብት ነው።

አየር ሐይልን ከድቶ በይፋ ግንቦት 7ን የተቀላቀለው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ታናሽ ወንድም ሠይፈ መዘነ በማዕከላዊ ቶርች እየተደረገ መሆኑ ታወቀ

“ተዋጊ አውሮፕላኖች የኮንትሮባንድ ማመላለሻ ሆነዋል” በማለት የኢትዮጵያ አየር ሃይልን እና የገዢውን ፓርቲ አካሄድ በመቃወም ግንቦት 7ን መቀላቀላቸው የሚታወሠው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ቤተሠቦች አደጋ ላይ ይገኛሉ፡፡
ኮተቤ 02 አካባቢ በተለምዶ ቆርቆሮ ሠፈር እየተባለ በሚጠራው ስፍራ የሚኖሩት የሻለቃ አክሊሉ ቤተሠቦች ሻለቃ አክሊሉ በተለያዩ ምክንያቶች ግንቦት 7ን መቀላቀላቸውን ተከትሎ በቤተሠቡ ላይ የሚካሄደው ምርመራ እና ክትትል በገዢው ፓርቲ የደህንነት ሀይሎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በተለይም በታናሽ ወንድሙ ሠይፈ መዘነ በማዕከላዊ ቶርች እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጧል፡፡

Wednesday, February 25, 2015

የባቡር ሃዲድ መስመር በሙስና ምክንያት ከደረጃ ውጭ እንዲሆን በመደረጉ የ124 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ደርሷል።

በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ ነው – ሚኒስትሩ

* ከ30 እስከ 40% የግንባታ ወጭ ይዘረፋል!!

የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንገድ ስራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና፣ ከቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን አምነዋል።
የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው ጥናት በባቡር መስመር ግንባታ 2.3 ኪሜ የባቡር ሃዲድ መስመር በሙስና ምክንያት ከደረጃ ውጭ እንዲሆን በመደረጉ የ124 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ደርሷል። የአደጋ መከላከያ ብረቶች የተሰሩት ከወጣላቸው የጥራት ደረጃ በሶስት እጅ ያነሱ ሆነው በመገኘታቸው ጉዳዩ ለቦርድ ሰብሳቢው አርከበ እቁባይ ቢቀርብም ምላሽ ሳይሰጠው በመቅረቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገባ ማወቅ አለመቻሉን ገልጿል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር – ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

የጎረቤት ኬንያ ዳኛ ለኬንያ መንግሥት አስፈጻሚው ክፍል ልኩን ነገረው፤ ሕገ መንግሥቱን በመርፌ አስተኝተህ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ሕግ ለማውጣት አትችልም፤ ስለዚህም የሰነዘርኸውን የጉልበት ሕግ አንሣ፤ አለው፤ ዳኛ አይጥፋ! ሌላ ቢቀር ከጎረቤት ዳኝነትን እንስማ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር ስንት ጋዜጠኛ፣ ስንት የሃይማኖትና ስንት የፖሊቲካ መሪዎች ከየወህኒ ቤቱ ይወጡ ነበር! ሁላችንም እንደልባችን ሳንፈራ፣ ሳንፈራራ በሙሉ ነጻነት ችግሮቻችንን የወያኔን ጭቆና ጨምሮ ለመወያየትና መፍትሔዎችን ለመለዋወጥ የምንችልበት መድረክ፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ራድዮና ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ውስጥ ይኖረን ነበር፤ ስንት ሰው ሥራ ያገኝ ነበር፡፡
ከሁሉም በላይ በየመንገዱ ጠመንጃ የያዘ ሊያስፈራራን የሚሞክር ሆድአደር እያየን፣ እንደዚሁም በየጫካው ያሉትን እያሰብን ሰላማችንን ከምናጣ አበባውን ትተን፣ ሩዙን ትተን፣ የተወደደልንን ጤፋችንን እያመረትን አዲስ ኑሮ ብንጀምር የተሻለ ነበር፡፡
ግን አንድ እንቅፋት አለብን፤ እነዚህ ከየኪዮስኩ እውቀት ገዝተን አዋቂዎች ሆነናል የሚሉት እንትኖች እንመጀመሪያ ችግሩ እንዲገባቸው፣ ሁለተኛ መፍትሔው እንዲገባቸው፣ ሦስተኛ ጉልበትና እውቀት አንድ አለመሆናቸውን ብቻ ሳይሆን በጉልበት እውቀት የማይገኝ መሆኑን ማሳመን በረዶ እየወረደ የስሜን ተራራን መውጣት ነው፤ በረዶ ሳይኖር ወጥቼዋለሁ!

ከሜድትራኒያን ሞት ፊት የቆሙት ስደተኞች

0,,17150593_403,00ባለፈው የጎርጎሮሳውያኑ አመት የሜድትራኒያን ባህርን በጀልባ ለማቋረጥ ከሞከሩ 218,000 ሰዎች መካከል 3,500 መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን አስታውቋል። በዚህ በተመሳሳይ መንገድ ወደ አውሮጳ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች ቁጥር በአሳሳቢ ደረጃ በመጨመር ላይ ነው።
ሰለሞን መንግስቴ በሊቢያዋ የቤንጋዚ ከተማ ባለቤቶቹ ጥለውት የሄዱትን ቤት ይንከባከባል።አትክልት ይኮተኩታል። ግቢውን ያጸዳል። ሰለሞን በቤንጋዚ ብቻውን አይደለም። ባለቤቱ የዝና እዘዘው ቀን ቀን ከሰው ቤት ትሰራለች። ሰለሞን ስለ ወርሃዊ ደሞዙ ሲጠየቅ ፈገግ እያለ «በእውነት መቼ እንደሚከፍሉኝም አላወኩም።» ሲል ይመልሳል።
ሰለሞን ተወልዶ ካደገበት የጎንደር አካባቢ ወደ ሱዳን ገዳሪፍ የተጓዘው ለደላሎች አምስት ሺ የኢትዮጵያ ብር ከፍሎ በአስቸጋሪ የሌሊት ጉዞ ነበር። ጉዞውን ያመቻቹለት የኢትዮጵያ እና የሱዳን ህገ-ወጥ ደላሎች ነበሩ። «ጉዞው የሚጀመረው ለሊት ሰው በሌለበት ሰዓት በእግር ነው። የሚለው ሰለሞን መንገዱ ከሶስት እስከ ሰባት ቀናት ሊወስድ እንደሚችል ይናገራል።

Friday, February 20, 2015

ኢሕአዴግ የሕወሐትን የትግል ታሪክ የኢትዮጵያ ሕዝብ የነጻነት ትግል ታሪክ አካል ለማድረግ መሥራት ይገባዋል! በኒቆዲሞስ

ጽሑፌን በአንድ ገጠመኜ ልጀምር፡፡ በአንድ ወቅት ከጎንደር አገር ገና በአፍላነት ወጣትነት ዘመኗ ወደ ትግል ከገባች ታጋይና ከእናቷ ጋር ለመገናኘትና በአንድ ምሽትም ውይይታቸውን ለማድመጥ ዕድሉ ገጥሞኝ ነበር፡፡ የትግል ዘመኑ በድል ተጠናቆ፣ አገር ተረጋግቶ በነበረበት ሰዓት ልጃቸውን ለመጠየቅና ለሕክምና ከጎንደር የመጡ እኚህ እናት በወታደራዊ ዩኒፎርምና ማዕረግ ተንቆጥቁጣ ከአጠገባቸው ተቀመጠችውን የትናንትናዋን የበረሃ ፋኖ የዛሬዋን ወታደራዊ መኮንን ልጃቸውን በዛች ቅጽበትም ልክ እንደ ልጅነቷ ዘመን ዓይን ዓይኗን በናፍቆትና በስስት እያይዋት እንዲህ አሏት፡-
እንደው ራቴዋ አሁንማ ሥልጣን ስትይዙ፣ ወንበሩም ሲደላደል፣ ምቾቱም ድሎቱም ሲመጣ እኮ ረሳችሁን … እንደው ያ ከእናንተ ከልጆቻችን ጋር ያየነው መከራና ሥቃይ፣ እንባችን፣ እግዚኦታችንና ጸሎታችን የሚረሳ ነው፡፡ ገና ጡቶችሽ እንኳን በቅጡ ሳያጎጠጉጡ ከአጎትሽ ልጅ ጋር ጠፍተሸ ወደ በረሃ ገባሽ የተባለበትን ዜና በሰማሁ እለት ያፈሰስኩትስ እንባ ልጄ፡፡

‹‹ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ በምርጫ ሂደቱ እንዲቆይ አይፈልግም›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት


ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ እንደተሰረዙበት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በመላ አገሪቱ በተለይም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንች ማጅ፣ በምዕ/ጎጃም፣ በሲዳማ፣ በከምባታ፣ በጋሞጎፋ፣ አዲስ አበባ፣ በደቡብ ጎንደርና ጉጅን ጨምሮ በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ አንድን ዕጩ ለመሰረዝ የሚያበቃ ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት ሳይኖር ‹‹ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ታዘናል›› በማለት ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤትና ለክልል ምክር ቤቶች ያስመዘገብናቸው ዕጩ ተወዳዳሪዎቹን በመሰረዝ ከምርጫው ውድድር ውጪ እንዲሆኑ እየተደረገ እንደሆነ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡

Monday, February 16, 2015

በሁለት ወር ውስጥ ከ15 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን ገብተዋል(IOM)

 የመን ውስጥ ምላሱን የተቆረጠውን ሀፊዝ ጨምሮ 25 ኢትዮጵያዊያን ሆስፒታል ገብተዋል  ዮርዳኖስን መኪና ላይ አስረው መሬት ለመሬት ጎተቷት፣ (ሚሚ) ተደፈረች…ቃለ ምልልስ አለኝ (ግሩም ተ/ሀይማኖት) የመን ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰው በደል ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መጥቷዋል፡፡ በጅቡቲ አድርገው ቀይ ባህርን ተሻግረው ወደ የመን የሚገቡትን ኢትዮጵያዊያንን በማገት 1000 እና 1500 የሳዑዲ አረቢያ ሪያል እና ከዛም በላይ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲያስልኩ የሚያደርጉ አፋኞች መኖራችን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ መግለጼ ይታወሳል፡፡

የአማራ ህዝብ ስቃይ እንዲያበቃ ወያኔን መቅበር ይኖርብናል

ዛሬ ወያኔ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ያፈናቀላቸው አማሮች የመጀመሪያዎቹ የወያኔዎች የጥቃት ሰለባዎች አይደሉም። የመጨረሻዎቹም አይሆኑም። ወያኔ ከነ ጸረ አማራ ፖሊሲው በስልጣን እስካለ ድረስና በአማራ ስም አማራውን እያፈኑ፣ እየሰለሉ ከወያኔ ፍርፋሪ እየለቀሙ ለመኖር የቆረጡ ከአማራው መሃል የወጡ ከሃዲዎች አማራውን መቆጠጠር እስከቻሉ ድረስ የአማራ ህዝብ መራቆት፣ ስደት፣ ውርደት፣ ሰቆቃና ሞት የማይለዩት ህዝብ እንደሆነ ይቀጥላል።

Wednesday, February 11, 2015

አበበ ገላው በአባዱላ ገመዳ 2 የውሸት ዲግሪዎች ግዢ ዙሪያ ማስረጃዎችን ለቀቀ

[Updated](ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የሃሰት ዲግሪዎችን ከአሜሪካና አውሮፓ እንዲሁም ከቻይና እየገዙ እንደሚጠቀሙ በተደጋጋሚ እየተጋለጠ መሆኑ የሚታወስ ነው;; አበበ ገላው የዛሬ አንድ ወር ገደማ የዶ/ር ኮንተንጢኖስ በርሀን የሃሰት ዲግሪዎችን ያጋለጠ ሲሆን አሁን ተረኛው አባዱላ ገመዳ ናቸው ብሏል::
“ክቡር አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ አሜሪካ ሴንቸሪ ከሚባል የዲግሪ ወፍጮ ቤት የሃሰት ዲግሪዎች ገዝተው ጥቅም ላይ ማዋላቸው ተረጋገጠ” ሲል በፌስቡክ ገጹ ያስታወቀው አበበ ገላው ማስረጃዎቹን ዛሬ ለቋል::
አባ ዱላ ገመዳ የባችለር ዲግሪያቸውን እና የማስተር ኦፍ አርት ዲግሪያቸው ከአሜሪካው ሴንቸሪ ኮሌጅ በ2001 እና በ204 የገዙ ሲሆን ከ እንግሊዙ ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲም ማስተር ዲግሪያቸውን እንዳገኙ ታውቋል::

የሰማያዊ አባላት በእጩነት እንዳይመዘገቡ ምርጫ ቦርድ እንቅፋት እየፈጠረ ነው

የምርጫ ቦርድ አባላት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ለእጩነት እንዳይመገቡ እንቅፋት እየፈጠሩ መሆኑን ፓርቲውን ወክለው በእጩነት ለመመዝገብ የቀረቡት የፓርቲው አባላት  ገልጸዋል፡፡ የቀድሞ አንድነት የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበረውና በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲን የተቀላቀለው አቶ ስንታየሁ ቸኮል የትውልድ ቦታው በሆነው ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ በእጩነት እንዳይመዘገብ የምርጫ ቦርድ ተወካዮች እንቅፋት እንደፈጠሩበት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
በእጩነት ለመቅረብ በአካባቢው ለሁለት አመት መኖር ወይንም ተወላጅ መሆን 
የሚጠበቅ ሲሆን አቶ ስንታየሁ በቦታው ተወላጅ በመሆኑ መመዝገብ የሚችል ቢሆንም ‹‹ምስክር አምጣ›› መባሉን ገልጾል፡፡ ‹‹ምንም እንኳ ተወላጅ በመሆኑ መመዝገብ እችል የነበር ቢሆንም ምስክር ስወስድም ምስክሮቹን ‹ችግር ከተፈጠረ እናንተ ናችሁ ተጠያቂ የምትሆኑት› እያሉ ምስክሮቹን እያሸሹ› እንዳልመዘገብ እንቅፋት ፈጥረውብኛል›› ሲል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በሞጣ፣ በፍኖተ ሰላም፣ በባሌ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በተቀመጠው ጊዜ እንዳይመዘገቡ እንቅፋት እየተፈጠረባቸው ነው ተብሏል፡፡ አባላቱ ‹‹መረጃ አቅርቡ፣ ምስክር አቅርቡ›› ተብለው መረጃና ምስክር ይዘው ወደ ምዝገባ ጣቢያዎች ሲሄዱ ቢሮዎች ዝግ እንደሚሆኑና ‹‹አሁን ጥቆማ ነው፡፡ ምዝገባ አይደለም፡፡›› እያሉ እንደሚመልሷቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል የጋራ ምክር ቤት አባል የሆኑ ፓርቲዎችን እጩዎች በስልክም ሳይቀር እየጠሩ እንደሚመዘግቡ፣ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች ምዝገባ ጣቢያ ድረስ ሄደው ለመመዝገብ ሲያመለክቱ እንቅፋት ሲፈጥሩባቸው የብአዴን እጩዎች በአንድ ሰው ተወካይነት እንደሚመዘግቡ የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ፀኃፊ አቶ ሳሙኤል አወቀ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ሃይለማርያም ደሳለኝ የመለስን ሌጋሲ ክደው ከባላንጣቸው ከአቶ አርከበ ጋር ሽር ጉድ ማለታቸው የት ያደርሳቸው ይሆን? (ሪፖርታዥ)

HaileMariam
ምርጫ እና ድርጅታዊ ጉባኤ -አሁን ያለው አመራር ይቀጥላል
አቶ መለስ ያለሰብሳቢ በትነዋቸው የሄዱትና በዓይነ ቁራኛ የሚጠበባቁት የኢህአዴግ ባለሥልጣናት የሚተማመኑበት ድርጅት ሳያውቁት ፈርሷልና መክቶ የሚያድናቸው አይመስልም። ለምሳሌ እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲፈጠር ተቃዋሚዎቻቸውን ማራገፍ የሚችሉበት የፓርቲው መዋቅር አካል የሆነው አንዱ መሣሪያ ድርጅታዊ ጉባኤና ምርጫ ነው። በዚህ ወቅት መተማመን ስለጠፋና ከመበላላት መሰንበት ስለተመረጠ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ድርጅታዊ ጉባኤያቸው ከምርጫው በኋላ እንዲደረግ ተወስኗል። ባለፈው ከተደረገው 9ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ በኋላ 10ኛው መደረግ የነበረበት ከምርጫው በፊት ነበር። አሁን ግን መች እንደሚደረግ የት እንደሚደረግ ሳይገለጽ በእንጥልጥል እንዲቀጥሉ ተደርጓል።

Thursday, February 5, 2015

የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ


መግለጫውን የ‹ቀድሞው አንድነት ፓርቲ› አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔው አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እንዲሁም የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሌሎችን በመወከል ሰጥተዋል፡፡
‹‹የምናምነው በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ይህን ሰላማዊ ትግል ለመምራት ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ብቁ ነው ብለን በማመን ፓርቲውን ተቀላቅለናል›› ብለዋል በመግለጫው ላይ የተወከሉት አዲሶቹ የሰማያዊ አባላት፡፡
በዚህ መሰረትም በርከት ያሉ አመራሮችና አባላት በይፋ የሰማያዊ ፓርቲ የአባልነት ፎርም ሞልተዋል፡፡

Thursday, January 29, 2015

ትግሬ ብሎ ነገር…

አንዳንዶቻችን ኢህአዴግ ያጠፋውን ጥፋት ለትግሬና ለትግራይ ጠቅልላችሁ ለምን እንደምታስረክቡ አይገባኝም፡፡አንዳንዶቻችሁማ ብሶባችኃል ትንሽ ዕድልና ብዙ ሃይል ብታገኙ መታወቂያ እያያችሁ ይሄን ህዝብ ብትረፈርፉት ደስታችሁ መሆኑን ትሰብካላችሁ፡፡ወንድሞቼ ኢህአዴግ ከመላው ብሄረሰቦች የተውጣጡ እንከፎች የመሰረቱት ማህበር እንጂ ትግሬና ትግሬያዊያን የፈጠሩት ክስተት አይደለም፡፡
የአማራ መሬት ምርጥ ሰዎችን እንደማፍራቱ አዲሱ ለገሰ፣ታምራት ላይኔ፣አለምነው መኮነንን የመሰሉ በሰው ደም ሻወር የሚያምራቸው ሰዎችን አፍርቷል፡፡የኦሮሞ ህዝብ ታሪክን በብርሃን ያደመቁ ጀግኖችን እንደመውለዱ አባዱላ ገመዳ፣ሙክታር ከድር፣ግርማ ብሩን የመሰሉ አስረፍራፊዎችን ለኢህአዴግ አዋጥቷል፡፡ጉራጌ ካሱ ኢላላን፣ሲዳማ ሽፈራው ሽጉጤን፣ወላይታ ሃይለማሪያምን አሳድጓል፡፡ሶማሌ ፣ጋምቤላ ፣ሀረር ውስጥ ለተፈጠሩ እልቂቶች ምላጭ ሳቢዎቹ ፣አሰቃዮቹ ራሳቸው በአከባቢው ተወልደው ያደጉ ሳዲስቶች አልነበሩም?

በኢትዮጵያ መንግስት በጥብቅ የሚፈለጉ 3 አርቲስቶች

Kibebeew geda

ከሮቤል ሔኖክ
እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳብን በነፃነት ያለመግለጽ መብት አለመከበሩ ያጠቃው ጋዜጠኞችን ብቻ አይደለም። አርቲስቶችም ጋዜጠኞች ከሚከፍሉት መስዋእትነት ያልተናነሰ ትግል እያደረጉ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለመታደል ሆኖ የሃሳብን የመግለጽ ነጻነት በመገደቡ ዛሬ እንደ ታላቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙና ተመስገን ደሳለን ያሉ ጋዜጠኞች ያልሆነ ክስ ተልጠፎባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ። የእነዚ ታላላቅ ጋዜጠኞች ‘ወንጀል’ መንግስት እንደሚለው ሳይሆን የሕዝብን በደልና ብሶት ማሰማታቸው ብቻ ነው።

መታረም የሚገባዉ ማነዉ? ርዕዮት አለሙ ከቃሊቲ እስር ቤት

በግል የህትመት ዉጤቶች አማካኝነት በሀገሬ ዉስጥ የምመለከታቸዉን ችግሮች ለህዝብ ማቅረብና እንደዜጋም መፍትሔ ይሆናሉ ብዬ የማስባቸዉን ሀሳቦች መጠቆም ከጀመርኩ አምስት አመታት አለፉ፡፡ የመጀመሪያ ፅሑፌን ያዘጋጀሁት ” “ስህተቶችን” ለማረም የተፈፀሙ ስህተቶችና የስህተት ማረሚያ እርምጃዎች” በሚል ርዕስ እንደነበረ አስታዉሳለሁ፡፡ በዚህም ፅሑፍ የፕሬስ፣የፖለቲካፓርቲዎች ምዝገባና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የተመለከቱ አዋጆች የወጡበት ምክንያትና እንደሀገር የሚያሳድሩትን ተፅእኖ ለመዳሰስ ብሎም ኢህአዴግ ከስህተቶቹ እንዲታረም ለመምከር ሞክሬያለሁ፡፡

Ryotየኢህአዴግ ሰዎች በአንድ የገዢዉ ፓርቲ ልሳን በሆነ ድረገፅ አማካኝነት የማስጠንቀቂያ ይዘት ያለዉ ምላሽ መስጠት የጀመሩት ከላይ ከጠቀስኩት የመጀመሪያ ፅሁፌ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በአዲስፕሬስ ጋዜጣ ላይ በአዘጋጅነት ተቀጥሬ መስራት ስጀምር ግን ሁኔታዉ እየባሰ መጣ፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም አዳማ ላይ ከተለያዩ ሚዲያዎች ለተዉጣጣን ጋዜጠኞች የሰጠዉን ስልጠና ከተካፈልኩ በኋል ከስልጠናዉ ጋር በተያያዘ ለህትመት ያበቃሁት ፅሁፍ ኢህአዴጎችን በእጅጉ አስቆጣቸዉ፡፡ በመሆኑም ወደቢሮአችን ተደዉሎ ከኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የተደወለ መሆኑ ከተገለፀ በኋላ ለጽሑፌ ምላሽ የላኩ በመሆኑ በፍጥነነት እንድናወጣዉ ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጠን፡፡ ምላሻቸዉን ለማዉጣት የእነሱ መደወልም ሆነ ትዕዛዝ አስፈላጊ አልነበረም፡፡

Tuesday, January 27, 2015

በኖርዌይ ኦስሎ እንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በደማቅ ሁኔታ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

norway 1
norway ethiopian
norway ethiopian
norway ethiopian 3
                             ቀን፡ 01/26/2015
በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በዛሬው እለት ሰኞ( January 26,2015) በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በኖርዌይ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በህብረት ሁነው ከ14፡00 _15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ አካሄዱ።
የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ የነበሩትንና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአረመኔው፣ ሰው በላ፣ ጨቋኙና በአንምባ ገነኑ የወያኔ ፋሺስታዊ ቡድን የአለም አቀፍ የሰባዊ መብትን ህግ በጣሰ መንገድ በሰኔ 2014 ታፍነው እስኳሁንም ድረስ ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም እንዲሁም የእንግሊዝ መንግስት አርበኛው የነጻነት ታጋዩ አንዳርጋቸው እየተፈጸመበት ያለውን ተፈጥሮአዊና ዲሞክራሲያዊ የመብት ጥሰት ተመልክቶ ከእስር ሊወጣበት የሚችልበትን አፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ ለማሳሰብ ነው።

Sunday, January 25, 2015

በኢትዮጵያ ውስጥ አገዛዙ የሚያካሂደው አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏል – ሸንጎ

ለአስቸኳይ ስርጭት
shengoየኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) እራሱን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫነው አገዛዝ በተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ አፈናውን አጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ለመረዳት ችሏል።  በነገው ዕለት (ጥር 17 ቀን 2007 ዓ. ም) በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ (አንድነት) አስተባባሪነት ሊደረግ ከታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ አስቀድሞ የአገዛዙ የፀጥታ ኃይሎች ቢያንስ አራት የአንድነት ፓርቲ የአመራር አባላትን ማሰራቸውን ሸንጎ ተገንዝቧል።  ከታሰሩት ውስጥ፦
  1. አቶ አሥራት አብርሃም – የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ
  2. አቶ ሰለሞን ሥዩም – የአንድነት የ”ሚሊዮኖች ድምጽ” የኢዲቶሪያል ቦርድ አባል
  3. አቶ ስንታየሁ ቸኮል – የአዲስ አበባ የወጣቶች ክፍል ሃላፊ
  4. አቶ ነዋይ ገበየሁ – የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ም/ሃላፊ እንደሚገኙበት ለመረዳት ተችሏል።

Thursday, January 22, 2015

የሕሊና እስረኛዋ ርዕዮት ዓለሙ ልደት: ከርዕዮት በጎውን እንቅና !

ይድነቃቸው ከበደ
ዙርያን በመመልከት ካለንበት መጀመር ለምንም ነገር የተሻለ ነው፤ ከቤተሰብህ፣ከጓደኛ፣ከማህበረሰብ ራስን ለመረዳት እና ትርጉም ያለው ሥራ ለመስራት፣ በጎውን ለማድረግ ብንቀና ለስኬታችን ቀላል መንገድ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል “በጎውንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቀችሁ ማን ነው ? በማላት በጴጥ.መ.ምዕ 3ቁ 13 ላይ ተገልፆ ይገኛል ፡፡
1310 ቀን በእስር እያሣለፈች የምትገኘው፣የተወዳጇ የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ የልደት በዓል ፣እጅግ በጣም ደስ በሚል ሁኔታ በድምቀት ተከብሯአል፡፡ በልደት ቀኗ ተዋቂ ግለሰቦች፣የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት፣ጋዜጠኞች፣የማህበራዊ-ድረ ገፅ ዋንኛ አንቀሳቃሾች፣ ጓደኞቿ እና ቤተሰብ በመገኘት የበዓሉ ተካፋይ ለመሆን ችለዋል፡፡ በቦታው በመገኘት ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፣ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፣ኢ/ር ይልቃል ጌትነት እንዲሁም አቶ በላይ በፍቃዱ በተሰጣቸው አጭር ደቂቃ በመጠቀም ለርዮት መልካ ልደት ከመመኘት በላፈ ፣አስደማሚ ንንግር አድረገዋል፡፡